Get Mystery Box with random crypto!

ቀሲስ ስንታየሁ የኔአባት

የቴሌግራም ቻናል አርማ ksintyehu — ቀሲስ ስንታየሁ የኔአባት
የቴሌግራም ቻናል አርማ ksintyehu — ቀሲስ ስንታየሁ የኔአባት
የሰርጥ አድራሻ: @ksintyehu
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 616
የሰርጥ መግለጫ

ስለ ክርስትና ህይዎታችን የምንወያይበት፣ የምንመካከርበት እና የምንጠያይቅበት አዲሰ የቴሌግራም ገፅ ነው!
ለማግኘት @KSintayehu
እንማማር ዘንድ በፌስቡክም አግኙን https://m.facebook.com/ቀሲስ-ስንታየሁ-የኔአባት-765068226962266/?ref=notif_textonly

Ratings & Reviews

3.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-08-03 11:00:00 ሞት

ብዙ ሰዎች ሞትን ከመጥላታቸውም በላይ ለተስፋ መቁረጥ ምክንያት አድርገው ያቀርቡታል ሰዎች ሀዘን ሲገጥማቸው በአብዛኛው ጥቋቁር ልብሶችን በመልበስ ሞትን በእንባና በልቅሶ ይቀበሉታል ይሁን እንጂ የሞት ነገር እንኳ ለበጎ ሊሆን ይችላል፡፡
ሞት ሰዎች ከፍተኛውን ደረጃ በእርሱ በኩል የሚገኙበትና ወደ ተሻለ ሕየወት የሚሸጋገሩበት ነው ፡፡በትንሣኤ ይዘን የምንነሳው ሰማያዊና መንፈሳዊ አካል ነው በዚያን ጊዜ በክብር የምንነሳው የእግዚአብሔርን መንግሥት የሚወርስ ሰማያዊ አካል ይዘን የምንወርደው ይህንን የተፈጥሮ አካላችንን ነው ታዲያ ሞት ለበጎ እንዲደረግ አልተመለከታችሁምን?
እስኪ ቅዱስ እንጦንስንና የአባቱን የአሟሟት ታሪክ እንመልከት ፡፡ ለአባ እንጦንስ አሟሟት በዓለማዊው ሕይወት በሟችነትና በከንቱነት ላይ ጥልቅ ትምህርት
እንዲያገኝ ረድቶታል ፡፡ በዚያን ጊዜ ወጣቱ እንጦንስ
የሟች አባቱን አስከሬን ተመልክቶ እንዲህ ነበር "ታላቅነትህና ጉልበትህ ወዴት ደረሰ ?አንተ ይህን ዓለም ያለ ፈቃድህ እንድትለቀው ተገደሃል እኔ ግን እኔን ያለ ፈቃዴ ከመውሰዳቸው በፊት በገዛ ፈቃዴ
ይሄንን ዓለም ትቼው እሄዳለሁ " አለ ይህ የቅዱስ እንጦንስ የምንኩስና ሕይወት የመጀመሪያው ምዕራፍ ነበር፡፡
ሞት መኖርነ ማሳብ ሁሉጊዜ ከትዕዛዛቱ እና ከቃሉ እንዳንወጣ ያደርገናል ።
ሞት መኖርን ስናስብ መልካም ነገር ማድረግን እናስባለን ።
ስለዚህ ሞት በጎ ነገር ማሰቢያም ነው።
