Get Mystery Box with random crypto!

ሊቅነት-የአስተሳሰብ ለውጥ (Likawunt Consultancy)

የቴሌግራም ቻናል አርማ liquism — ሊቅነት-የአስተሳሰብ ለውጥ (Likawunt Consultancy)
የቴሌግራም ቻናል አርማ liquism — ሊቅነት-የአስተሳሰብ ለውጥ (Likawunt Consultancy)
የሰርጥ አድራሻ: @liquism
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.35K
የሰርጥ መግለጫ

ሊቅነት ለኢትዮጵያዬ
This is a High Performance industry that creates ICON'S through SUCCESS SYSTEM that never never fails.I.e

(Liquism/ሊቅነት)
Consult Us
251910369257
251929192323

Ratings & Reviews

2.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-07-14 18:31:09 ለአዕምሮአችን እንጠንቀቅ

ለሆዳችን እኮ በጣም ጥንቃቄ እናደርጋለን፤ በፍፁም የቆሸሸ ምግብ አንበላም።
ታዲያ የነገ መድረሻችንን ለሚወስነው አዕምሯችንስ??

አዕምሯችን እንደ መሬት ነው፤ የተዘራበትን ማብቀል ነው ስራው።
መልካም ነገር ከነገርነው፣ መልካም ነገር ካየ የህይወት መንገዳችን ያማረና ደስተኛ እንሆናለን።

ለአዕምሮህ ምንድነው የምትመግበው? መጥፎ ዜና ነው ወይስ መልካም ሀሳብ? ስለ ሰው አሉባልታ ነው የምታስበው ወይስ ስለ ነገ መድረሻችን? ምርጫው ያንተ ነው። መልካሙን ምረጥ።

ሊቅነትን ምረጥ!

ሸጋ ምሽት።
104 views15:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-14 12:32:44
ከምሳችን ጋር እኩል አላምጠን መዋጥ ያሉብን እውነታዎች
Real Truths You Should Believe.


ከ ታላቁ ሊቃውንት ሊቅነት ጋር
Likawunt The Great I

ለቀጣይ 21 ቀናት ይቀጥላል።
Day 7
ቀን 7

ቢመርም ዋጠው መድሃኒት ነውና!
Its Pill You Must Take it!
139 views09:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-14 08:55:21 መካከለኛ አትሁን!

አዎ! እንደነገሩ አትሁን፤ ግራ ተጋብቶ መሄጃ እንደጠፋው፣ በማንገራገር ለውሳኔ ተቸግሮ ጊዜውን እንደሚያጠፋ ሰው አትሁን።

ያልተመቸህን አልተመቸኝም፣ የተመቸህንም ተመችቶኛል ወደጅዋለው የማለት ልምድ ይኑርህ።

ከበዛው ቸልተኝነት፣ ከመካከለኛነት፣ እንደ አብዛኛው ስሜትህን ከመቆጠብ ውጣ። ምንም ቢፈጠር ግድ የማይሰጥህ፣

የጊዜህ መባከን፣ የገንዘብህ ውድመት፣ የስሜትህ መዋዠቅ የማያሳስብህ ከሆነ እራስህን ጠይቅ። በዚህ ሁኔታ ከመካከለኛነት ከፍ ማለት አትችልም፤ ነገህን ማስተካከል፣ መቀየር አትችልም።

መደበኝነት በእላይህ ላይ ይነግሳል፤ ለምንም ነገር ግድ የማይሰጥህ፣ በልተህ ማደርህ ብቻ የሚያሳስብህ፣ የሰዎች መታመም፣ መሰቃየት፣ መሞት የማይጨንቅህ፣ ቸልተኝነት ያየለብህ፣ አብዛኛው ሰው በሚያልፈለው የህይወት አዙሪት አለፈህ ኑሮህን የምታገባድድ፣ የምትቋጭ ትሆናለህ።

Don't be a MEDIOCRE!

