Get Mystery Box with random crypto!

በእዉቀቱ ስዩም

የቴሌግራም ቻናል አርማ esubealem — በእዉቀቱ ስዩም
የቴሌግራም ቻናል አርማ esubealem — በእዉቀቱ ስዩም
የሰርጥ አድራሻ: @esubealem
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 961
የሰርጥ መግለጫ

ወዳጄ ሆይ ቀድመህ ከራስህ ጋር ታረቅ፤ቀጥለህ አዕምሮህን ወዳጅ አድርግ!
በመጨረሻም ከአለሙ ጋር ተስማምተህ መኖር የሚያስችልህን እዉቀት ና ልምድ ታገኛለህ።
✍...BE UR SELF
ለማንኛውም አስተያየት @Esubealembot
17/08/2013 E.C

Ratings & Reviews

4.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

2

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-09-01 20:13:44 ብዙ መናገርን እንደ ጥበብ ፣ ዝምታን ደሞ እንደ አላዋቂነት ከሚቆጥሩት ራሴን አሸሻለሁ።
99 views17:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-01 19:34:53

አልጨለመም ገና - መብራትም አልበራ
እያንዳንዱ ጎጆ - ይታያል በተራ
ብዥ ብዥ በሚለው - የጊዜ ሰንሰለት
ለጥ ባለው ሜዳ - በረጅሙ ርቀት
ያለአነጋጋሪ - ስጉዋዝ እንደ እረኛ
“ብእር ብቻ” ነበር - የልቤ ጓደኛ።

[ ግጥም - አሌክሳንድር ፑሽኪን ]
[ ዶ/ር ታደለ ገድሌ እንደተረጎመው ]


ቻናላችንን ለመቀላቀል @Esubealem
@Esubealem
110 views16:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-01 14:47:10 አንድ አስተማሪ ለተማሪዎቹ ዕጭ እንዴት ወደ ቢራቢሮነት እንዴት እንደሚቀየር እያስተማሩ ነው ::

እናም ዕጩ ወደ ቢራቢሮነት ከመቀየሩ በፊት ረጅም ሰዐት ከተሸፈነበት ልባስ ለመውጣት እንደሚፈጅበት ነግረዋቸው
ማንም ተማሪ እንዳይነካው አዘው ወጡ።

ተማሪዎቹም ይህን እልህ አስጨራሽ ግብ ግብ ሲመለከቱ ቢቆዩም አንድ የዕጩን መሰቃየት ማየት ያልቻለ ተማሪ
ተነስቶ የላይኛውን ልባስ ሰበረው።

ዕጩም ያለምንም ችግር ከልባሱ ወጥቶ ቢራቢሮ መሆን ቻለ።ግን በሕይወት መኖር አልቻለም ነበር።

ምክንያቱም ዕጩ ከልባሱ ጋር የሚያደርገው ግብ ግብ ነበር ወደሙሉ ቢራቢሮነት እሚቀይረው ይህም የተፈጥሮ ሕግ ነው።


ቻናላችንን ለመቀላቀል @Esubealem
@Esubealem
153 views11:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-01 14:45:50
ቻናላችንን ለመቀላቀል @Esubealem
@Esubealem
144 views11:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-30 20:15:27 ግጥም የአመለካከት መግለጫ አይደለም ፤ ከሚደማ ቁስል የሚንቆረቆር ዜማ ነው።
108 views17:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-30 19:50:57
#መውደድ_አባ_ጸጸት

ዋሽቼ እንደነበር ምነው ባወቅሽብኝ
ጉዴን ባየሽብኝ
"በቃኝ" ስልሽ ጮኬ መርሬ አማርሬ
አርሬ አሳርሬ
"እክ እንትፍ" ስልሽ ስተፋሽ አንቅሬ
ምነው ባወቅሽብኝ. . .ጉዴን ባየሽብኝ።
. . .

ቻናላችንን ለመቀላቀል @Esubealem
@Esubealem
122 views16:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-30 18:28:13 "ከመከራችሁ የሚበዛው ራሳችሁ የመረጣችሁት ነው።"

[ ካህሊል ጂብራን ]

አንዲትም ሴት ተናገረች እንዲህም አለችው። " ስለ ስቃይ ንገርን?"
እሱም አለ ፦

"ስቃያችሁ የማስተዋላችሁ ማቀፊያ ሽፋን (ቅርፊት) መሰበር ነው..."