135 viewsቀሲስ ስንታየሁ የኔአባት, 08:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-31 07:30:58 ጃንደረባ ማለት በሌላ የአገላለፁ ትርጉም ድንግል ማለት ነው።ይህ ማለት ህገ ጋብቻን ንቀው ወይም ትተው ብቻቸውን በድንግልና ህይወት ለመኖር የወሰኑ የእግዚአብሔር ሰዎች ናቸው። ጃንደረባነት በ3 አይነት መንገድ ሊገለፁ ይችላል።1ኛ/ ከእናታቸው መሀፀን ጀምሮ አካላዊ የስሜት ምልክት ሳይኖራቸው ጀንደረባ ሆነው የተወለዱ አሉ።2ኛ ደግሞ በመንፈሳዊ ተጋድሎ ወይም በሌላ ምክንያት በሰው አካላቸው ተሰልቦ ጃንደረባ የሆኑ አሉ። 3 ኛ/ ስለ መንፈሳዊ የእግዚአብሔር መንግስት ብለው (ስለ መንግስተ ሰማያት ብለው) ራሳቸውን ጀንደረባ ያደረጉ  አሉ። ስለዚህ ጉዳይ ጌታችን እየሱስ ክርስቶስ በፈሪሳዊያን ዘንድ ስለ ጋብቻ በቀረበለት ጥያቄ መነሻነት ማግባትም ሆነ አለማግባት ወይም ጃንደረባ ሆኖ መኖር ከእግዚአብሔር ዘንድ ለተሰጣቸው መሆኑን በሰጣቸው መልስ የጃንደረባን ምስጢር ነግሮናል።(ማቴ 19፥10-11) ስለዚህ ጠያቂያችን ማንኛውም ሰው ከእግዚአብሔር ዘንድ የተሰጠው ሀብት ፀጋ ምን እንደሆነ ለይቶ በማወቅና በመረዳት በፀጋው መኖር አለበት። በጋብቻ ተመስርቶ ትውልድ ማትረፍም ከእግዚአብሔር ፍቃድ የተነሳ እንጂ ሰው በራሱ አቅም ወይም ችሎታ ያመጣው ህልውና አይደለም።በሌላም በኩል አለምን ንቀው ሁሉን ትተው በዱር በገዳም እንደሚኖሩ ባህታውያን ወይም መናንያን ሳያገቡና ዘር ሳይተኩ በጃንደረባነት የሚኖሩ ፍጹማን የእግዚአብሔር ሰዎች ደግሞ የተሰጣቸው ፀጋ ዘመናቸውን ሁሉ እግዚአብሔርን ማገልገልን በነፍስም በሥጋም ለእግዚአብሔር በመገዛት ለማገልገል ከልጅና ከትዳር የበለጠ ስም ወይም ክብር ከእግዚአብሔር ዘንድ ያገኛሉ።ነብየ እግዚአብሔር ኢሳያስ ጃንደረባን “እነሆ እኔ ደረቅ ዛፍ ነኝ አይበል፤ እግዚአብሔር ሰንበቴን ስለሚጠብቁ ደስ የሚያስኘኝንም ነገር ስለሚመርጡ ቃል ኪዳኔንም ስለሚይዙ ጃንደረባዎች እንዲህ ይላልና ፤ በቤቴ በቅጥሬ ውስጥ ከወንዶችና ከሴቶች ልጆች ይልቅ የሚበልጥ መታሰቢያና ስም እሰጣቸዋለሁ የማይጠፋም የዘላለም ስም ሰጥቻቸዋለሁ” በማለት ለጀንዳረባዎች በጋብቻና በትዳር ከሚገኘው ትውልድ በላይ በእግዚአብሔር ዘንድ ለዘላለም የማይጠፋ ስም እንደሚሰጣቸው ቃል ኪዳን ገብቶላቸዋል (ኢሳ 56፥3-5
268 viewsቀሲስ ስንታየሁ የኔአባት, 04:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-31 07:15:54 ነገር አለ፤እርሱም፡-ሕዝብና አሕዛብ አንድ ሆነው ጌታን ለመ ከራ
መስቀል አሳልፈው እንደ ሰጡት፥አሕዛብና መናፍቃንም አንድ
ሆነው ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያንን ላይጥሉአት
እየታገሉአት፥ላትሞት እየገደሉአት መሆናቸውን ነው።እኛም
ለወዳጃችን ለቅዱስ ገብርኤል እንነግረዋለን።“የእግዚአብሔር