መሃከል ምንም አዲስ ነገር የለም፤ ህይወትህን የሚቀይር፣ የሚያሻሽልልህ፣ የሚያሳልፍልህ ተግባር ቀርቶ ሃሳብም አይኖርም።

በመካከለኛነት የሚያሳልፉ ሰዎች ለሰዎች ሃሳብ፣ አስተያየት፣ እይታ፣ አመለካከት ተገዢ ናቸው፤ የሚያሳስባቸው የእነርሱ ማደግ ሳይሆን ከሌሎች የሚያገኙት ምላሽ ነው፤ ተለይቶ መታየት፣ ከፍ ብሎ መፍካት፣ መድመቅ ይፈራሉ፤ ሁሌም በለመዱት መደበኛ ህይውት መኖርን ይመርጣሉ።

ነገር ግን ማንም በመደበኛው አለም እየተመላለሰ የተራነትና የጥቅም አልባነት ስሜት እያስተናገደ እንዲኖር የተፈረደበት የለም።

አዎ! መደበኛ ሰው ያለመሆን መብቱም፣ አቅሙም አለህ። ወኔህን አጠንክር፤ ስሜትህን አጎልብት። "ለውጥ የሌለው፣ ከፍታ ላይ የማያስቀምጠኝ አሰልቺ ህይውት በቅቶኛል፤ ከሰው መጠበቅ፣ ሰው ለይ መደገፍ ሰልችቶኛል"

በል። ተነስ ተፋለም፤ አዲስ አንተን ፍጠር፤ ሌላ አንተን ሁን፤ እራስህን አግኘው፤ ከመደበኛው፣ ከመካከለኛው፣ ምንም ቢመጣ ከማይበርደው ከማይሞቀው፣ ምንም ከማይሰማው ማንነት ውጣ፤

ከፍ በል እደግ፣ ተመንደግ፤ ተዓምረኛውን አንተ ፍጠር።
ይህን ማድረግ ሂደት ነው። ሂደቱም ሲስተም ይፈልጋል። እነሆ ሊቅነት።

ልዩ የክረምት ማይንድሴት ስልጠና ሐምሌ 12 ይጀምራል።

ይምጡ።ይማሩ።ይደጉ።
Paradigm Shift Training
ስር ነቀል የአስተሳሰብ ለውጥ
በአካል/በኦንላየን
በ 0929192323 ይደውሉ።

አድራሻ
ቄራ ዳውንታውን
4ኛ/#307
142 views05:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-14 08:55:14
121 views05:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-13 12:34:27
ከምሳችን ጋር እኩል አላምጠን መዋጥ ያሉብን እውነታዎች
Real Truths You Should Believe.


ከ ታላቁ ሊቃውንት ሊቅነት ጋር
Likawunt The Great I

ለቀጣይ 21 ቀናት ይቀጥላል።
Day 6
ቀን 6

ቢመርም ዋጠው መድሃኒት ነውና!
Its Pill You Must Take it!
156 views09:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-13 06:10:56
ትልቅ ደረጃ መድረስ ከፈለጋችሁ!

በእድሜ ቆጠራ ብቻ፣ በገንዘብ ብዛት ብቻ፣ በአእምሮ እውቀትም ብቻ . . . ትልቅ ደረጃ መድረስ አይቻልም፡፡

እነዚህንና ሌሎችም ነገሮች ኖሯቸው በሕብረተሰቡ መካከል ትልቅ ደረጃ የደረሱ ሰዎች የመኖራቸውን ያህል፣ እነዚህ ነገሮች እያሏቸው ለአናሳ ነገር ሰክነውና አናሳ ሕይወት ኖረው የሚያልፉ ጥቂቶች አይደሉም፡፡

ትልቅ ደረጃ መድረስ ከፈለጋችሁ፡-


1. ከትንሽነት አመለካከት መውጣት አስፈላጊ ነው፡፡ አመለካከታችን ዛሬ ካለንበት ደረጃችን ወደላቀ ከፍታ የሚያወጣንን ራእይና አላማ ካላካተተ ይህ የአመለካከታችን ትንሽነት የማንነት አናሳነት መፍጠሩ አይቀርም፡፡

2. ከትንንሽ ንግግሮች መላቀቅ የግድ ነው፡፡ የምናወራቸው ነገሮች በእለቱ ከሚናፈሰውና የሰውን ነገር ከመብላት አልፎ ካልሄደ የንግግራችን አናሳነት የማንነት ትንሽነት መፍጠሩ አይቀርም፡፡

