Get Mystery Box with random crypto!

Zoe Hailu Ministries (Galilee.TV)

የቴሌግራም ቻናል አርማ lifeofgodzoe — Zoe Hailu Ministries (Galilee.TV) Z
የቴሌግራም ቻናል አርማ lifeofgodzoe — Zoe Hailu Ministries (Galilee.TV)
የሰርጥ አድራሻ: @lifeofgodzoe
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 2.03K
የሰርጥ መግለጫ

➢.የተጠራችሀት ለዚህ ነውና ክርስቶስ ደግሞ ፍለጋውን እንድትከተሉ ምሳሌ ትቶላችሁ ስለእናንተ መከራን ተቀብሎአልና ።1ኛጼጥ2፣21 👉 @zoehailu
👉እኔ የክርስቶስ ተከታይ እንጂ አጃቢው አይደለሁም!

Ratings & Reviews

1.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

2


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-08-28 10:08:38 1ኛ ዮሐንስ 5
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
⁹ የሰውን ምስክር ብንቀበል የእግዚአብሔር ምስክር ከእርሱ ይልቅ ይበልጣል፤ ስለ ልጁ የመሰከረው የእግዚአብሔር ምስክር ይህ ነውና።
¹⁰ በእግዚአብሔር ልጅ የሚያምን በነፍሱ ምስክር አለው፤ በእግዚአብሔር የማያምን እግዚአብሔር ስለ ልጁ የመሰከረውን ምስክር ስላላመነ ሐሰተኛ አድርጎታል።
¹¹ እግዚአብሔርም የዘላለምን ሕይወት እንደ ሰጠን ይህም ሕይወት በልጁ እንዳለ ምስክሩ ይህ ነው።
¹² #ልጁ_ያለው_ሕይወት_አለው፤ የእግዚአብሔር ልጅ የሌለው ሕይወት የለውም።
¹³ የዘላለም ሕይወት እንዳላችሁ ታውቁ ዘንድ በእግዚአብሔር ልጅ ስም ለምታምኑ ይህን ጽፌላችኋለሁ።
https://t.me/lifeofGodzoe
ከ zoe ማስታወሻ ወዳጄን ኢየሱስን ኑና እዩት
16 viewsGod Is Good, edited  07:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-27 17:56:21 አንድ እግዚአብሔር አለና፥ በእግዚአብሔርና በሰውም መካከል ያለው መካከለኛው ደግሞ አንድ አለ፥ እርሱም ሰው የሆነ ክርስቶስ ኢየሱስ ነው፤  ራሱንም ለሁሉ ቤዛ ሰጠ፥ ይህም በገዛ ዘመኑ ምስክርነቱ ነበረ፤ (1ኛ ጢሞ 2፥5-6)

#መታረቃችን_በሞቱ_መዳናችን_በሕይወቱ!

ኢየሱስ የማዳንን ስራ አንድ ጊዜ  በመስቀል ላይ ፈፅሟል ነገር ግን ዛሬም ድረስ ህያው ነው፨ የዛሬ 2000 ዓመት የተሰራው ስራ አሁንም ትኩስነቱ እንዳለ ነው፨#ከእግዚአብሔር_ጋር_መታረቃችን_በኢየሱስ_ሞት አንድ ጊዜ የተጠናቀቀና የተፈጸመ ቢሆንም #መካከለኛነቱ ግን ዛሬም ድረስ ነው ወደፊትም ይኖራል፨

በእርግጥ ክርስቶስ ኢየሱሰ ዛሬ ስለመታረቃችን አንዳች የሚያደርገው ስራ የለም፨ በሰማያት በግርማው ዙፋን ቀኝ ያለው ሊቀ ካህናችን ኢየሱስ ክርስቶስ እንደ ቀደሙት የብሉይ ካህናት ዕለት ዕለት ስለ በደልና ስለ ኃጢአት የሚሆን ማናቸውንም ዓይነት መስዋዕት አያቀርብም፨ ለመስቀል ሞት ራሱን አሳልፎ ሲሰጥ ይህን አንድ ጊዜ ፈጽሞ አድርጎታልና፨ ስለዚህ የክርስቶስ የማስታረቅ ሥራ የተጠናቀቀ ነው ማለት ነው፨ ይህ ማለት መካከለኝነቱ ተጠናቋል ማለት ነውን?  አይደለም!!! መጽሐፍ እንዲህ ይላል

