Get Mystery Box with random crypto!

➤ሰላም ለኩልክሙ!አርድእተ ግእዝ ➤እንቋዕ አብጽሐነ/ክሙ ➤በየወሩ በጉጉት የምንጠብቀው ወር | ልሳነ ቀደምት

➤ሰላም ለኩልክሙ!አርድእተ ግእዝ
➤እንቋዕ አብጽሐነ/ክሙ
➤በየወሩ በጉጉት የምንጠብቀው ወርኀዊው የግእዝ መርሐ ግብር በሚቀጥለው ቅዳሜ ማለትም(በ 28/6/ 12 ይከበራል። በመሆኑም ቅዳሜ የካቲት (28/6/12) ከቀኑ በ 11 ሰዐት ሁላችሁም ተጋብዛችኋል።

➤ዕለቱ የካቲት (28/6/2012) ከቀኑ 11 ሰዐት ጀምሮ በቀዳማዊ ምንሊክ ፩ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ሲሆን የሚካሄደው የግእዝ ተማሪዎች እና ወዳጆች ወርሃዊ የግእዝን ቋንቋ ማጠናከሪያ ኘሮግራም የሚከተሉት ይዘቶች የሚኖሩት ሲኾን እርስዎም ተገኝተው የግእዝ ቋንቋ ዕውቀትዎን ያዳብሩ ዘንድ ተጋብዘዋል።

➤በዕለቱ የሚቀርቡ መርሐ ግብሮች፦

በዕለት ተዕለት እንቅስቃሴአችን የምንጠቀምባቸው የንግግር ቃላት በግእዝ
በግእዝ ንግግር እና የንባብ ዘዴዎች

የግስ አገሳሰስ በቅኔ ቤት አካሄድ

በግእዝ ተምሳሌት (ተረት)

እና ቅኔዎች የቀርባሉ።

እንዲኹም ግእዝን በተመለከተ ለሚነሣ ማንኛውም ጥያቄ መልስ ይሰጣል።
➤በተጨማሪም ስለቀጣዩ መርሐ ግብር አጭር ውይይት ይኖረናል።

✥በዕለቱ መገኘት አንድም ማትረፍ ነው።
አንድም ለግእዝ ትንሣኤ አሰተዋጽዖ ማድረግ
ነው።


የፕሮግራሙ አስተባባሪ
መ/ር ኀይለኢየሱስ መንግሥት