Get Mystery Box with random crypto!

' በአስቸኳይ መስጂዶችን ማፍረስ አቁሙ ፤ የፈረሱትንም በፍጥነት መልሳችሁ አሰሩ ፤ ሕዝበ ሙስሊሙን | ላኑፈሪቁ ኢላ የዉመል ቂያማ የዳዕዋ ቻናል

" በአስቸኳይ መስጂዶችን ማፍረስ አቁሙ ፤ የፈረሱትንም በፍጥነት መልሳችሁ አሰሩ ፤ ሕዝበ ሙስሊሙንም በይፋ ይቅርታ ጠይቁ " - የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት

የኢትዮጵያ የእስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ  ምክር ቤት በአዲሱ "በሸገር ከተማ " መስጂዶች እየፈረሱ መሆኑን በመግለጽ ይህ ድርጊት በአስቸኳይ እንዲቆም አሳሰበ።

ምክር ቤቱ  ለኦሮምያው ክልላዊ መንግስት  ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ በፃፈው ደብዳቤ  ነው ይህንን ማሳሰቢያ ያስተላለፈው።

ጠቅላይ ምክር ቤቱ በደብዳቤው ፤ የኦሮሚያ  ብሔራዊ  ክልላዊ መንግስት እየፈረሱ ያሉ መስጂዶች በአስቸኳይ እንዲያስቆም ብሏል።

ከዚህ ባለፈም ፤ የፈረሱ መስጂዶች በሸገር ከተማ አስተዳደር በፍጥነት እንዲሰሩና ሕዝበ ሙስሊሙን አስተዳደሩ በይፋ  ይቅርታ እንዲጠይቅ አሳስቧል።

የኦሮሚያ እስልምና ጉዳዮች  ከፍተኛ ምክር ፥ ለጠቅላይ ምክር ቤቱ በተፃፈው ደብዳቤ :-
1. በሸገር ከተማ ኮዬ ፈጬ ክፍለ ከተማ ዉንዴሳ ወረዳ ልዩ ስፍራ ቀርሳ በቀን 14/07/15
2. በሸገር ከተማ ሰበታ ክፍለ ከተማ መጉላ ቶውፊቅ መስጂድ 19/08/15
3. በሸገር ከተማ መልካ ኖኖ ክፍለ ከተማ ወረዳ ልዩ ስሙ አን ኢ ሳይት ሰላም መስጂድ በቀን 24/08/25
4. በሸገር ከተማ ቡራዩ ክፍለ ከተማ ልዩ ስሙ አሸዋ ሜዳ በቀን 25/08/15 መፍረሳቸውና ጉዳዩ ከአቅሙ በላይ መሆኑን አሳውቋል።