3. ከትንንሽ ገጠመኞች በላይ መኖር ወሳኝ ነው፡፡ በየቀኑ የሚገጥሙንን ጥቃቅን አስቸጋሪ ገጠመኞች አልፈን በመሄድ ትኩረታችንን ዋናውና ዘላቂው የሕይወታችን አላማ ላይ ካላደረግን ሁኔታው የማንነት አናሳነት መፍጠሩ አይቀርም፡፡፡፡

4. ከትንንሽ ዘሮች ዘልቆ መሄድ ጠቃሚ ነው፡፡ ትንሽ ዘር፣ ትንሽ ፍሬ … ትንሽ ሙከራ፣ ትንሽ ስኬት … ትንሽ መስዋእትነት ትንሽ ዋጋ … ትንሽ እቅድ፣ ትንሽ ውጤት ስሌቱ ይኸው ነው፡፡ ከዚህ አዙሪት ወጥተን በትልቁ መዝራት ካልጀመረን ሁታው የማንነት አናሳነት መፍጠሩ አይቀርም፡፡
172 views03:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-12 19:59:21 ስንፍና ባንተ አያምርም!

ወጣት ሆነህ ካልተለወጥክ መቼ ልትለወጥ ነው?አቅም ባለህ ሰዓት ካልሰራህ መቼ ልትሰራ ነው? ካልዘራህ እኮ አታጭድም፤ ለራሴ ያለሁት እኔ ነኝ ይሄን ወርቃማ ዕድሜዬን ተዓምር እሰራበታለው በል!

ከ 10 ዓመትም በኋላ ከሰው መጠበቅ ነው የምትፈልገው? ከራስህ አልፈህ የምትወዳቸውን ሰዎች መቀየር አትፈልግም? እርግጠኛ ነኝ ትፈልጋለህ! ስለዚህ ተነስ! የምትችለውን ሁሉ አድርግ!

ቁጭ አትበል!

የማይጠቅምህን ፕሮግራም አትይ! ጊዜ ቆሞ አይጠብቅም ንቃ ወዳጄ! ስንፍና ባንተ አያምርም!

ምርጥ ምሽት
197 views16:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-12 12:31:10
ከምሳህ ጋር እኩል አላምጠህ መዋጥ ያሉብን እውነታዎች
Real Truths You Should Believe.


ከ ታላቁ ሊቃውንት ሊቅነት ጋር
Likawunt The Great I

ለቀጣይ 21 ቀናት ይቀጥላል።
Day 5

ቢመርም ዋጠው መድሃኒት ነውና!
Its Pill You Must Take it!
213 views09:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-12 06:27:00 #የለውጥ_ሂደት

ቤትህ ውስጥ አንድ የበረዶ ቁራጭ አስቀምጠሃል እንበል ። ክፍልህ በጣም ቀዝቃዛ ነው ። ትንፋሽህ እራሱ ሲወጣ ዳመና መስሎ ይታይሃል ። የሙቀት መጠኑ 25 ዲግሪ ነው ። ከዚያ ጀምሮ ቀስ በቀስ ክፍልህ መሞቅ ጀመረች ።
26 ዲግሪ ፣ 27 ዲግሪ ፣ 28 ዲግሪ ...
ፊት ለፊት የተቀመጠው የበረዶ ቁራጭ እስካሁን ምንም አልሆነም ።

29 ዲግሪ ፣
30 ዲግሪ ፣
31 ዲግሪ ፣
እስካሁን ምንም አልተፈጠረም ።

ከዚያ 32 ዲግሪ
አሁን በረዶ መቅለጥ ጀመረ ። አስቀድሞ ከነበረው ሙቀት ብዙም የጨመረ የማይመስለው የ 1ዲግሪ የሙቀት መጨመር ትልቅ ለውጥን አመጣች ።