መልአክ በሚፈሩት ሰዎች ዙሪያ ይሰፍራል፥ያድ
ናቸውማል፤”ይላል።መዝ፡ ፴፫፥፯። -መናፍቃኑ፡-“ታቦት በቅዱሳን
ስም ለምን ይሰየማል? እግዚአብሔር ለሙሴ የሰጠው አንድ
ታቦት ነው፥የተቀረው ከየት መጣ?”የሚል ጅል ጥያቄ
ይጠይቃሉ።ይህንንም የሚሉት፡-የሚነገራ ቸውን መልስ
ላለመስማት ጆሮአቸውን ደፍነው፥ላለመቀበልም ልቡናቸውን
አደንድነው ነው። ነገር ግን ይኸንን ጥያቄ
ለመጠየቅ፥በመጀመሪያ፡-ሙሴ የተቀበለውን ታቦት
መቀበል፥የእግዚአብ ሔርንም ቅዱሳን መቀበል
ይጠበቅባቸዋል።ተቀብለውም ከሆነ ይንገሩን።ምክንያቱም፡-የጌታ
ቃል ፡-“እናንተን የሚቀበል እኔን ይቀበላል፥እኔንም የሚቀበል
የላከኝን (አብን መንፈስ ቅዱስን) ይቀበ ላል።ነቢይን በነቢይ ስም
የሚቀበል የነቢይን ዋጋ ይወስዳል፥ጻድቅንም በጻድቅ ስም
የሚቀበል የጻድቁን ዋጋ ይወስዳል።ማንም ከእነዚህ ከታናናሾቹ
ለአንዱ በደቀ መዝሙር ስም ቀዝቃዛ ጽዋ ውኃ
የሚያጠጣ፥እውነት እላችኋለሁ፥ዋጋው
አይጠፋበትም፤”ይላል።ማቴ፡፲፥፵።ጥያቄውን በጥ ያቄ ስንመለስ
ደግሞ፡-ሙሴም፥ ነቢያትም፥ሐዋርያትም ጽፈውልን የሄዱት
መጻሕፍት አንድ አንድ ቅጽ ብቻ ናቸው፥ታድያ ዛሬ ዓለምን
ያጥለቀለቁት ቅዱሳት መጻሕፍት ከየት መጡ? ብለን እንጠ
ይቃለን። -“ታቦት በቅዱሳን ስም ለምን ይሰየማል?” የሚለውን
ጥያቄ ለመመለስ ብዙ ድካም የሚጠይቅ አይደለም።መልሱ
አጭር ነው፥እርሱም ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ያስተማረው ት/
ት ነው። “ኢተ አምሩኑ ከመ ታቦቱ ለእግዚአብሔር አንትሙ
ወመንፈሰ እግዚአብሔር ላዕሌክሙ? ወዘሰ አማ ሰነ ቤተ
እግዚአብሔር ሎቱኒ ያማስኖ እግዚአብሔር፥ወቤቱሰ
ለእግዚአብሔር አንትሙ ውእቱ፥ ወቅዱሳን አንትሙ፥ወኢታርኵሱ
ቤቶ ለእግዚአብሔር።እናንተ የእግዚአብሔር ታቦት(ማደሪያ፥
ቤት) እንደ ኾናችሁ አታውቁምን? መንፈስ ቅዱስ አድሮባችሁ
እንዳለ አታውቁምን? የእግዚአ ብሔር ማደሪያ የሆነ ሰውነቱን
በኃጢአት ያሳደፈውን ግን እግዚአብሔር ፈርዶ ያጠፋዋል፥እናን
ተስ የእግዚአብሔር ታቦት (ማደሪያ) ናችሁ፥ንጹሐን ክቡራን
ናችሁ፤”ይላል።፩ኛ፡ቆሮ፡፫፥፲፮።ስለ ዚህ፡-እንደ ሐዋርያው አማናዊ
ት/ት ቅዱሳን በአጸደ ሥጋም በአጸደ ነፍስም የእግዚአብሔር ታቦ
ታት በመሆናቸው፡-ታቦት በስማቸውይሠየማል። -“ድከም ያለው
አንድ እንጨት ያስራል፤”እንዲሉ፥የሚታደስ ነገር በሌለባት ቤተ
ክርስቲያን፡-“እና ድሳለን፤”ብለው መከራቸውን የሚያዩ የውስጥ
መናፍቃን ደግሞ፡-“የአዲስ ኪዳን ታቦት ኢየሱስ ነው፤” እያሉ
ለማደናገር እየሞከሩ ነው።“ለመሆኑ በቤተ ክርስቲያን የኢየሱስ
