Get Mystery Box with random crypto!

የችሎት ውሎ !! የአስገድዶ መድፈር ወንጀል የፈጸመው ግለሰብ በእስር ተቀጣ ተከሳሽ ከድር መሃመድ | አለ_ህግ🔵Ale_Hig

የችሎት ውሎ !!

የአስገድዶ መድፈር ወንጀል የፈጸመው ግለሰብ በእስር ተቀጣ ተከሳሽ ከድር መሃመድ በቤተሰቦቹ ቤት በቤት ሰራተኝነት ታገለግል የነበረችው ዙለይካ ጀማል ላይ በሃምሌ ወር 2ዐ13 ዓ.ም በፈጸመው የአስገድዶ መድፈር እና ከድርጊቱ በኋላ የተፈጸመውን ጽንስ ለማስወረድ ባደረገው ሙከራ በፈጸመው የጽንስ ማስወረድ ሙከራ ወንጀል በሁለተኛ ክስነት የምስራቅ ስልጢ ወረዳ ዐቃቤ ህግ ክስ አቅርቦበታል።

ጉዳዩን ሲመለከት የቆየው የወረዳው ፍርድ ቤት ተከሳሽን ነጻ ነው በማለት በሁለተኛው ክስ በ1ዓመት ከ3ወር ቀላል እስራት ወስኖበታል።

በውሳኔው ቅሬታ የተሰማው ዐ/ህግ ለስልጤ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት

ይግባኝ አቅርቧል።ከፍተኛ ፍርድ ቤቱም የስር ፍርድ ቤትን ውሳኔ

በማሻሻል በ1ዓመት ከ6ወር እስራት ወስኗል።

በዚህ ውሳኔ ቅር የተሰኘው የዞኑ ዐቃቤ ህግ ጉዳዩን በይግባኝ ለደቡብ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት አቅርቦ ክርክር በማድረግ ከፍተኛ ፍርድ ቤቱ በቅጣት አጣጣል ላይ የፈጸመውን ስህተት በማረም ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ በቀን 19/12/2014 በዋለው ችሎት ተከሳስሽን በ 8ዓመት ከ5ወር ጽኑ እስራት እንዲቀጣ ወስኗል።

መረጃው የስልጤ ዞን ፍትህ መምሪያ – Siltie Zone Justice Department
https://t.me/lawsocieties