Get Mystery Box with random crypto!

Berbir Mereja / በርብር መረጃ

የቴሌግራም ቻናል አርማ lidinacomp — Berbir Mereja / በርብር መረጃ B
የቴሌግራም ቻናል አርማ lidinacomp — Berbir Mereja / በርብር መረጃ
የሰርጥ አድራሻ: @lidinacomp
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 782
የሰርጥ መግለጫ

☘️ትኩስና አዳዲስ መረጃ ለማግኘት በTelegram፣ Facebook ና Youtube ቻናል ይቀላቀሉን 👇👇👇
👉👉Telegram :- https://t.me/lidinacomp
👉👉Facebook--› https://www.facebook.com/berbirmereja/
👉👉Youtube: - https://is.gd/HNOSmr

Ratings & Reviews

3.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-08-05 21:46:20

61 viewsLidetu G, 18:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-05 19:50:47
#HappeningNow

ኢትዮ ቴሌኮም ቴሌብር መላ፤ ቴሌብር እንደኪሴ እንዲሁም ቴሌብር ቁጠባ የተሰኙ የፋይናንሻል አገልግሎቶችን ዛሬ በስካይ ላይት ሆቴል በማስተዋወቅ ላይ ይገኛል።

ቴሌ ብር መላ፦ የቴሌብር ደንበኞቹን ባንቀሳቀሱት የገንዘብ ዝውውር መሰረት ታይቶ እስከ በቀን እስከ 2,000 በወር ደግሞ እስከ 10,000 ብር የሚደርስ ብድር የሚያመቻች አገልግሎት ነው።

ቴሌ ብር እንደኪሴ ፦ በቴሌብር አማካኝነት ግብይት በሚፈጸምበት ጊዜ የቴሌብር ሂሳቦ ከሚገዙት እቃ በታች ከሆነ ቀሪውን ክፍያ ጨምሮ ለሻጭ ይከፍልና ገንዘብ ገቢ ሲያደርጉ ከሂሳቦ ላይ ተቀናሽ የሚያደርግ አገልግሎት ነው።

ቴሌብር ቁጠባ፦ ቴሌብር ላይ ካለው የገንዘብ መጠን ላይ መቆጠብ የሚያስችል አገልግሎት ሲሆን በሁለት አማራጮች ማለትም በወለድና ያለወለድ የቀረበ ነው። የወለድ መጠኑም 7% ሲሆን ወለዱ መጠን በቀን ተሰልቶ በሂሳቦ ገቢ ይደረጋል።

Telegram :- https://t.me/lidinacomp

Facebook--› https://www.facebook.com/berbirmereja/

Youtube: - https://is.gd/HNOSmr
107 viewsLidetu G, 16:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-05 18:39:43

124 viewsLidetu G, 15:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-05 16:39:52 ወደ ኢትዮጵያ ዘልቆ በመግባት ወረራ ለመፈጸም የሞከረው የአልሸባብ ሃይል በተደጋጋሚ መመታቱ ሲገለጽ ቆይቷል። ዛሬ ይፋ እንደሆነው ደግሞ ከ800 በላይ የአልሸባብ ታጣቂዎች የተገደሉ ሲሆን መቶ ተማርከዋል።

የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፌ በቲውተር ገጻቸው ምስል አስደግፈው ይፋ እንዳደረጉት ይህ በጥቅም ተደልሎ ወደ ኢትዮጵያ ለመዝለቅ ያሰበው ሃይል የተመታው ሁለተኛ እንዳያስብ ተደርጎ ነው።

በሚያራምዱት አቋምና አካታች ፖለቲካ ጥርስ የተነከሰባቸው፣ አልፎም “አሸባሪ” እየተባሉ ሰሞኑንን ዘመቻ የተከፈተባቸው ሙስጠፌ ሰራዊቱን በማስተባበርና ሞራል በመስጠት የቅርብ እገዛ ሲያደርጉ እንደነበር ተመልክቷል።

“አሸባሪው ወደ ድንበር ለመጠጋት እንዳያስብ ተደርጎ ተመቷል” ሲሉ በቲውተር ገጻቸው አስፍረዋል።

ስለጥቃቱ መረጃ የሰጡ እንዳሉት የኢትዮጵያ አየር ሃይል በዘመናዊ ቴክኖሎጂ በመታገዝ የአሸባሪዎን ሃይል ከያለበት በመለብለብ ለግረኛው ሃይል ሰፊ ድጋፍ አድርጓል።

