Get Mystery Box with random crypto!

በናይሮቢ በታገተው ኢትዮጲያዊ ዙሪያ ለኬኒያ መንግስት ሁለት ጊዜ ደብዳቤ ፅፈናል ሲሉ አምባሳደር መ | LEYU NEWS

በናይሮቢ በታገተው ኢትዮጲያዊ ዙሪያ ለኬኒያ መንግስት ሁለት ጊዜ ደብዳቤ ፅፈናል ሲሉ አምባሳደር መለሰ ተናገሩ

የኬኒያ መንግስት ለደብዳቤው ስለሰጠው ምላሽ ግን አምባሳደሩ የሰጡት ማብራሪያ የለም


በኬኒያ ናይሮቢ ማንነታቸው ባልታወቁና የደንብ ልብስ በለበሱ አምስት ግለሰቦች የታገተው ኢትዮጲያዊ ሳምሶን ተክለሚካኤል ያለበት ሳይታወቅ አንድ ዓመት ከስድስት ወራት አስቆጥሯል። ይህንኑ ተከትሎ የኢትዮጵያ በጠቅላይ ሚኒስቴር ጽሕፈት ቤት፣ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርና በኢትዮጵያ የኬንያ ኤምባሲ ላይ ክስ መመሥረታቸውን የታጋች ባለቤትና ጠበቃቸው ማስታወቃቸው ይታወሳል።

የአቶ ሳምሶን ባለቤት ወ/ሮ ሚለን ሐለፎም፣ አቶ ሳምሶን በኬንያ ፖሊሶች ታፍነው ከተወሰዱ አንድ ዓመት ከስድስት ወራት ቢሆናቸውም፣ የሚመለከታቸው አካላት ሁሉ ስለጉዳዩ ምርመራ እያደረጉ መሆናቸውን ከመግለጽ ባሻገር፣ ያሉበትን ሁኔታ ለማሳወቅ እየተንቀሳቀሱ ያለበት ሁኔታ ቸልተኝነት ታይቶበታል ማለታቸው አይዘነጋም።

ይህንኑ ተከትሎ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ለቀረበበት ቅሬታ ምን ምላሽ አለው በሚል ከጋዜጠኞች ጥያቄ ቀርቦለታል።የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃለአቀባይ አምባሰደር መለስ አለም ጉዳዩ ከተከሰተበት ጊዜ አንስቶ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ክትትል ሲያደርግ መቆየቱንና አሁንም እያደረገ መሆኑን በማንሳት ለኬኒያ መንግስት ሁለት ጊዜ ደብዳቤ ጽፈናል ማለታቸውን ብስራት ሬዲዮ ሰምቷል።የኬኒያ መንግስት ለደብዳቤው ስለ ሰጠው ምላሽ ግን አምባሳደር መለሰ አለም ከመግለፅ ተቆጥበዋል።

በፌዴራል መንግሥትና በኦሮሚያ ክልል በማንኛውም ፍርድ ቤት ጠበቃና የሕግ አማካሪ የሆኑት ጠበቃ ዳባ ጩፋ (ዶ/ር) በበኩላቸው፣ ‹‹ደንበኛዬ በኬንያ በደረሰባቸው የሰብዓዊ መብት ጥሰት ከአንድ ዓመት በላይ ያለበት አይታወቅም፤›› ብለው፣ መታሰራቸው ወይም መሞታቸው አለመነገሩ አሳሳቢ እንደሆነ መግለፃቸውን ብስራት ሬዲዮ መዘገቡ ይታወሳል።
‹‹ጉዳዩ ወደ ፍርድ ቤት የመጣበት ምክንያት እነዚህ የተከሰሱ አካላት ግዴታቸውን ባለመወጣታቸው ነው፡፡ ፍርድ ቤት በሕግ አግባብ ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ ማስገደድ የሚችል በመሆኑ እንደሚያስገድዳቸው እንጠብቃለን፤›› ሲሉም ጠበቃው ተናግረዋል፡፡
ዳጉ ጆርናል

@Leyu_News
@Leyu_News