ክርስቶስ ያልሆነ ታቦት አለ ወይ?” ቢባሉ፥ካልለገሙ በስተቀር
መልሱን ያውቁታል።ቅዱስ ጳውሎስ እኮ፡-“እናንተ የእግዚአብሔር
ታቦት ናችሁ፤” ብሎ ጨርሶታል።ኢየሱስ ክርስቶስ ደግሞ
እግዚአብሔር ነው። ዮሐ፡፩፥፩፣የሐዋ፡፳፥፳፰።ስለሆነም፡-
በቅዱሳን ስም የተሰየሙት ታቦታት ሁሉ የኢየሱስ ክርስቶስ
ናቸው።የተቀረጸባቸው፡-“አልፋ ወዖ፤” የሚለውም የኢየሱስ
ክርስቶስ ኅቡዕ ስም ነው።የኢየሱስ ክርስቶስ ስም ደግሞ፡-
በተዋህዶ የከበረ አምላክ ስም በመሆኑ፥ከስም ሁሉ በላይ የሆነ
ስም ነው፥ ኃይልና ሥልጣንም አለው።ቅዱሳን ሐዋርያት አያሌ
ተአምራትን በስሙ ያደረጉት ለዚህ ነው፥ ዛሬም በስሙ
ተአምራት ይደረጋል፥እየተደረገም ነው።“ኢየሱስ ክርስቶስ
ትናንትና ዛሬ እስከ ዘለዓ ለምም ያው ነው።”ዕብ፡፲፫፥
፰።ከስሙም ጋር፡-“ከመ ለስሙ ለኢየሱስ ክርስቶስ ይስግድ ኵሉ
ብርክ ዘበሰማያት ወዘበምድር፤ ሁሉ(መላእክትም የሰው
ልጆችም) ለኢየሱስ ክርስቶስ ስም ይሰ ግዱ ዘንድ፤”የሚለው
ይቀረጽበታል።በመጨረሻም በዚያ ታቦት የተሠየመው ጻድቅ
ወይም ቅዱስ ስም ይቀረጻል።ምክንያቱም እግዚአብሔር ቅዱሱን
ታቦቱ አድርጎታልና ነው፥ቅዱሱም በብዙ ገድል
ተቀጥቅጦ፥ቅድስናን ንጽሕናን ገንዘብ በማድረግ ለእግዚአብሔር
ታቦቱ ሆኖ ተገኝቶአልና ነው።እንግዲህ፡-“ታቦቱ፡-ለምን የተክለ
ሃይማኖት፥ የገብረ መንፈስ ቅዱስ ተብሎ ይጠራል?” ማለት፡-
የኢየሱስ ክርስቶስ ስም፡-በልቡናቸው የተቀረጸላቸው፥ሰውነታቸው
ም የእርሱ ማደሪያ የሆነላቸው ቅዱሳን፡-ለምን ተክለ
ሃይማኖት፥ገብረ መንፈስ ቅዱስ ተብለው ይጠራሉ? እንደ ማለት
ነው።ታድያ፡-እነርሱ የኢየሱስ ታቦት(ማደሪያ)
በመሆናቸው፥የእነርሱን ስሞች አስቀርተን “ኢየሱስ” እያልን
እንጥራቸው? እኛስ የፈጣሪን ስም ለፍጡር አንሰጥም፥ እነርሱም
አይሹትም፤ እነርሱ የሚሹት፡-ገብረ ኢየሱስ መባልን
ነው።“ሐዋርያ ሊሆን የተጠራ የኢየሱስ ክርስቶስ ባሪያ ጳውሎስ
በነቢያቱ አፍ በቅዱሳን መጻሕፍት አስቀድሞ ተስፋ ለሰጠው
ለእግዚአብሔር ወንጌል ተለየ፤” ይላል።ሮሜ፡፩፥፩ ። -የመናፍቃን
ዓላማ የቅዱሳንን ስም መፋቅ፥መታሰቢያቸውንም ማጥፋት
ነው፥ቀጥለውም የኢየሱ ስን ስም መፋቅ ነው።ይኸንንም፡-
በምዕራቡ ዓለም ባሉ ጌቶቻቸው ላይ አይተናል።የቅዱሳን ስም
እኮ በዚህ ዓለም ባለች ሰማያዊት ቤተ ክርስቲያን ብቻ ሳይሆን፡-
በልበ ሥላሴም የተቀረጸ ነው። በቅዱስ ዮሐንስ የራእይ መጽሐፍ
ላይ እንደተገለጠው፡-“በሕይወት መጽሐፍ መጻፍ፤”የተባለው
በልበ ሥላሴ መቀረጽን ነው።“ድል የነሣው እንዲሁ በነጭ
ልብስ ይጐናጸፋል፥ስሙንም ከሕይ ወት መጽሐፍ
አልደመስስም፥በአባቴና በመላእክት ፊት ለስሙ
እመሰክርለታለሁ።መንፈስ ለአብ ያተ ክርስቲያናት የሚለውን ጆሮ
