Get Mystery Box with random crypto!

በቦሌ ክፍለ ከተማ ቡልቡላ አካባቢ በተነሳ የእሳት አደጋ 10 የንግድ ሱቆች ወደሙ ትናንት የካቲት | ልዩ መረጃ ®

በቦሌ ክፍለ ከተማ ቡልቡላ አካባቢ በተነሳ የእሳት አደጋ 10 የንግድ ሱቆች ወደሙ

ትናንት የካቲት 9 ቀን 2015 ሌሊት 7:51 በአዲስ አበባ ቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 12 ልዪ ቦታዉ ቡልቡላ እየባለ በሚጠራዉ አካባቢ በተነሳ የእሳት አደጋ 10 የንግድ ሱቆች መውደማቸውን የእሳትና አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን አስታወቀ።

የእሳት አደጋዉን ለመቆጣጠር 4 የአደጋ መቆጣጠር ተሽከርካሪዎች አንድ አንቡላንስና 27 የአደጋ መቆጣጠር ሰራተኞቾ የተሰማሩ ሲሆን፤ የእሳት አደጋዉ ተስፋፎቶ የከፋ ጉዳት ሳያደርስ በቁጥጥር ሥር መዋሉ ተገልጿል።

በእሳት አደጋዉ በሰዉ ሕይወት ላይ ጉዳት አለማድረሱና በንብረት ላይ የደረሰዉ የጉዳት መጠን ግምትና የአደጋዉ መንስኤ እየተጣራ እንደሚገኝም ተነግሯል።

በአዲስ አበባ የእሳት አደጋዎች እየተደጋገሙ በንብረት ላይም ጉዳት እያደረሱ ይገኛል።

አሁን ያለንበት ወቅት (የአየር ጸባዩ) ለእሳት አደጋ መከሰትና መባባስ ከፍተኛ አስተዋጽኦ የሚያደርግ በመሆኑ ሕብረተሰቡ እሳትና የኤሌክትሪክ ሀይል ምንጮችን በሚጠቀም ጊዜ ከወትሮዉ የተለየ ጥንቃቄ ማድረግ ይኖርበታል ሲል የእሳትና አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን አስታውቋል።

በሌላ በኩል ማናቸዉም አደጋዎች ሲያጋጥሙ አደጋዎች ከመስፋፋታቸዉ በፊት በ939 የነጻ ስልክ መስመር ፈጥኖ ማሳወቅ እንደሚያስፈልግም ኮሚሽኑ አሳስቧል።

@leyumerga