Get Mystery Box with random crypto!

የዓለም ባንክ የብሔራዊ መታወቂያ ፕሮጀክትን በፋይናንስ ለመደገፍ ግምገማ እያደረገ ነው በሙከራ ደ | ልዩ መረጃ ®

የዓለም ባንክ የብሔራዊ መታወቂያ ፕሮጀክትን በፋይናንስ ለመደገፍ ግምገማ እያደረገ ነው

በሙከራ ደረጃ በአዲስ አበባና በተወሰኑ የክልል ከተሞች የተጀመረውን የብሔራዊ መታወቂያ ፕሮጀክት ወደ ሙሉ ትግበራ ለማስገባት የሚያስችለውን ፋይናንስ ለመደገፍ፣ የዓለም ባንክ ሒደቱን እየገመገመ እንደሚገኝ ታወቀ፡፡

የዓለም ባንክ ለኢትዮጵያ ዜጎች፣ በተለይም ሁሉን አካታችና ተዓማኒ አገልግሎቶችን በሥርዓት ለመስጠት ያስችላል ተብሎ ወደ ሥራ የገባውን የብሔራዊ ዲጂታል መታወቂያ  አገልግሎትን የገንዘብ ድጋፍ ለመልቀቅ፣ የተቋሙን የቦርድ ውሳኔ እየተጠባበቀ እንደሚገኝ ተሰምቷል፡፡

በገንዘብ ሚኒስቴርና በጠቅላይ ሚኒስቴር ጽሕፈት ቤት ሥር በባለቤትነት የሚመራውን ይህንን ፕሮጀክት፣ የዓለም ባንክን ጨምሮ ሌሎች የፋይናንስ ምንጮች እስከ 300 ሚሊዮን ዶላር ፈሰስ ሊያደርጉበት በሚችሉበት ሁኔታ ላይ እየተጤነ እንደሚገኝ የዓለም ባንክ መረጃ ያሳያል