ያለው ይስማ፤”ይላል።ራእ፡፫፥፭፤፳፥፲፪።ከዚህም፡-ኢየሱስ ክርስ
ቶስ፡-ሕይወታቸውን ለሞት አሳልፈው እስከ መስጠት
ደርሰው፥በስሙ ለመሰከሩለት ቅዱሳን፡-በስማቸው እንደ
ሚመሰክርላቸው እንማራለን።በወንጌልም፡-“ስለዚህ በሰው ፊት
ለሚመሰክር ልኝ ሁሉ እኔ ደግሞ በሰማያት ባለው በአባቴ ፊት
እመሰክርለታለሁ፤”ብሎአል።ማቴ፡፲፥፴፪።አበ ብዙኃን
አብርሃምን፡-“ስምህንም አከብረዋለሁ፥ለበረከትም
ሁን፥የሚባርኩህንም እባርካለሁ፥የሚ ረግሙህንም
እረግማለሁ፤”እንዳለው፥እነዚህ ኢየሱስ ክርስቶስ ያከበራቸው
የቅዱሳን ስሞች፡-በሰ ማይ ባለ በእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ
መሠረቶችም ላይ ተቀርጸዋል።“በምሥራቅ ሦስት ደጆች፥
በሰሜንም ሦስት ደጆች፥በደቡብም ሦስት ደጆች፥በምዕራብም
ሦስት ደጆች ነበሩ።ለከተማይቱም ቅጥር አሥራ ሁለት
መሠረቶች ነበሩአት፥በእነርሱም ውስጥ የአሥራ ሁለቱ የበጉ
(የኢየሱስ ክርስ ቶስ) ሐዋርያት ስሞች ተጽፈው(ተቀርጸው)
ነበር፤” ይላል።ዘፍ፡፲፪፥፪፣ራእ፡፳፩፥፲፫። -የቅዱሳን ስም እና
መታሰቢያ በመናፍቃን ወሬና ጥላቻ የሚጠፋ
አይደለም።ምክንያቱም በቤቱ ውስጥ የማይጠፋ ስም እና
መታሰቢያ የሰጣቸው እግዚአብሔር ነውና።በነቢዩ በኢሳይያስ
የትን ቢት መጽሐፍ እንደተጻፈው፡-“በቤቴና በቅጥሬ ውስጥ
ከወንዶችና ከሴቶች ልጆች ይልቅ የሚበ ልጥ መታሰቢያና ስም
እሰጣቸዋለሁ፤”ብሎአል።ኢሳ፡፶፮፥፭።ቅዱስ ዳዊት፡-“የጻድቅ
መታሰቢያ ለዘለዓለም ይኖራል፤”ያለው ለዚህ ነው።መዝ፡
፻፲፩፥፮።የሚጠፋው የእነማን ስምና መታሰቢያ እን ደሆነ ሲናገር
ደግሞ፡-“መታሰቢያቸውን ከምድር ያጠፋ ዘንድ የእግዚአብሔር
ፊት ክፉን በሚያደ ርጉ ላይ ነው፤”ብሎአል።መዝ፡፴፫
163 viewsቀሲስ ስንታየሁ የኔአባት, 04:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-31 07:15:53 ታቦት፡- ለምን በቅዱሳን ስም ይሠየማል?” -“የሞኝ ልቅሶ
መልሶ መልሶ፤”፡-እንዲል፥መናፍቃን የኢትዮጵያን መሬት
ከረገጡበት ጊዜ ጀምሮ “በአዲስ ኪዳን ታቦት
ተሽሮአል፤”የሚለውን ሲያስተጋቡ ቆይተዋል።ነገር ግን፡-“እኔ
ሕግንና ነቢ ያትን ለመሻር የመጣሁ አይምሰላችሁ፤”ማቴ፡፭፥፲
፯፤የሚለው የጌታ ቃል እና “በሰማይም ያለው የእግዚአብሔር
መቅደስ ተከፈተ፥የኪዳኑም ታቦት በመቅደሱ ታየ፥መብረቅና
ድምፅም ነጐድጓ ድም የምድርም መናወጥ ታላቅም በረዶ
ሆነ።”ራእ፡፲፩፥፲፱።የሚለው የዮሐንስ ራእይ አላላውስ
ስላላቸው፥ኑፋቄያቸውን በማሻሻል፡-“ታቦት ለምን በቅዱሳን ስም
ይሰየማል?”የሚለውን ጥያቄ፡-መልሰው መላልሰው እንደ ውሻ
