Get Mystery Box with random crypto!

ፍቅር ቤቱን ይስራ ፍቅር ቤቱን ይስራ እጅጉን አስፍቶ፣ መኖሪያ ይሆናል ለልባሞች ደልቶ፣ | ኩን ሰለፍያ አለልጀዳ አሰለፍይ መነሀጅ ኦፊሲላዊ ቻናል

ፍቅር ቤቱን ይስራ




ፍቅር ቤቱን ይስራ እጅጉን አስፍቶ፣
መኖሪያ ይሆናል ለልባሞች ደልቶ፣

በኢስላም ተጋብቶ ፍቅሩን ያጣጣመ፣
የአላህ ባሪያ ነው ሀላሉን ያራቀ።

ፍቅር ፍቅር ሆኖ ከልብ ስትኖረው፣
የአላህን ፀጋ ወደህ ስትይዘው፣
ፍቅር ቤቱን ይስራ ለዱኒያም ለአሄራው፣
በሰለፎች መንገድ ባልተበራረዘው።


አደምና ሃዋ ልክ እንደተባዙት፣
አንቢያ ሙርሰልም ልክ አንደተጋቡት፣
ሀቢቢና ሙሀመድ
ሶለዋቱ ረቢ ወሰላሙ አለይህ፣
ልክ እንደኖሩበት፣
አንተም ኖረህ ኖረህ ፍቅር ቤቱን ይስራ፣
የአዱኒ አታድርገው ይርዘም ለአሄራ፣
በአዱኒያ ፍቅርን ጀነትን በአሄራ፣
እንድታገኘው ሁን ወንድሜዋ አደራ፣

በሀላል ከሳስበህ ሚዛን እንድሞላ፣
ፍትሀዊ ሆነህ ተጓዝ ወደ አሄራ፣
ትዳርህ ሰምሮልህ በተውሂድ ባንድራ፣
በሱና አሸብርቆ ደምቆል ባዱኒያ፣
በአሄራም ጀነትን ተመኝተህ ቀና፣
ይቺን ምድር ሂዳት በእወነት ጎዳና።


አቡ ተቅይ ቃዒድ
https://t.me/LoveOfMarriage