Get Mystery Box with random crypto!

በኔፓል አውሮፕላን ተከስክሶ የ40 ሰዎች ሕይወት አለፈ 72 ሰዎችን አሳፍሮ ከካትማንዱ ወደ ፖክ | ልዩ መረጃ ®

በኔፓል አውሮፕላን ተከስክሶ የ40 ሰዎች ሕይወት አለፈ

72 ሰዎችን አሳፍሮ ከካትማንዱ ወደ ፖክሃራ ይበር የነበረው የየቲ አየር መንገድ አውሮፕላን የተከሰከሰው በማዕከላዊ ኔፓል አውሮፕላን ማረፊያ አካባቢ በማረፍ ላይ ሳለ ነው ተብሏል፡፡
በዚህም እስካሁን 40 አስከሬን መገኘቱን ነው ሬውተርስ የዘገበው፡፡

የኔፓል ጠቅላይ ሚኒስትር ፑሽፓ ካማል ዳሃል ካቢኔያቸውን ለአስቸኳይ ስብሰባ መጥራታቸው እና የአደጋ ጊዜ ሠራተኞችም በሥፍራው ተገኝተው የነፍስ አድን ሥራ እያከናወኑ መሆኑ ተመልክቷል፡፡

ከተጓዦቹ መካከልም÷ የሕንድ፣ ሩሲያ፣ የደቡብ ኮሪያ እና የአውስትራሊያ ዜጎች እንደሚገኙበት ነው የተጠቆመው፡፡