Get Mystery Box with random crypto!

#moe የትምህርት ሚኒስቴር የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ወስደው ውጤታቸው ከግማሽ በታች የሆኑትን | ልዩ መረጃ ®

#moe

የትምህርት ሚኒስቴር የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ወስደው ውጤታቸው ከግማሽ በታች የሆኑትን በቅድመ መደበኛ ዩኒቨርሲቲ ትምህርት ጉድለታቸውን እንዲሞሉ ኮርስ ይወስዳሉ ብሏል።

የትምህርት ሚኒስቴር ዴኤታው ዶ/ር ሳሙኤል ክፍሌ ለኤፍ ቢ ሲ በሰጡት ቃል ፤ " እነኚህ ተማሪዎች ያለባቸውን ጉድለት የሚሞላው የሬሜዲያል ፕሮግራም ይከታተላሉ፤  ያ ማለት በ2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የተማሯቸውን ከሞላ ጎደል እነኚህን ኮርሶችን እንዲማሩ እናደርጋለን " ብለዋል።

" ዋና ዋና ይዘቶች እና መታወቅ ያለባቸውን እስከ አራት ወር ወስደን ከየካቲት 15 እስከ ሰኔ መጫረሻ አካባቢ እነኚህን ትምህርቶችን እንዲማሩና እንዲከልሱ እናደርጋለን " ሲሉ ዶ/ር ሳሙኤል ተናግረዋል።

ዶ/ር ሳሙኤል ክፍሌ ፤ " ተማሪዎች ተከታታይ ምዘና ይመዘኑና ከመቶ ይያዝላቸዋል ፤ እሱን ወደ 30% ቀይረን ከማዕከል ተመሳሳይ ፈተና በግል ተቋማትም ዕጩ ለሆኖ ፍሬሽ ተማሪዎች በመንግስት ተቋማት ላሉ እጩ ፍሬሽ ማን ተማሪዎች ተመሳሳይ ፈተና እንሰጣለን። ይሄንን አድርገን 50 % እና ከዛ በላይ ያመጡትን ወደ መደበኛ ፌሽ ማን ፕሮግራም እንዲገቡ ይደረጋል። መደበኛ ፍሬሽማን ፕሮግራም ተከታትለው የዩኒቨርሲቲ ተማሪ ይሆናሉ " ብለዋል።

ተማሪዎች የሚማሩት በ2ኛ ደረጃ ትምህርት ላይ ያሳዩት ጉድለት ሲሆን ፦

- ቋንቋ፣
-  ሂሳብ፣
- የተፈጥሮ ሳይንስ (ኬሚስትሪ፣ ባዮሎጂ፣ ፊዚክስ) አስፈላጊ ከሆነ ዩኒቨርሲቲዎች ተጨማሪ ይዘት ይጨምሩላዋል ተብሏል።

በማህበራዊ ሳይንስ ደግሞ ፦

- ጂዮግራፊ፣
- ታሪክ፣
- ቋንቋ እና ሂሳብ የሚማሩ ሲሆን ዩኒቨርሲቲዎች እንደፍላጎታቸው ተጨማሪ ይዘት ሊጨምሩላቸው እንደሚችሉ ተገልጿል።

መንግስት ለ100 ሺህ ተማሪዎች የቅድመ ፍሬሽማን ኮርስ እድል የሚያማቻች ሲሆን ለዚህም ቁርጥ ያለ ነጥብ እንደሚያስቀምጥ ይጠበቃል በራሳቸው ወጪ ሸፍነው ኮርስ ለሚወስዱ መንግስት ዝቅተኛ የመቁረጫ ነጥብ እንደሚያስቀምጥ ተነግሯል።

ዶ/ር ሳሙኤል ክፍሌ ፦

" ወጪውን ችሎ ወደ መንግስት ተቋማት የሚሄደው የግል ውሳኔ ስለሆነ አነስተኛውን መቁረጫ ነጥብ ብቻ መንገር ነው የኛ ኃላፊነት።

በመንግስት የሚሄደውን መለየት ስላለብን በዝርዝር ለሴቶች፣ ለወንዶች፣ ለተፈጥሮ ሳይንስ ፣ ለማህበራዊ ሳይንስ ፣ አካል ጉዳት ላለባቸው፣ ከታዳጊ ክልል ለመጡ፣ ለአርብቶ አደር አካባቢዎች በዝርዝር ማስቀመጥ ስላለብን 100 ሺ ለመቀበል ስንት ተማሪ ምንያክል መቁረጫ ነጥብ አድርገን ነው የምናገኘው የሚለው የመንግስት ውሳኔ ነው የሚሆነው።

እኚህ መንግስት ወጪያቸውን ችሎ፣ ዶርም አስገብቶ፣ አብልቶ ፣ አስተኝቶ ሬሚዲያል ፕሮግራም ለሚሰጣቸው ነው።

በራስ ለሚወሰን አነስተኛውን ነው መንገር ያለብን በራስ ውሳኔ የሚለው የግድ ወደ ግል ተቋማት ይሄዳሉ ማለት አይደለም በመንግስት ተቋማትም ሊማሩ ይችላሉ ወጪያቸውን ሸፍነው " ብለዋል።

ይኸው እድል ለአንድ አመት ብቻ እንደሆነ ተገልጿል።

በ2014 ዓ/ም ፈተና ያለፉ #ተማሪዎችን_ምደባ እስከ #እሁድ ለማሳወቅ ፤ የቅድመ ፍሬሽማን ተማሪዎችን መቀበያ ነጥብ እስከ #ሰኞ ይፋ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን ትምህርት ሚኒስቴር ለፋና ብሮድካስት ኮርፖሬት ተናግሯል።

@leyumerga