ብዙውን ጊዜ ሁኔታ ቀያሪ ቅፅፈቶች ቀደም ብለው የተሰሩ የብዙ ተግባራት ድምር ውጤቶች ናቸው ። እነዚህ ተደራራቢ ቅድመ ተግባራት ዋናውን ለውጥ ለማምጣት የሚያስፈልገውን አቅም ይገነባሉ ። ይህ ሁኔታ በሁሉም ቦታዎች የሚታይ ነገር ነው ። ካንሰር የሂወት ዘመኑን 80 በመቶ የሚያሳልፈው የማይታይ ሁኖ ነው ። ከዚያ የሰውነትን አካል የሚቆጣጠረው ግን በወራት ውስጥ ነው ። ሸመበቆም መሬት ለመሬት ስሮቹን በሚዘረጋባቸው አምስት አመታት ውስጥ ብዙም አይታይም ። ከዚያ ቡኀላ ነው በስድስት ሳምንታት ውስጥ በአየር ላይ እስከ 90 ጫማ ድረስ ማደግ የሚችለው ።

በተመሳሳይ ሁኔታ ልማዶችም የሆነ ወሳኝ ምዕራፍን አልፈን አዲስ ሁኔታ ውስጥ ገብተን እስክንገኝ ድረስ ምንም ለውጥ የሚፈጥሩ አይመስሉንም ። በየትኛውም ሁኔታ መጀመሪያ እና መካከለኛ ዘመን ውስጥ ብዙውን ጊዜ የመከፋት ሸለቆ ይኖራል ። ለውጥ ለማምጣት ስትነሳ የእድገት ደረጃዎችህን በማይቆራረጥ እና ወጥ በሆነ መልኩ ማየት እንደምትችል ታስባለህ ። ግን አታይም ። በመጀመሪያዎቹ ቀናት ፣ ሳምንታትና ምናልባትም ወራት አከባቢ ለውጥ የማይመጣ መስሎ መታየቱ በጣም የሚያበሳጭ ነው ። የትም ምትሄድ መስሎ አይሰማህም ። ይህ የየትኛውም የድርርቦሽ ድል መገለጫ ባህሪ ነው ። ሁልጊዜም ትላልቅ ውጤቶች የሚመጡት ዘግይተው ነው ።

ለመተው ስትታገል ራስህን ብታገኘው የመሻሻል አቅም አጥተህ እንዳይመስልህ ። ይልቁንም እንደዚህ የሚሆነው ገና የተዳፈነውን ችሎታህን ጉብታ ስላለፍክ ብቻ ነው ። "ጠንክሬ ብሰራም ውጤት አላመጣም " አይነት አቤቱታ "በረዶው ለምን በ26 ፣በ27 ወይ በ28 ዲግሪ አልቀለጠም ?" ብሎ ቅሬታ እንደ ማቅረብ ያለ ነው ። ድካምህ አልባከነም ፤ እየተጠራቀመ ነው እንጂ ። ሁሉም ድካሞች ተደማምረው 32 ዲግሪ ላይ ውጤት ማሳየት ይጀምራሉና ።

በስተመጨረሻ የእምቅ ችሎታ ጉብታህን ስታልፍ ሰዎች ስኬትህን የአንድ ቀን ሰኬት ብለው ይጠሩታል ። የውጪው ዓለም ሁሉንም የለውጥ ደረጃዎችህን አያዩም ። ሰዎች ማይት የሚችሉት ድራማዊ የሆነውን የለውጡን ፍሬ መገለጫ ብቻ ነው ። አንተ ግን ለዚህ ያበቁህ ምንም ለውጥ እያሳየህ በማይመስል ሰዓት ሁሉ የሰራሃቸው ጠንካራ ስራዎች መሆናቸውን ታውቃለህ ።

እናም ምንም እንኳን በመከፋት ሸለቆ ውስጥ ብታልፍም ለለውጥ በጣም እየቀረብክ ነውና መስራትህን ቀጥል ።

ልዩ የክረምት ማይንድሴት ስልጠና ሐምሌ 12 ይጀምራል።

ይምጡ።ይማሩ።ይደጉ።
Paradigm Shift Training
ስር ነቀል የአስተሳሰብ ለውጥ
በአካል/በኦንላየን
በ 0929192323 ይደውሉ።

አድራሻ
ቄራ ዳውንታውን
4ኛ/#307
203 views03:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-12 06:26:54
174 views03:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