ሲያላዝኑ ይሰማል።ቤተ ክርስቲያንም፡-“በእግራቸው እንዳይረግ
ጡት ተመልሰውም እንዳይነክሱአችሁ፥የተቀደሰውን ለውሾች
አትስጡ፥ዕንቈቻችሁንም በእሪያ ዎች ፊት እንዳትጥሉ።”ያለውን
የጌታን ቃል ይዛ፥ከዚህም ጋር ታላቁ ሐዋርያ ቅዱስ ጳውሎስ፡-
“ከውሾች ተጠበቁ፤”በማለት የመከረውን ምክር ገንዘብ
አድርጋ፥በውሾች የተመሰሉ መናፍቃንን አፍ በንጹህ ትምህርቷ
ስትዘጋ ኖራለች። ማቴ፡፯፥፮፣ፊል፡፫፥፪። - -የመናፍቃን
የመጀመሪያውም የመጨረሻውም ሥራቸው እግዚአብሔር
የወደዳቸውን እና ያከበ ራቸውን ቅዱሳን መጥላትና ማዋረድ
ነው።የሚገርመው ነገር፡-“ኢየሱስን እንወደዋለን፤”እያሉ በኢ
የሱስ ስም የተጋደሉትን፥ኢየሱስም የወደዳቸውን ቅዱሳን
መጥላታቸው ነው።ለዚህም ድርጊታ ቸው እንኳን እኛን ራሳቸውን
እንኳ የሚያሳምን መልስ እንደሌላቸው እናውቃለን።ኅሊና
አጥተው እንጂ የተሸከሙትን መጽሐፍ ቅዱስ፡-በመጋዝ እየተ-
ተረተሩ፥በሰይፍ እየተመተሩ (እየታረዱ)፥ በእሳትም እየተቃጠሉ
በአጥንትና በደማቸው የጻፉት ቅዱሳን ናቸው።ሰው እህል
እየተመገበ፡-ታርሳ ተቆ ፍራ ያበቀለች መሬትን እና አርሶ ቆፍሮ
ያመረተ ገበሬን እንዴት ይጠላል? ምክንያቱም እነርሱን መጥላት
ማለት፡-መጋቢነቱ በእነርሱ ላይ የተገለጠ እግዚአብሔርን
መጥላት ነውና። በዚህ ምሳሌ መሠረት፡-“እነዚህ
መናፍቃን፡-“ቅዱሳን የጻፉትን ቅዱሳት መጻሕፍት ተቀብለናል፤”
እያሉ ቅዱሳንን የሚጠሉት ለም ንድነው?”ብለን ብንጠይቅ
መልስ አናገኝለትም።ወገኖቼ፡-እንኳን ቅዱሳንን፥ጠላቶቻችንን
እንኳ እንድንጠላ ጌታ አልፈቀደልንም።“እኔ ግን
እላችኋለሁ፥በሰማያት ላለ አባታችሁ ልጆች ትሆኑ ዘንድ ጠላቶቻ
ችሁን ውደዱ፤”ብሎናል።ማቴ፡፭፥፵፬። - ማንም ቢሆን ቅዱሳንን
ቢጠላ፥ከሁሉ አስቀድሞ ኢየሱስ ክርስቶስን እንደጠላ ማወቅ
አለበት። ይኸንንም፡-“ዓለም ቢጠላችሁ ከእናንተ በፊት እኔን
እንደ ጠላኝ እወቁ።ከዓለምስ ብትሆኑ ዓለም የራሱ የሆነውን
ይወድ ነበር፤ነገር ግን እኔ ከዓለም መረጥኋችሁ እንጂ ከዓለም
ስለ አይደላችሁ ስለዚህ ዓለም ይጠላችኋል።ባሪያ ከጌታው
አይበልጥም ብዬ የነገርኋችሁን ቃል አስቡ።እኔን አሳ ደውኝ
እንደ ሆኑ እናንተን ደግሞ ያሳድዱአችኋል፤ቃሌን ጠብቀው እንደ
ሆኑ ቃላችሁን ደግሞ ይጠብቃሉ።”በማለት አስቀድሞ
ነግሮናል።ዮሐ፡ ፲፭፥፲፰። -መናፍቃን፡-የኢየሱስን ስም ስለጠሩ
እውነተኞች ናቸው ማለት አይደለም፤ምክንያቱም፡-አጋንን ትም
ስሙን ይጠሩታል፥ይለምኑታልም።“ኢየሱስ ሆይ፥የእግዚአብሔር
ልጅ፥ከአንተ ጋር ምን አለን?(አንተን የምንቃወምበት ምን
ኃይል፥ምን ሥልጣን አለን?) ጊዜው (ዕለተ ዓርብ፥ዕለተ ምጽ
አት) ሳይደርስ ልትሣቅየን (ልትፈርድብን) መጣህን? (ነውን?)
