Get Mystery Box with random crypto!

❥:::::::እባክሽን ታጋሽ ሁኚ:::::::::❥ · #በጣም የሚዋደዱ በኢማናቸው ጠንካሮች የሆኑ ባ | ለሙስሊሟ እህቴ

❥:::::::እባክሽን ታጋሽ ሁኚ:::::::::❥
·
#በጣም የሚዋደዱ በኢማናቸው ጠንካሮች የሆኑ ባለትዳሮች ነበሩ። አንድ ቀን ሚስት ከባሏ እና ከቤተሰቦቿ ጋር የማምሸት ፕሮግራም ትይዝና ለቧሏ ቀድማ ትነግረዋለች። ባል ግን በዛ ቀን ከቀጠሮው ሰአት አሳልፎ እንደውም ያመሻል።
·
ሚስት ስትደውል ስልኩ አይሰራም። በጣም ትናደዳለች። ባልም አምሽቶና ደክሞት ቤት ሲገባ ሚስቱም «ከቤተሰቦቼ መቅረቴ ሲገርመኝ እንዲህ አምሽተክ ትመጣለክ? ለምን አታድርም ነበር ...... ?» በጣም ጮክ ብላ ትናገረዋለች ባል የሆነውን ሊያስረዳት ቢሞክርም ልትሰማው አልፈለገችም በጣም ደክሞት ስለነበር ትቷት ወደ መኝታው ይሄዳል።
·
በሁለተኛ ቀን ድጋሚ ያመሻል ሚስት ስትደውል ስልኩን ያነሳችው ሴት ነበረች «ሄሎ» ስትላት ስልኳን ተናዳ ትዘጋዋለች። ባል ሲገባ እሳት ለብሳ እሳት ጎርሳ ትጠብቀዋለች። ባሏም እንደገባ እንዲህ አለችዉ።
·
ሚስት፦ «እኔ ምንክ ነኝ ላንተ ?»
·
ባል፦ «ውድ ሚስቴ ነሻ።»
·
ሚስት፦ «ያቺስ»
·
ባል፦ «ከወደሁላው ዘወር ዘወር ይልና የቷ ?
·
ሚስት፦ «ስልኩን ያነሳችው ወይዘሮ»
·
ባል፦ «ስልኩን ለማውጣት እጁን ወደ ኪሱ ሲያስገባ ስልክ የለም። «ማሬ ስልኬ የለም፣» ይደነግጥና ማፈላለግ ይጀምራል።»
·
ሚስትም ሊዋሻት የፈለገ ስለመሰላት አላመነችው በቃ እንዲፈታት ትነግረዋለች። ባል ሊያረጋጋት ቢሞክርም አልቻለም። ባልም እሺ ይንጋና ነገ ወደ ቤተሰቦችሽ ትሄጃለሽ ብሎ ይለምናታል። በዚህ መልኩም እሱ መኝታ ቤት እሷ ደሞ የሳሎኑ ሶፋ ላይ ተለያይተዉ ተኙ።
·
በጠዋት የቤታቸው በር ይንኳኳል ሚስትም ከተኛችበት ሶፋ ላይ ነቅታ በሩን ስትከፍት አንድ አርጀት ያሉ ሴትዮ ከወጣት ሴት ልጃቸው ጋር ይመጡና ባሏ እንዳለ ይጠይቋታል። እሷም ትጠራዋለች ሴትዮዋም ስልኩን እርሳቸው ጋር እረስቶት እንደነበረ ነገረው ይሰጡትና በጣም ሲመርቁት ታያለች።
·
ሚስት፦ «ለምንድን ነው ብላ ስትጠይቅ ?»
·
የልጁ እናት፦ «ባልሽ በጣም ጥሩ ሰው ነው። ከቀኖች በፊት ለወንዱ ልጄ ደም ለግሶ የልጄን ሂወት ታደገልኝ።» የልጁ እናትም አስከትለዉ
«ትላንት ደግሞ ልጄን ሊጠይቅ መጥቶ ሳለቅስ አየኝ ለምን እንዳለቀስኩ ጠይቆኝ ለልጄ ከሆስፒታል የታዘዘለትን መድሀኒት መግዣ እንዳልነበረኝ ስነግረው በየ ሱቁ ሲፈልግ አምሽቶ ገዝቶ አመጣልኝ። እናም ሆስፒታል ዉስጥ ስልኩን እረስቶት ሄደ ስትደውይ ልጄ ነበረች ያነሳችው።»
·
ትላታለች ሚስትም በባሏ ታጋሽነትና ቸርነት ተገርማ ይቅርታ ትጠይቀዋለች።

ውድ እህቴ ከታሪኩ የምትማሪው ለነገሮች ኡዙር መስጠት እንዳለብሽ ነው። ባልሽ ላንቺ ታመኝ መሆኑን ልብሽን አሳምኝው። በትንሽ ነገር የአላህን ስጦታና የቤትሽን ጣፋጭ ደስታ ምድራዊ ጀነትሽን በቀላሉ አታበላሺዉ። እሱ ያንቺ ደስታ ነው የሚያስደስተው ግን የተቸገሩትንም መርዳት እንዳለበት አትርሺ።
·
ሁል ጊዜ ቤትሽን አስታዉሺ ላንቺ ብቻ ሳይሆን ለመላዉ ቤተሰብሽ ለአላህም ብለሽ።

:::::::ቴሌግራማችን::::::::

@lemuslimuaehte