Get Mystery Box with random crypto!

ረሱል ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም እንዲ ይላሉ፦ ➧ሴቶች ሆይ ሰደቃ አብዝታችሁ ስጡ! አብዛኞቹ የጀሀነ | ለሙስሊሟ እህቴ

ረሱል ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም እንዲ ይላሉ፦

➧ሴቶች ሆይ ሰደቃ አብዝታችሁ ስጡ! አብዛኞቹ የጀሀነም እሳት ነዋሪዎች እናንተ ሁናችሁ አይቻችኋላሁና።

➧ጀሀነም ውስጥ የበዛንበት ምክንያቱ ምንድን ነው አንቱ የአላህ መልዕክተኛ ብለው ጠየቁ፡ ከዛም ረሱል"እርግማን ስለምታበዙና የባላችሁን ውለታ ስለምትክዱ ብለው መለሱላቸው።


➻ሴቶችን ጀሀነም ውስጥ እንዲበዙ ያደረጋቸው ሁለት ምክንያቶች ፡

①እርግማን ስለሚያበዙ

② ከባላቸው ጋ ለአመታት የደስታን ህይወት አሳልፈው ልክ አንድ ቀን የሆነ ነገር ሳያሟላላት ሲቀር "አንተ ምን አድርገህልኝ ታውቃለህ ምናምን ብለው ያን ሁሉ በደስታ ያሳለፉትን ያን ሁሉ ውሌታውን በአንዲት ጉድለት ስለሚክዱ"እንዲሁም የባላቸውን ሀቅ ስለማያሟሉ በሚልም ተፈስሯል።

➧እንዳጠቃላይ ከነዚህና መሰል ተግባራቶች ራሳችሁን በማራቅ ነፍሳችሁን ከጀሀነም እሳት በአላህ ፈቃድ ታደጉ።

➧በዋናነት ጀሀነም ውስጥ የሴትች መብዛት ሰበብ እነዚህ ሁለት ነገሮች መሆናቸውን ረሱል ተናግረዋል።

አላህ ሁላችንንም ከጀሀነም እሳት ይጠብቀን አሚን።

ምንጭ ሶሂሁል ቡኻሪ (304)

𝒽𝓊𝓈ℯ𝓃 𝒶𝒽𝓂ℯ𝒹

https://t.me/joinchat/AAAAAFVzuS5gUe0MqdnPQQ