ብለው ጮኹ። . . . አጋንንቱም ፡-ታወጣንስ እንደሆንህ ወደ
እሪያው መንጋ ስደደን ብለው ለመኑት፤”ጌታም በእሪያዎቹ
እንዲያ ድሩ ፈቀደላቸው፥ይላል።ማቴ፡፰፥፳፱።ይህ ነገራቸው
ማለትም ስሙን መጥራታቸውና ወደ እርሱ
መለመናቸው፥እነርሱን(አጋንንትን)፡-እውነተኞች
አያሰኛቸውም፥አለቃቸው ዲያብሎስ የሐሰት አባት እንደሆነ ጌታ
በወንጌል ተናግሮአልና።ዮሐ፡፰፥፵፭። -የቅዱሳን ጠላት
ከሳሻቸውም ሰይጣን ነው፤“አሁን የአምላካችን ማዳንና ኃይል
መንግሥትም የክ ርስቶስም ሥልጣን ሆነ፥ቀንና ሌሊትም
በአምላካችን ፊት የሚከሳቸው የወንድሞቻችን(የቅዱሳን) ከሳሽ
ተጥሎአልና፤”ይላል።ራእ፡፲፪፥፲።እርሱ ጻድቁን ኢዮብን ሲከሰው
ታይቶአል።ይሁን እንጂ ፡-“በውኑ ባሪያዬን ኢዮብን
ተመለከትኸውን? በምድር ላይ እንደ እርሱ ፍጹምና
ቅን፥እግዚአብ ሔርንም የሚፈራ፥ከክፋትም የራቀ ሰው
የለም።”በማለት እግዚአብሔር አሳፍሮታል።ጻድቁ ኢዮ ብም፡-
ሰይጣን ያመጣውን መከራ ሁሉ በመታገሥ በሃይማኖቱ ጽናት
ሰይጣንን አሸንፎታል። ኢዮ፡፩፥፰።በአዲስ ኪዳን ደግሞ፡-
በአይሁድ ልቡና አድሮ በጌታ ላይ መከራ መስቀልን እንዳጸ
ናበት፥አናምንም ባሉ በአሕዛብ፥እንዲሁም በአፋቸው እናምናለን
በሚሉ መናፍቃን ልቡና አድሮ በቅዱሳን ላይ መከራ አጽንቶ
ባቸዋል።ቅዱሳንን እንደ ከብት ያሳረዳቸው እርሱ ነው፥ዛሬም
ቢሆን በሀገር ውስጥም ሆነ ከሀገር ውጪ ቅዱሳንን ከማሳረድ
አላረፈም።ይህ በየጊዜው የሚፈሰው የቅ ዱሳን ደም በከንቱ
የሚቀር አይደለም፥እንደ አቤል ደም በእግዚአብሔር ፊት
ይካሰሳል።ዘፍ፡፬፥፲ ።ጌታ በወንጌል፡-“ከጻድቁ ከአቤል ደም ጀምሮ
በቤተ መቅደስና በመሠዊያው መካከል እሰከ ገደ ላችሁት እስከ
በራክዩ ልጅ እሰከ ዘካርያስ ደም ድረስ በምድር ላይ የፈሰሰው
የጻድቅ ደም ሁሉ ይደርስባችሁ ዘንድ፤(ያስፈርድባችኋል)
፤”ብሎአል።ማቴ፡፳፫፥፴፭።በአጸደ ነፍስ ያሉ ቅዱሳንም
፡-“ቅዱስና እውነተኛ ጌታ ሆይ፥እስከ መቼ ድረስ አትፈርድም?
ደማችንንስ በምድር በሚኖሩት ላይ እስከ መቼ
አትበቀልም?”ሲሉ ተሰምተዋል። ራእ፡፭፥፲። -መጽሐፍ ቅዱስ
እንደሚነግረን፥የጌታ ጠላቶች የሆኑ ሰዎች፡-የዲያብሎስ ልጆች
እንደሆኑ ሁሉ፥ የቅዱሳንም ጠላቶች የዲያብሎስ ልጆች
ናቸው።ጌታ፡-“እግዚአብሔርን እናመልካለን፤”እያሉ የተ ቃወሙትን
አይሁድ፡-“እግዚአብሔርስ አባታችሁ ከሆነ በወደዳችሁኝ ነበር፤ .