" ጠላቶች ሳለን ከእግዚአብሔር ጋር በልጁ ሞት ከታረቅን፥ ይልቁንም ከታረቅን በኋላ በሕይወቱ እንድናለን " (ሮሜ 5፥10)

መታረቃችን በሞቱ መዳናችን ግን በሕይወቱ ነው፨ ለመታረቃችን መካከለኛ የነበረው ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ዛሬም ለሰዎች መዳን መካከለኛ ነው፨

ሐዋርያው ሲናገር ከተናገርነውም ዋና ነገሩ ይህ ነው፤ በሰማያት በግርማው ዙፋን ቀኝ የተቀመጠ እንዲህ ያለ ሊቀ ካህናት አለን፤ እርሱም የመቅደስና የእውነተኛይቱ ድንኳን አገልጋይ ነው፥ እርስዋም በሰው ሳይሆን በጌታ የተተከለች ናት። (ዕብ 8፥1-2)

በዚህ በማያልፍ ሕይወት ኃይል በመልከ ጸዲቅ ሹመት የዘላለም ሊቀ ካህን በሆነበት ሰማያዊ አገልግሎቱ ነው ሰዎች የሚድኑት!  የማዳኑ ስራው ከማያልፈው ሕይወቱና በግርማው ዙፋን ቀኝ ካለው ሰማያዊ አገልግሎቱ ጋር የተወዳጀና የተቆራኘ መሆኑ ግልፅ ነው!

አሁንም ሐዋርያው በዚህ ከሰማያዊ አገልግሎቱ ጋር በተያያዘ ሲመሰክር " ስለ እነርሱም ሊያማልድ ዘወትር በሕይወት ይኖራልና ስለዚህ ደግሞ በእርሱ ወደ እግዚአብሔር የሚመጡትን ፈጽሞ ሊያድናቸው ይችላል። " (ዕብ 7፥25) ያለውም ለዚህ ነው!

