Get Mystery Box with random crypto!

በኬንያ 21 ኢትዮጲያውን ስደተኞች የረሃብ አድማ አድርገዋል መባሉን ተከትሎ መንግስት ዜጎቹን ወደ | ልዩ መረጃ ®

በኬንያ 21 ኢትዮጲያውን ስደተኞች የረሃብ አድማ አድርገዋል መባሉን ተከትሎ መንግስት ዜጎቹን ወደ ሀገር ለመመለስ እየሰራ መሆኑን አስታወቀ

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር መለሰ አለም በመንግስት በኩል የተካሄዱ ፖለቲካዊ እና ዲፕሎማሲያዊ ስራዎችን በተመለከተ ለጋዜጠኞች ማብራሪያ ሰጥተዋል።

ኢትዮጵያውን እንደሃገራቸው እንዲኖሩ የሚፈለግበት ሀገር አንዷ ኬንያ መሆኗን አምባሳደር መለሰ አለም በሰጡት መግለጫ አስታውቀዋል። ህገወጥ ስደተኞች በተለያየ መልኩ ወደ ኬንያ እንደሚገቡ አክለዋል።

ሆኖም የትኛውም ሃገር ውስጥ የጉዞ ሰነድ ሳይዙ መገኘት የማይቻል ቢሆንም በኬኒያ የሚያዙ ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች እንግልት ሳይደርስባቸዉ ወደ ሃገራቸው እንዲመለሱ እንደሚደረግ መናገራቸው. ታውቋል

በአሁኑ ሰዓት በኬኒያ እስር ቤት ዉስጥ በረሃብ አድማ ላይ የሚገኙ  21 የሚሆኑት ህገወጥ ስደተኛ  ኢትዮጵያውያን በተመለከተ ለአምባሳደር መለሰ በቀረበላቸው ጥያቄ በተለመደው መልኩ ወደ ሀገር እንዲመለሱ እንደሚደረግ ገልፀዋል።

እንደ ሀገር ስደተኞችን የማስመለስ ስራ በከፍተኛ ሁኔታ እየተሰራ ቢሆንም በተደጋጋሚ በህገወጥ መልኩ ጉዞ የሚያደርጉ ዜጎች መኖታቸው ስራውን አስቸጋሪ ማድረጉም አክለዋል።