Get Mystery Box with random crypto!

​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​─​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​─━━─━━ ⊱✿⊰ ━━ | ፍቅር እና የኛ ሰፈር ቀልዶች 🎼🎧Ofichal kumis

​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​─​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​─━━─━━ ⊱✿⊰ ━━━━━━──


እስቲ ላፍቅር ደሞ....

ሰው አጥር ወጥቼ - ፅጌረዳ ልቅጠፍ፥
አበባዬን ይዤ - እግሯ ሥር ልነጠፍ፤
ጨረቃ ላይ ላፍጥጥ - ከዋክብትን ልቁጠር፥
የቦይ ውኃ ልምታ - በለቀምኩት ጠጠር፤
በመስኮት ላማትር - በሚወርደው ዝናብ፥
ቀን ተሌት ልተክዝ - በፈጠርኩት ምናብ።…

እስቲ ደሞ ላፍቅር…
እሷው ፖለቲካ - እሷው ሰበር ዜና፥
እሷው ባለንዋይ - እሷው ባለዝና፥
እሷው የ’ምነቴ ቄስ - እሷው ቅድስና፥
ዓለም በቃኝ ብዬ - በሷው ወሬ ልጽና።
ከፈገገች ልሣቅ - ካለቀሰች ልሙት፥
እኔ አለኹ ለቀልዷ - ደደቦች ባይሰሙት።…

እስቲ ላፍቅር ደሞ…
መንገድ ስሟን ልጥራ - አበደ ይበሉ፥
እሷ ውስጥ እንዳለኹ - የማያውቁ ኹሉ፤
ጥዑም ዜማ ይኹን - የምትጨቀጭቀኝ፥
የሰለቸኝ ኹሉ - ባ’ንድ አዳር ይናፍቀኝ፤
እንዴትም ትስደበኝ - ስሜን ታጥፋው አኹን፥
ብቻ ስሜን ትጥራ - ብቻ ካፏ ይኹን።…

እስቲ ላፍቅር ደሞ…
ዘፈን ትርጉም ይስጠኝ - ደሞ ላንጎራጉር፥
ስለመቃ አንገት - ስለሀር ጸጉር፤
ላንዲት እንስት ልውደቅ - ሎሌነቴን ልግመድ፥
የያዝኩትን ልጣል - ዐዲስ ጌታ ልልመድ።

እስቲ ላፍቅር ደሞ....


━━━━━━✦✗✦━━━━━━━
ምርጫዎ ስለሆነ እናመሰግናለን



➳➳➳ ሼር ያድርጉ!! ➢➢➢

Join us  @kumis4274
@kumis4274