#ትናንት_ያዳነን_ዛሬም_ነገም_የሚያድን_ኢየሱስ_ብቻ_ነው!
"ኢየሱስ ክርስቶስ ትናንትና ዛሬ እስከ ለዘላለምም ያው ነው። " (ዕብ 13፥8)
https://t.me/lifeofGodzoe
ከ zoe ማስታወሻ ወዳጄን ኢየሱስን ኑና እዩት
192 viewsZoe , 14:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-11 09:21:20 ዘጸአት 34
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
⁵ #እግዚአብሔርም_በደመናው ውስጥ ወረደ፥ በዚያም ከእርሱ ጋር ቆመ፥ የእግዚአብሔርንም ስም #አወጀ።
⁶ እግዚአብሔርም በፊቱ አልፎ፦ እግዚአብሔር፥ እግዚአብሔር መሐሪ፥ ሞገስ ያለው፥ ታጋሽም፥ ባለ ብዙ ቸርነትና እውነት፥
⁷ እስከ ሺህ ትውልድም ቸርነትን የሚጠብቅ፥ አበሳንና መተላለፍን ኃጢአትንም ይቅር የሚል፥ በደለኛውንም ከቶ የማያነጻ፥ የአባቶችንም ኃጢአት በልጆች እስከ ሦስትና እስከ አራት ትውልድም በልጅ ልጆች የሚያመጣ አምላክ ነው ሲል አወጀ።
https://t.me/lifeofGodzoe
ከ zoe ማስታወሻ ወዳጄን ኢየሱስን ኑና እዩት
568 viewsZoe , edited  06:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-05 19:10:06 #በእኛ_ስፍራ_የሚቆም {Holy spirit }
#አገልጋይ_ዞዊ(Zσє)
ʝσιи https://t.me/lifeofGodzoe
ከ zoe ማስታወሻ ወዳጄ ኢየሱስን ኑና እዩት
654 viewsGod Is Good, 16:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-01 12:42:19 #እግዚአብሔር_መልካም_ነዉ!
#አገልጋይ_ዞዊ(Zσє)
ʝσιи https://t.me/lifeofGodzoe
ከ zoe ማስታወሻ ወዳጄ ኢየሱስን ኑና እዩት
726 viewsZoe , 09:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-25 15:13:34 #ዓይኖቼን_ክፈት!
#አገልጋይ_ዞዊ(Zσє)
ʝσιи https://t.me/lifeofGodzoe
ከ zoe ማስታወሻ ወዳጄ ኢየሱስን ኑና እዩት
846 viewsGod Is Good, edited  12:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-21 18:41:56 ➬"የአንድ ተልዕኮ ስኬት ከአንተ ጋር ባሉት ሰዎች ታማኝነት ላይ ይመረኮዛል"!
    ታማኝነት እንዲሰፍን ተጋደል!
https://t.me/lifeofGodzoe
ከ zoe ማስታወሻ ወዳጄ ኢየሱስን ኑና እዩት
1.0K viewsZoe , 15:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-03 02:13:15 #በታላቅ_ፍቅር_ተወደናል!
➬ክርስቶስ በፍቅር ለእኛ መዳን እና መለወጥ የባሪያን መልክ ያዘ! ክርስቶስ በፍቅር ለመስቀል ሞት እንኳን የታዘዘ ሆነ! ነገር ግን የባሪያን መልክ ይዞ በሰውም ምሳሌ ሆኖ ራሱን ባዶ አደረገ፥ በምስሉም እንደ ሰው ተገኝቶ ራሱን አዋረደ፥ ለሞትም ይኸውም የመስቀል ሞት እንኳ የታዘዘ ሆነ። ፊልጵስዩስ ሰዎች 2፥7-8
#ክርስቶስ_የፍቅርን_ምሳሌ_ትቶልናል! ክርስቶስ እንደወደደን በፍቅር ልንመላለስ ይገባል!
ክርስቶስም ደግሞ እንደ ወደዳችሁ ለእግዚአብሔርም የመዓዛ ሽታ የሚሆንን መባንና መሥዋዕትን አድርጎ ስለ እናንተ ራሱን አሳልፎ እንደ ሰጠ በፍቅር ተመላለሱ። ኤፌሶን 5፥2
ክርስቶስ ራሱን አሳልፎ እንደሰጠን እኛም ስለወንድሞቻችን ራሳችንን አሳልፈን ልንሰጥ ይገባል፨
እርሱ ስለ እኛ ነፍሱን አሳልፎ ሰጥቶአልና በዚህ ፍቅርን አውቀናል፤ እኛም ስለ ወንድሞቻችን ነፍሳችንን አሳልፈን እንድንሰጥ ይገባናል። 1ኛ ዮሐንስ 3፥16
