2022-08-23 13:07:21
ንባብን ልማድ ለማድረግ የምንጠቀምባቸው መንገዶች
1. ለምን እንደምናነብ ማወቅ
አንድ ነገር ለምን ብለን መጠየቅ ካልቻልን ለማድረግ አቅም አናገኝም
2. ስለማንበብ ያሉ አሉታዊ ነገሮችን ከአስተሳሰባችን ማስወገድ
3. ለማንበብ ግዜን መወሰን
4. ከማንበብ በፊት ሶሻል ሚዲያ አለመጠቀም
ብዙዎች ትልቁ ችግራችን በአሁኑ ዘመን ሶሻል ሚዲያ ላይ የምናጠፋው ግዜ ብዙ መሆኑን አለማስተዋል ነው። ሶሻል ሚዲያ አጠገባችን አስቀምጠን ማንበብ እጅግ አስቸጋሪ ስለሆነ በንባብ ስአት ማጥፋት ወይም ከአጠገብ ማራቅ
5. ንባብን በትንሹ መጀመር
በአንድ ግዜ ብዙ ለማንበብ አለመሞከር ምክንያቱም ቶሎ ስልቹ ሆነን እንዳናቆም
አንድን መፅሐፍ በሶስት ቀን ለመጨረስ ከመሞከር በየቀኑ ትንሽ ትንሽ በማንበብ ልማድ ማድረግ
6. የሚጠቅምህን መፅሐፍ ቅድሚያ ስጠው
የምታነበውን መፅሐፍ መተግበር ከቻልክ አስተሳሰብ ላይ የሚመጣው ለውጥ ከፍተኛ ስለሚሆን ንባብን እጅግ ትወደዋለህ
7. ንባብን ከልማድ ጋር አስተሳስረው
አንድ የሀመድከው ነገር ካለ እዛ አካባቢ የምታነበውን መፅሐፍ አስቀምጠውና ትንንሽ ገፆችን በማንበብ ወደ ንባብ ባህል መምጣት ትችላለህ ከቁርስ ጋር ከሰአት ከብና በኋላ ሊሆን ይችላል ብቻ ከአንድ ልማድ ጋር አስተሳስረው
8. ለንባብ ስፍራን ምረጥ
ስታነብ ትኩረትን ከሚስብ ከምታየውም ሆነ ከምትሰማ ራቅ በል
ሀሳብን ሰብስቦ ለነገሩ ትኩረት ሰጦ ለማንበብ እጅግ ጠቃሚ ነው።
9. መፅሐፍን የመጨረስ ልማድ ይኑርህ
ትልቅ መፅሐፍ ጀምረህ የማትጨርስ ከመሞከር ትንሽ ገፅ ያለውን መፅሐፍ በማንበብ መጨረስን ግብ አድርግ
10. ያነበብከውን መፅሐፍ ማካፈል ልማድ አድርግ
የምታነበው መፅሐፍ ለአንተ ብቻ ሳይሆን ለሌሎች እንደሆነ አስተውል ባካፈልክ ቁጥር ለአንተ ይጨመራል አንተም ስታወራው በበለጠ መፅሐፉን ማስተር ታደርገዋለህ
11. መፅሐፍ መግዛት ልማድ አድርግ
መፅሐፍ መግዛት በራሱ ለማንበብ ያነሳስሀል ደግሞ አእምሮ ላይ ኢይቨስትመንት ማድረግ ስለሆነ ኩራት ይሰማሃል አንድ ቀን ታነባለህ!!
12. የመፅሐፍ ሰመሪ ማንበብ
ሰመሪ ስታነብ መፅሐፉን ለማንበብ ያነሳስሀል ስለዚህ በኢንተርኔት ውስጥ በመግባት ብዙ ሰመሪዎችን በኦዲዮ ሆነ በፅሁፍ መጠቀም አንዱ መንገድ ነው።
ልህቀት ላይብረሪ
ከሰማሁተና ካነበብኩት በተሞክሮ የታየ ነው።ቨ
275 views10:07