Get Mystery Box with random crypto!

የሲሚንቶ ምርት ላይ ከተተመነው ዋጋ በላይ በሚሸጡ አከፋፋዮች እና የችርቻሮ ድርጅቶች ላይ እርምጃ | LEYU NEWS

የሲሚንቶ ምርት ላይ ከተተመነው ዋጋ በላይ በሚሸጡ አከፋፋዮች እና የችርቻሮ ድርጅቶች ላይ እርምጃ እንደሚወስድ የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ አስታወቀ

የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ በከተማዋ የሚታዩ አላስፈላጊ የዋጋ ጭማሪዎችን ለመከላከል የተለያዩ ስራዎችን እየሰራ እንደሆነ አስታውቋል፡፡ በዚህ መሰረት ቢሮው በሲሚንቶ ምርት ላይ ከተተመነው ዋጋ  በላይ በሚሸጡ የንግድ ድርጅቶች ላይ ከማሸግ ጀምሮ ሌሎች ህጋዊ እርምጃዎችን እንደሚወስድ አስታውቋል።

ህብረተሰቡ በተለይም ሸማቾች ከተተመነው ዋጋ በላይ ከፍለው መሸመት የሌለባቸው ሲሆን፣ ጉዳዩ ሲያጋጥማቸው በነፃ የስልክ መስመር 8588 በመደወል ጥቆማ አድርሱኝ ሲል ቢሮው አሳውቋል፡፡

የሲሚንቶ መሸጫ ዋጋን በተመለከተ ደርባ በ1067.36 ፣ ዳንጎቴ 1106.85፣ ሀበሻ በ1305 ብር፣ ሙገር በ1016 ብር፣ ኢትዮ 1056.80 ሳንቲም የመሸጫ ዋጋው መሆኑን ቢሮው አስታውቋል።

@Leyu_News
@Leyu_News