አሰቅድሞ የሎጂስቲክ አቅማቸውን ያመከነው የኢትዮጵያ አየር ሃይል የውሰደው እርምጃና እግረኛው ሃይል ተናቦ ያካሄዱት ጥቃት ለሌሎችም ትምህርት የሚሰጥ መሆኑን የገለጹ “አሁን የኢትዮጵያን መከላከያ መተናኮስ ከቴክኖሎጂ ጋር መጫወት ነው። አያዋጣም። ትህነግም ውጊያ ካሰበ ተመሳሳይ እርምጃ ይወሰድበታል” ሲሉ አሁን ላይ የኢትዮጵያ መከላከያ የደረሰበትን አቋም ገልጸዋል።

የሶማሌ ክልል ልዩ ሃይል በሚያስደንቅ ብቃትና ዕልህ ግዳጁን በመወጣት ላይ መሆኑንን ያመለከቱት ክፍሎች አክለውም ” ሙስጣፊ ላይ የተከፍተው ዘመቻ ለምንና በምን መነሻ እንደሆነ ዛሬ ግልጽ ሆኗል” ብለዋል።

አቶ ሙስጣፌ የትህነግትን የቀደመ ሶማሌ ክልልን የማተራመስ እቅድ በማክሸፍና ክልሉን በማረጋጋት ኢትዮጵያዊያን በሰላም ሳይፈሩ አብረው እንዲኖሩ በማድረጋቸው እንደ ምስሌ የሚጠቀሱ መሪ ናቸው። ይህንን የሚጠሉ በተቃራኒው ” ለምን ዕቅድቻንን አፈረስክ” በሚል የጥላቻ ዘመቻ እንደሚከፍቱባቸውና እየከፈቱባቸው እንደሆነ ይታወቃል።

Telegram :- https://t.me/lidinacomp

Facebook--› https://www.facebook.com/berbirmereja/

Youtube: - https://is.gd/HNOSmr
128 viewsLidetu G, 13:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-05 14:54:21
ተወዳጁ የእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ ዛሬ ምሽት ይጀመራል

የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ከወራት እረፍት በኋላ ዛሬ ሲጀመር የጥቁሮች ህይወት ያገባኛል በሚል የጀመረው ድጋፍ እንዲቆም መወሰኑን ቀደም ብሎ አሳውቋል። ድርጊቱ እንዲቆም የተወሰነው የታሰበውን ለውጥ ማምጣት ባለመቻሉ ነው ተብሏል።

የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ዛሬ ክሪስታል ፓላስ ከአርሴናል ምሽት 4 ሰዓት ላይ በሼልስት ፓርክ ሰታዲየም በሚያደርጉት ጨዋታ ይጀመራል፡፡ እስቲ ለዛሬ የመጀመሪያ ሳምንት የሚደረጉ የእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ ጨዋታዎችን እንጠቁማችሁ።

Telegram :- https://t.me/lidinacomp

Facebook--› https://www.facebook.com/berbirmereja/

Youtube: - https://is.gd/HNOSmr
131 viewsLidetu G, 11:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-05 14:53:03
ዋይት ሃውስ አቅራቢያ የወደቀው መብረቅ አራት ሰዎችን ክፉኛ አቆሰለ

ሐሙስ አመሻሽ አራቱን ሰዎች የመታው የመብረቅ አደጋ የደረሰው የዋይት ሃውስ አጥር አጠገብ ካለ ዛፍ ጎን ነው። የአካባቢው የድንገተኛ አደጋዎች ባለስልጣናት እንዳሉት በመብረቁ የተመቱት ሁለት ወንዶች እና ሁለት ሴቶች ዋይት ሃውስ አቅራቢያ ባለ ፓርክ ውስጥ ሳሉ ነበር።

ፓርኩ ለአሜሪካ የፕሬዝዳንት መኖሪያ ካለው ቅርበት የተነሳ ተጎጂዎችን ለመርዳት ቀድመው በስፍራው ከደረሱት መካከል የደህንነት አባላት እንደነበሩበት ተገልጿል።

የዋሽንግተን ዲሲ የእሳት እና ድንገተኛ አደጋ በሰጠው መግለጫ “አራቱም ከከባድ እስከ ለሕይወት አስጊ የሆነ ጉዳት አስተናግደዋል። አራቱንም በፍጥነት አካባቢው ወደሚገኙ ሆስፒታሎች ተወስደዋል" ብሏል።

Telegram :- https://t.me/lidinacomp

Facebook--› https://www.facebook.com/berbirmereja/

Youtube: - https://is.gd/HNOSmr
136 viewsLidetu G, 11:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-05 14:51:21
#ጾመ_ፍልሰታ

