Get Mystery Box with random crypto!

አብን አብን በአማራ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ኃላፊ ግርማ የሺጥላ ላይ የተፈጸመው ግድያ 'የአገሪቱ | LEYU NEWS

አብን

አብን በአማራ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ኃላፊ ግርማ የሺጥላ ላይ የተፈጸመው ግድያ "የአገሪቱን ሰላምና መረጋጋት አደጋ ላይ የሚጥል የዜሮ ድምር ፖለቲካዊ ሽብር ውጤት" መኾኑን ገልጧል።

አብን ቀደም ሲል በክልሉ አመራሮች ላይ የተፈጸመው የግድያ ወንጀል "ተሸፋፍኖ መቅረቱና ተጠያቂነት አለመስፈኑ"፣ አኹንም የአመራሮች ግድያ "ተባብሶ እንዲቀጥል" ምክንያት መኾኑን አምናለኹ ብሏል።

አብን ግድያው ሳይጣራና የገዳዮች ማንነት ሳይታወቅ፣ ከድርጊቱ "ፖለቲካዊ ትርፍ ለማግኘት ሲባል በአደባባይ የሚደርጉ ፍረጃዎችንና መግለጫዎችን" እንደሚያወግዝም ገልጧል።

የግድያው ፈጻሚዎች ማንነት እንዲጣራና ተጠያቂዎች ለፍርድ እንዲቀርቡ አብን ጨምሮ ጠይቋል።

@Leyu_News
@Leyu_News