Get Mystery Box with random crypto!

ሰላም ለኵልክሙ እንደምን አላችሁ? ከዚህ በፊት በአካል የግእዝ ትምህርትን ከደረጃ አንድ እስከ ደ | ልሳነ ቀደምት

ሰላም ለኵልክሙ
እንደምን አላችሁ?

ከዚህ በፊት በአካል የግእዝ ትምህርትን
ከደረጃ አንድ እስከ ደረጃ ሦስት በርካታ ተማሪዎችን ለማፍራት ተችሏል፡፡
አብዛኛዎቻችሁ ደግሞ ትምህርቱን
በመከተተል ላይ ሳላችሁ በዓለማችን
ብሎም በሀገራችን በተከሠተው ችግር
ምክንያት ገጽ ለገጽ መቀጠል አልተቻለም፡፡

በመሆኑም ከመካካላችሁ ትምህርቱን በቴሌግራም እንድንቀጥል በተደጋጋሚ ስትጠይቁኝ ነበር፡፡እኔም የአናንተን ጥያቄ
መነሻ በመድረግ ሳስብበት ቆይቻለሁ፡፡

ትምህርቱ ገጽ ለገጽ ሳይሆን በኢንተርኔት አማካኝነት በመኾኑ በድምፅ ለማዘጋጀት (የሚያስፈልጉ መሣሪያዎች) እንዲሁም
ሌሎች ወጭዎችን ራሴ ሸፍኜ ለመስተማር አቅሜ ስለማይፈቅድ ይህንን ወጭ ለመሸፈን ያስችለኝ ዘንድ ተማሪዎች መጠነኛ ክፍያ
እየከፈሉ ለማስተማር አስቤአለሁ፡፡

በዚህ ትምህርት እንዲካተቱ የምፈለገው
እስከ አሁን ያስተማርኳቸው የ-23-ዙር ተማሪዎችን ሲኾን አብዛኛዎቻችሁ ቢያንስ
የደረጃ አንድን ትምህርት ያጠናቀቃችሁ
በመኾኑ ትምህርቱ ቢኾን ብየ ያሰብኩት
በጥያቄ እና መልስ ነው፡፡

ተማሪው በትምህርት ቀኖች ማንኛውንም
የግእዝ ጥያቄዎች ያለገደብ ያቀርባል፡፡
እኔ ደግሞ ጥያቄዎችን አንድ በአንድ
በማየት እና ጥያቄውን መነሻ በማድረግ
ሰፊ ክለሳ እና ትንተና በጽሑፍ እና በድምፅ ለማዘጋጀት ነው፡፡
ከዚህም በተጨማሪ ተማሪው ይኹን
በሚለው መንገድ ለማስተማር የምችል
በመኾኑ በቴሌግራም ለመማር፣ ለመከለስ የምትፈልጉ ተማሪዎች ለሚኖረን ቆይታ ከ 2
እስከ ሦስት ወራት ከ 100 እስከ 300 ብር እንደየ አቅማችሁ በፈቃደኝነት ለምትከፍሉ ከዚህ በታች የምጠቅሰውን ሊንክ በመጫን ወደ ትምህርቱ 'ቻናል' መግባት የምትችሉ መኾኑን መግለጽ እወዳለሁ፡፡


ወደ ቻናሉ መግቢያው ሊንክ

https://t.me/joinchat/AAAAAFhbAhb8FDJEEJf5Wg


ማሳሰቢያ
ትምህርቱ ከኹለት ወራት እስከ ሦስት
ወራት የሚቆይ ሲኾን በሳምንት ሦስት ቀን ይሰጣል።
በተረፈ ተማሪዎች በሚፈልጉት መጠን
ነገሮችን ማስተካከል የሚቻል መኾኑን
መጠቆም እወዳለሁ።

ከእናንተ ጋር ለተማሩ ለምታውቋቸው
ጓደኞቻችኹ አጋሩልኝ።

መ/ር ኃይለ ኢየሱስ መንግሥት