ክርስቶስ እንደወደደን እርስ በእርሳችን ልንዋደድ ይገባል! እርስ በርሳችሁ ትዋደዱ ዘንድ፥ እንደ ወደድኋችሁ እናንተ ደግሞ እርስ በርሳችሁ ትዋደዱ ዘንድ አዲስ ትእዛዝ እሰጣችኋለሁ። ዮሃንስ 13፥34
ጳውሎስ ለክርስቶስ ቤተክርስትያን አገልግሎት በፍቅር በሙሉ ፈቃደኝነት ራሱን ባሪያ አድርጎ ሰጠ፨
ሐዋርያ ሊሆን የተጠራ የኢየሱስ ክርስቶስ ባሪያ ጳውሎስ በነቢያቱ አፍ በቅዱሳን መጻሕፍት አስቀድሞ ተስፋ ለሰጠው ለእግዚአብሔር ወንጌል ተለየ።
ሮሜ 1፥1-2
በታላቅ ፍቅር ተወደናል! እርሱ እንደወደደን እርስ በእርሳችን ልንዋደድ ይገባናል!
እኔ እንደ ወደድኋችሁ እርስ በርሳችሁ ትዋደዱ ዘንድ ትእዛዜ ይህች ናት። ነፍሱን ስለ ወዳጆቹ ከመስጠት ይልቅ ከዚህ የሚበልጥ ፍቅር ለማንም የለውም። ዮሃንስ 15፥12-13
https://t.me/lifeofGodzoe
ከ zoe ማስታወሻ ወዳጄ ኢየሱስን ኑና እዩት
1.8K viewsZoe , edited  23:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-29 11:25:29 "ልባችሁን ልክ እንደ ፅላት ስታቀርቡ የቃሉ መገለጥ ብቻ ሳይሆን ያ_መገለጥ ፍሬ የሚያፈራበትን የመንፈሱን አሰራር አብራችሁ ትቀበላላችሁ"! Zσє
https://t.me/lifeofGodzoe
1.3K viewsBertukan Taddesa, edited  08:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-28 09:07:05 #ወደፈተና_አለመግባት_ይቻላል!
ብዙ ሰዎች ስለፈተና ያላቸው እውቀት ውስን ስለሆነ ፈተና በቀላሉ ይጥላቸዋል! ስለፈተና ምንም ማድረግ እንደማይችሉ እድላቸውን ብቻ እንደሚሞክሩ ይሰማቸዋል፨ነገር ግን ስለፈተና የሆነ ነገር ማድረግ ይቻላል፨►ፈተና ፈተና ነው! ፈተናን ለማለፍ እውቀትን ጥንቃቄንና ትጋትን ይጠይቃል! ፈተና የሚመጣው ካልተዘጋጀን ሊጥለን ነው! ወደ ፈተና አለመግባት ማለት ፈተናው በእኛ ላይ ያለው እኛን የመጣል አላማ ሳይሳካለት ሲቀርና ፈተናውን በድል ስናልፈው ነው! ወደ ፈተና አለመግባት ግን እንዴት ደስ የሚል ነገር ነው?? ብዙ ሰዎች ግን ለፈተናው ያልበቁ ሆነው በፈተና ወድቀዋል! ከመንገዳቸውም ተሰናክለዋል! ወደፈተና አለመግባት ይቻላል፨ ተፈትኖ ማለፍን የመሰለ የሚያስደስት ነገር የለም! ደስ የሚለው ነገር ደግሞ ወደ ፈተና አለመግባት ይቻላል፨ ፈተና በሞላበት አለም ወደፈተና አለመግባት እንዴት ድንቅ እድል ነው፨ ችግሩ በምቹና በሰላሙ ጊዜ ፈተና የሚመጣ የሚመጣም አይመስል፨ ፈተና እጅግ ሩቅ ቦታ ያለና ለመምጣት ብዙ ጊዜ የሚፈጅበት ነው የሚመስለው፨ ባይመስልም ግን ፈተና መምጣቱ አይቀርም፨ ፈተና ግን ቢመጣ ሳይሆን ሲመጣ ነው የሚባለው፨ በዚያ ላይ መቼም እንደሚመጣ አለማወቃችንም ነው ፈተናን ፈተና ያደረገው፨ ፈተና አዘገጋጅተቶ አስጠንቅቀቁ ❶ ❷ ❸ብሎ ቀን ቆጥሮ አይመጣም፨ ፈተና ድንገት ነው የመሚመጠጣው!
መልካሙ የምስራች ግን ፈተና መጥቶ በእኛ ላይ ግን አንዳች እንዳያደርግና በሰላም እንድናልፈው ማድረግ እንደሚቻል መፅሃፍ ቅዱስ ያስተምራል፨ #አለቃዬ_አስተማሪዬ_አምላኬ_አባቴ_ወዳጄ_ኢየሱስ፤ ፈተና ሲመጣ #እንዳይጥለንና+እንዳይወስደን ምን ማድረግ እንዳለብን ይናገራል፨
ፈተና ሳይመጣ በሰላሙ ቀን በምቾቱ ቀን ለፈተና ቀን በሚገባ መዘጋጀት ይቻላል! ወደፈተና አለመግባት የሚቻለው #ተግቶ_በመፀለይ ነው!
"ወደ ፈተና እንዳትገቡ ትጉና ፀልዩ"፣ ማቴዎስ 26፥41
https://t.me/lifeofGodzoe
ከ zoe ማስታወሻ ወዳጄን ኢየሱስን ኑና እዩት
944 viewsZoe , 06:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