Get Mystery Box with random crypto!

ሰው ስለምን ሰው-ነቱን ረሳንንንንንን አንዳንድ የህዝብ አገልጋይ የሆኑ ስራ ቤት ወገኖች | ኦፍቲ ቲዩብ-ልበ ጥሞና

ሰው ስለምን ሰው-ነቱን ረሳንንንንንን

አንዳንድ የህዝብ አገልጋይ የሆኑ ስራ ቤት ወገኖች በርግጥ ሰው-ነታቸውን ያከብሩታልን?

ሰው-ነት እኮ ህሊና-ቢስነት አይደለም።
ሰውነት ውስጥ ምን ይሉኝ አለበት።
እንዲህ በተውሸለሸለ አፈጻጸም ተሰርቶና ምንዳን ተቀብሎ ቤተሰብ ማስተዳደር በእውነት ለኔ ውርደትና ቅሌት ነው።

የደመ-ወዜን ዋጋ እንጅ ተጨማሪ የሌሎችን የላብ ለጠፈ-ፍራንክ ከምንዳዬ ጋር ቀላቅዬ ወደ ቤቴ ያስገባሁ ዕለት እኔ ሞቻለሁ። ሰውም አልሰኝ። ልብሰ-ጅቡን ክልውሰ-ሰው መሳይ በሸንጎ ሬሳ እንጅ።

ሌሊቱን አልተኛሁም። ስራ መስራት ነበረብኝ። ዕቅዴም በሸለብታ ተከታታይ ሁለት ቀናትን በጠንካራ ስራ ማሳለፍ ነበር።
ግና...በየትኛው ቅያስ ሰዓታቴን ለምግባሬ ልጠቀምበት? አንዳንዴ ቅያሶች ሁሉ ምርጫ ቢስና ዝግ ይሆንብኛል።

በእውነት ከማማረር ማምረርን በኑረተ ገጼ ትርጉም በሚቸር መልኩ ማንፀባረቅ እንድችል ሰው-ነትን ያልዘነጉ አመራሮች በየዘርፉ ኢትዮጵያ ትፈልጋለች። እኔም።