Get Mystery Box with random crypto!

Psychiatry ላይ ያለ አንድ ነገር ትዝ ብሎኝ ነው... አንዳንድ የጭንቀት ታማሚዎች ለምናልባ | 📗ከመፅሐፍት.ዓለም📗

Psychiatry ላይ ያለ አንድ ነገር ትዝ ብሎኝ ነው...

አንዳንድ የጭንቀት ታማሚዎች ለምናልባት ወይም ቢነሳብኝ ብለው መድሃኒታቸውን ይዘው ይንቀሳቀሳሉ። ታዲያ መድሃኒቱን ስለያዙት ብቻ የጭንቀቱ መምጣት ይቀንሳል። ምክንያቱም መድሃኒቱን መጠቀሙን ብቻ ሳይሆን እራሱ መድሃኒቱን ከጭንቀት ቅነሳ ጋር አስተሳስረው እንዲያምኑ(conditioned) ሆነዋል።

ሰሞኑን ደሞ Joey Diaz የJoe Rogan ቆየት ያለ podcast ላይ፥ ስለ አለፈ የCocaine ሱሱ ሲያወራ ይህን የመሰለ ነገር አለ። የፊልም ቀረፃ ላይ ውሎ እየተጠዳደፈ ወደ Cocaine ግዢው ይሄዳል። እና ልክ ገዝቶ በእጁ እንዳስገባው ወይም ወደ ቤት ሲሄድ የሚጠብቀው Cocaine እንዳለ ማወቁ ብቻ እረፍት እንደሚሰጠው ይናገራል። ከመጠቀሙ ባልተናነሰ ሁኔታ የነገሩ መኖር የሚያረጋጋ ይሆናል ማለት ነው።


እና ምን አሰብኩ... እቺን ነገር ብዙ ነገር ላይ አፕላይ ልናረጋት አንችልም? የማንጠቀማቸው ግን የያዝናቸው ብዙ ነገሮች የሉም? ልንጠቀማቸው የማንፈልጋቸው ግን ደሞ ብንለቃቸው የሚቸግረን ነገሮች የሉም? እንደው ከአቅም በላይ ሲሆን የምንሻቸው፥ እስከዚያ ግን ይዘናቸው የምንቆይ ነገሮች? ወይም ሰዎች?

ለመረጋጋት ስንል...



@leywo