Get Mystery Box with random crypto!

ትላንት በቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን በተከሰተው ጉዳይ ቤተክርስቲያን መግለጫ ሰጠች በኢ/ኦ/ | ልዩ መረጃ ®

ትላንት በቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን በተከሰተው ጉዳይ ቤተክርስቲያን መግለጫ ሰጠች

በኢ/ኦ/ተ/ ቤ/ ክ/ የአ/አ ሀገረ ሰብከት በመናገሻ ገነተ ጽጌ ቅ/ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን በመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች አማካኝነት ተፈጽሟል ባለው ሕገ ወጥ ድርጊትን አስመልክቶ ዛሬ መግለጫ ሰጥቷል።

የቅ/ጊዮርጊስ ክብረ በዓል ለማክበር ህዝቡ ከየቤቱ ተሰባስቦ ከጠዋቱ 3:15 ላይ በሰሜን በኩል ከመንግሥት የጸጥታ አካላት 2 ጊዜ በተተኮሰ አስለቃሽ ጭስና በቅጥሩ በተፈጠረው ረብሻ እስከአሁን ባለው መረጃ የ1 ምዕመን "በአስለቃሽ ጭስ ታፍነው" ህይወታቸው ማለፉን ገልጿል።

በተጨማሪም አገልጋይ ካህናት ምእመናንና ምእመናት ከፍተኛ የሆነ አካላዊ እና ሥነ ልቡናዊ ጉዳት ደርሶባቸዋል ከ15 ያላነሱ የሰንበት ትምህርት ቤት አገልጋይ ተማሪዎች በደረሰባቸው ጉዳት ምክንያት ወደ ሆስፒታል መወሰዳቸው ተጠቅሷል፡፡ 

የመንግሥት ኮሚኒኬሽን ቢሮ በዓሉን አስመልክቶ በዕለቱ ያወጣውን መግለጫም ከነበረው እውነታ በእጅጉ የራቀ በሚል የተገለጸ ሲሆን መንግሥት ችግሩን ለማረምና መፍታት ፍላጎት የሌለው መሆኑን ያመለከተ ነው ብለዋል።

መንግሥት የቤ/ክርስቲያንን ክብርና ልዕልና በሚዳፈር መልኩ በተፈጸመው ሕገ ወጥ ተግባር ላይ የተሳተፉና ይህን ድርጊት የፈጸሙና ያስፈጸሙ እንዲፈፀም ያዘዙ የመንግሥት ኃላፊዎችን በ15 ቀናት ጊዜ ውስጥ ለይቶ በሕግ እንዲጠየቁ እንዲያደርግ" ተጠይቋል።

በተለመደው የሀሰት ውንጀላ በዓላችንን በማክበር ላይ እያሉ የመንግሥት የፀጥታ አካላት በፈፀሙት ሕገ ወጥ ተግባር ምክንያት በተፈጠረው ግርግር መነሻት የታሰሩ ምመናንን ያለምንም ቅድመ ሁኔታ እንዲፈቱ ይህ የማይሆን ከሆነ ቤ/ክርስቲያን መብቷን ለማስከበር ወደ ቀጣይ እርምጃዎች የምትገባ ገልጻለች።

ሙሉ መግለጫ ከላይ ተያይዟል

@leyumerga