Get Mystery Box with random crypto!

ቻይና ለኢትዮጵያ የዕዳ ስረዛ ለማድረግ ስምምነት ፈረመች ከተሾሙ ገና አንደኛ ወራቸውን ያስቆጠሩት | ልዩ መረጃ ®

ቻይና ለኢትዮጵያ የዕዳ ስረዛ ለማድረግ ስምምነት ፈረመች

ከተሾሙ ገና አንደኛ ወራቸውን ያስቆጠሩት የቻይናው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የመጀመሪያ ይፋዊ የሥራ ጉብኝታቸውን በኢትዮጵያ በማድረግ፣ ከኢትዮጵያ አቻቸው ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ጋር የዕዳ ስረዛን ጨምሮ የተለያዩ የሁለትዮሽ ስምምነቶችን ተፈራረሙ።

ከአቶ ደመቀ መኮንን ጋር ከተወያዩ በኋላም ኢትዮጵያ ከቻይና ከተበደረችው ውስጥ የተወሰነውን ዕዳ ለመሰረዝ የሚያስችል ስምምነት በሁለቱ ሚኒስትሮች መካከል እንደተፈረመ ከውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የተገኘ መረጃ ያመለክታል።

ይሁን እንጂ በዕዳ ስረዛ ስምምነቱ ቻይና ምን ያህል የዕዳ ስረዛ እንደምታደረግ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ቢሮ ያለው ነገር የለም። 

ኢትዮጵያ ባለፉት አስርና ከዚያ በላይ ዓመታት ከቻይና መንግሥት ተበድራ ያልከፈለችው ከ14 ቢሊዮን ዶላር በላይ ዕዳ እንዳለባት የሚታወቅ ሲሆን፣ ይህም ኢትዮጵያ ካለባት አጠቃላይ 27.9 ቢሊዮን ዶላር የውጭ ዕዳ ውስጥ ወደ ግማሽ የሚጠጋ ነው። 
@leyumerga

ethiopianreporter