የ2014 ዓ.ም ጾመ ፍልሰታን በተመለከተ የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖትከዋሽንግተን ዲሲ፤ ሰሜን አሜሪካ መልዕክት አስተላልፈዋል።

ከመልዕክታቸው የተወሰደ ፦

" ሁላችንም እንደምንገነዘበው በአሁኑ ጊዜ የኢትዮጵያ ሕዝብ ፍላጎት ፍጹም ሰላም ያላት ሀገር እንድትኖረው ነው፤ ይህ ትክክለኛ ፍላጎት ነው፡፡ ይሁንና ያለ እግዚአብሔር ፈቃድ ሁሉም ነገር ስለማይሆን ፍጹም ሰላም በሀገር ሰፍኖ ሕዝባችን እግዚአብሔር በሰጠው ምድር በፍቅር፣ በአንድነት በነጻነትና በእኩልነት እንዲኖር ኢትዮጵያውያንና ኢትዮጵያውያት ሁሉ በዚህ ወቅት የቅድስት ድንግል ማርያምን ጸሎትና ስእለት ተማኅፅኖና አስተበቊዖት አጋዥ አድርገን በልዩ ሱባዔ ወደ እግዚአብሔር በመቅረብ በንሥሐ፣ በጾም፣ በጸሎት፣ ነዳያንን በመርዳትና ቅዱስ ቊርባንን በመቀበል እሱን መማፀን ይኖርብናል፡፡

... በሀገራችን የተከሠቱት ያላስፈላጊ ግጭቶችን በድርድር ለመፍታት እየተሞከሩ ያሉ አንዳንድ የሰላምና የውይይት ድምፆች ተስፋ ሰጪ ስለሆኑ ሥር ሰደው፣ በተግባር ተተርጉመው፣ ለተጐዳው ሕዝባችን መጠገኛ ይሆኑ ዘንድ፣ ኢትዮጵያውያንና ኢትዮጵያውያት ሁሉ በዚህ ዙርያ በሱባዔው ወቅት ወደ እግዚአብሔር አቤት በማለትና ሂደቱን በመደገፍ የበኩላቸውን ጥረት እንዲያደርጉ፣ መንግሥትም ሆነ የዓለም አቀፉ ማኅበረ ሰብ በዚህ በጎ ሐሳብ እንዲገፉበትና ሕዝባችንንና ሀገራችንን ከጥፋት እንዲታደጉ አባታዊ መልእክታችንን በእግዚአብሔር ስም እናስተላልፋለን፡፡

እግዚአብሔር አምላክ ጾሙን የሰላም፣ የሥርየት፣የፍቅር፣ የአንድነት ጾም ያድርግልን።

ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን ይባርክ
ወስብሐት ለእግዚአብሔር አሜን "

(ሙሉ መልዕክታቸው ከላይ ተያይዟል)
119 viewsLidetu G, 11:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-05 14:18:58
"ቻይና ታይዋንን ከዓለም አቀፍ መድረኮች አስገልላ ልታስቀራት አትችልም" - ናንሲ ፔሎሲ

ሰሞንኑ የአለምን ትኩረት በሳበ ሁኔታ በደቡብ እስያ ቀጣና ጉብኝት ያደረጉት የአሜሪካ ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ናንሲ ፔሎሲ ቻይና ታይዋንን ከዓለም አቀፍ መድረኮች አስገልላ ልታስቀራት አትችልም ሲሉ ተናግረዋል። ፔሎሲ ይህ እንዲሆን "አሜሪካ አትፈቅድም" ብለዋል።

አክለውም ታይዋን በእንዲህ ዐይነት መድረኮች እንዳትሳተፍና ባለስልጣናቶቿ እንዳይጓዙ ሊያደርጉ ቢችሉም እንኳን እኛን ግን ሊያስቀሩን አይችሉም፤ "የጉዞ እቅዳችንንም እነሱ አያወጡልንም" ሲሉም ነው ፔሎሲ የተናገሩት። የአሜሪካ ባለስልጣናት ወደ ታይዋን መጓዛቸው እንደሚቀጥልና የታይዋን ባለስልጣናትም ይሄንኑ እንደሚያደርጉም ገልጸዋል።

Telegram :- https://t.me/lidinacomp

Facebook--› https://www.facebook.com/berbirmereja/

Youtube: - https://is.gd/HNOSmr
125 viewsLidetu G, 11:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-05 08:57:21

180 viewsLidetu G, 05:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