Get Mystery Box with random crypto!

የፍረሽን ሁኔታ አይቶ መሳቅ የተለመደ እና ሁላችንም ተስቆበት ያለፍንበት ቢሆንም ስለ ዘንድሮ አ | MENELIK UNIVERSITY news

የፍረሽን ሁኔታ አይቶ መሳቅ የተለመደ እና ሁላችንም ተስቆበት ያለፍንበት ቢሆንም

ስለ ዘንድሮ አስቂኝ ክስተቶች አንዳንድ ነገር ልበላችሁ

1
ጠዋት ወደ መመገቢያ ካፌ ከቤተክርስቲያን የሚመጡ ተማሪዎች ነጠላ ለብሶ ወደ ካፌው መግባት አይቻልም። እናም ነጠላ የለበሱ ተማሪዎች ካፌው አካባቢ ነጠላቸውን እያስቀመጡ ሲገቡ አንድ ልጅ እያያቸው ኖሯል። እና የካፌው አሰራር ከላይ የቤተክርስቲያን ጉልላት ያለው ይመስል ነበርና ካፌው ቤተክርስቲያን መስሎት ዞሮ ያማተበው ነገር ሳቅ ያስይዛል።

2
እዚያው ካፌ ውስጥ የሚታይ ጉድ ነው። ይህ ደግሞ በተደጋጋሚ በየአመቱ የሚስተዋልም ነው።
ካፌ ውስጥ ገብቶ ማጨብጨብ

ይህ ክስተት በላውንጆችም ላይ ይስተዋላል።
"አስተናጋጅ" ብሎ እየቀወጡ ማጨብጨብ።

ታዲያ ይህችን ካልንም አይቀር

3 ዶርም አካባቢ
የወንዶች ዶርም አካባቢ የተከሰተ አስቂኝ ክስተት ነው

አንድ ልጅ ከፎቅ ላይ በፌስታል የተቋጠረ ቆሻሻ ይዞ ይወርዳል።በበሩ ላይ አንድ ልጅ ያገኝና "ቆሻሻ መድፊያው የት ነው?" ሲል ይጠይቃል። ያ ሰውም
"ኬት ነው ያመጣኸው"
"ከዶርም"
"የት ነው ዶርምህ"
"1ኛ ፎቅ"
"በቃ ሂድና እዛው በር ላይ አስቀምጠው"
ቆሻሻውን ይዞ ወደ ዶርም
Dbu university
4
ይቀጥላል