"በፍራፍሬዎች ውስጥ ያለው እንደ ድንጋይ የጠጠረ ፍሬ ልቡ ተከፍቶ በፀሀይ ውስጥ ይቆም ዘንድ የግድ መሰበር
እንዳለበት ሁሉ እናንተም ስቃይን ማወቅ ይገባችኋል..."

"ልባችሁንስ በህይወታችሁ የእለት ተዕለት ተዐምራት ውስጥ በአስደሳች ሁኔታ ልታቆዩት ይቻለችኋልን? ስቃያችሁስ
ከደስታችሁ ያነሰ አስደናቂ ይመስላችኋልን?"

"በእርሻ ማሳዎቻችሁ ላይ የሚፈራረቁትን ወቅቶች ሁልጊዜ በፀጋ እንደምትቀበሉዋቸው ሁሉ የልቦቻችሁን ወቅቶችም ፀጋ መቀበል ይኖርባችኋል። የሀዘናችሁን የክረምት ወራትም በፀጥታ ትጠብቃላችሁ..."

"ከመከራችሁ የሚበዛው ራሳችሁ የመረጣችሁት ነው። በውስጣችሁ ያለው ሀኪምም የራሳችሁን ህመም የሚፈውስበት
መድሀኒት አለው። ስለዚህ ሃኪሙን እመኑት እና መራራ መድሃኒቱንም በፀጥታ ተረጋግታችሁ ተጎንጩ!"


ቻናላችንን ለመቀላቀል @Esubealem
@Esubealem
145 views15:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-28 20:11:59 ሕዝቡ ጥዑም ወይን አይወድም ፤ በማይረባው ሰክሯልና...!
247 views17:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-28 08:52:04 ቻይና በጎበዝ አለቃ ተከፋፍላ "ዘመነ መሣፍንት " በመሰለ ዕጣ ፈንታ ታብታ በነበረበት ወቅት ነው።

ኮንፊሺየስ የአንድነት አስተምህሮቱን በሥነ ምግባር አሽሞንሙኖ አቀረበ። የኮንፊሺየስ ደቀመዝሙር ሆኖ በቻይና ዕጣ ፈንታ የተነካ አንድ ተማሪ መምህሩ ፊት ቀረበ።

"ምን አሰብክ" ሲል ጠየቀ ኮንፊሺየስ

"አስተምህሮትህን ወደ ተጎራባች የጎበዝ አለቃ ግዛቶች፤ ማስፋፋት"

"አደገኛ ሥፍራ እንደሆነ ታውቅ የለም?"

"አዎ"

"ታድያ?"

"እቋቋመዋለሁ" በተማሪ ወኔ

"አይመስለኝም፤እስቲ አንዳንድ ጥያቄዎችን ላቅርብልህ"

"ይቀጥሉ መምህር ሆይ"


"ለመሆኑ ወደ ቺ ግዛት ስትገባ ቢያላግጡብህ ምን ታደርጋለህ?"


"ስላልመቱኝ አመሰግናቸዋለሁ "


"ጥሩ፣ ቢመቱህስ ?"

"ስላልገደሉኝ አመሰግናቸዋለሁ "


"ቢገድሉህስ?"

"ወደ ዘላለማዊው መገኛዬ የህይወት ባህር ስለቀላቀሉኝ አመሰግናቸዋለሁ"


"መሄድ ትችላለህ " አለ ኮንፊሺየስ።


. . .በስድብ የማረን ሊመታን የሚችለው ሰው ነው፤ በአካል ማጉደል የተወን ሰው የመግደል ዕድል በእጁ ላይ ያለች ባለጊዜ ነው. . .
:
:
:
ጠላት......ካደረገው በላይ እንዳያደርግ ማን አገደው. . .?

. . .አተራረፋችን በአምላካችን መሆኑ ቀረ እንዴ?. . .


ቻናላችንን ለመቀላቀል @Esubealem
@Esubealem
277 views05:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-28 08:42:16
ቻናላችንን ለመቀላቀል @Esubealem
@Esubealem
249 views05:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