. . እናንተ ከአባታ ችሁ ከዲያብሎስ ናችሁ፥የአባታችሁን ምኞት
ልታደርጉ ትወዳላችሁ፤”ያላቸው ለዚህ ነው።ዮሐ፡፰፥፵፬።ቅዱስ
ጳውሎስም፡-የተቃወመውን ጠንቋይ፡-“አንተ ተንኰል ሁሉ
ክፋትም ሁሉ የሞላ ብህ የዲያብሎስ ልጅ፥የጽድቅም ሁሉ
ጠላት፤”ብሎታል።የሐዋ፡፲፫፥፲።መናፍቃንም ትክክለኛ የመ ጽሐፍ
ቅዱስ አማኞች፥የጌታም ተከታዮች ቢሆኑ ኖሮ፥የጌታን ቅዱሳን
በወደዱ ነበር፥ነገር ግን አል ሆነላቸውም።እንዲያውም እነርሱን
ከመጥላት አልፈው፥“ቅዱሳንን ለምን ወደዳችሁ?” በሚል
በኦርቶዶክሳውያን ላይ ያላቸው ጥላቻ ገደብ የለውም። -ባለፈው
አንድ ጤንነቱ ያልተረጋገጠ መናፍቅ፡-“ዲያብሎስ
ይረዳችሁ፤”ብሎ ከአንገቱ ሳይሆን ከአንጀቱ የጻፈውን ጽሑፍ
ተመልክቼ፥የጥላቻቸው ጥግ እስከ ምን ድረስ እንደሆነ
ተገንዝቤአለሁ ።ታድያ በመግደል ከሚያምኑ ሰዎች በምን ተለዩ?
እንግዲህ ለወዳጃቸው ለዲያብሎስ ነግረው ሊያሳርዱን
እንደሆነም አብረን እናያለን።ለነገሩ እርሱ ምኑ ሞኝ ነው?
በእነርሱ አድሮ፥በእነርሱው እጅ ነው የሚያርደው።ከላይ
የተጠቀሰው የመናፍቁ እርግማን የሚያሳየው በኦርቶዶክሳውያን
መታረድ፥በአብያተ ክርስቲያናትም መቃጠል መናፍቃኑ ምን ያህል
ደስተኞች እንደሆኑ ነው።ከዚ ህም ጋር አንድ የምናስተው ለው
149 viewsቀሲስ ስንታየሁ የኔአባት, 04:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-30 14:22:00 በመተከል ዞን በዳንጉር ወረዳ የሚገኘው የበላያ ንጉሠ #ዳዊት ገዳም የእርዳታ ጥሪ
ታሪኩን ያለወቀው አውቆ እንዲረዳን
Share share አድርጉልን!
=====
ስለበላያ አጭር ታሪክ

የአድያም ሰገድ ኢያሱ አባት ከንግስናው ከተሻረ በኋለ የጥንት ሀገር ወደ ምትበል በላያ ንጉስ ዳዊት ቀበሌ መጣ።
ከመጣ በኀላ በያዘው ወቅታዊ በሽታ ታሞ አረፈ። የአረፈበት ልዩ ስፍራ ደጥሆ ከሚበል ጎጥ " አባ ላምታ" ሾላ ስር በክብር ተቀበረ ፡፡
ከዚህ በኋላ ልጃቸው አድያም ሰገድ ኢያሱ ንጉስ ከሆነ በኋላ አባቱ የአረፈበትን ፍላጋ መጣ ሲመጣም 7ቱን ፅላት በቄስ አባዋሬ በማስያዝ ወደ በላያ ንጉስ ዳዊት ቀበሌ መጣ ፡፡
አድያም ሰገድ ኢያሱ የአባቱ አፅም አረፎ ከተከበረው ቦታ አፅሙን ይዞ አውጥቶ ሲሄድ
እናዚህን ፅለቶችን እዚህ አባቴ ከተከበረበት ቦታ ፅላቶች ይተከሉ ብሉ ከንጉስ ዳዊት ቀበሌ አስረክቦ ሄደ፡፡
ይህ ገዳም በኢትዮጵያ ኦርተዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲን በመተከል ሀገረ ስብከት በዳንጉር ወረዳ በላያ ንጉስ ዳዊት ቀበሌ የሚገኝ ነው ።
ገዳሙ የተመሠረተውም በ1674 ዓ/ም በትልቁ አዲያም ሰገድ ኢያሱ ጊዜ ሲሆን ይህ ማለትም ቤተክርስቲያኑ 339 በላይ ዓመታት ያስቆጠረ ነው ።ይህ ገዳም ብዙ ታሪክ እና ገቢረ ተአምራት የሰራ እና እየሰራ ያለው ሲሆን

ለምሳሌ :ጠላት ፋሺስት ኢትዮጵያን በወረራት ጊዜ ከ 32 ጊዜ በአውርፕላን በተወረወረ የቦንብ ጥቃት ሳያደረስ መቅረቱን ና አውርፕላኑም ሂዶ ተረራ ለይ እንደወደቃ የወደቀበትም ቦታ እስከ አሁን ድረስ በአገውኛ "እርቡላ" ተብላ ትጣራለች፡፡ይህ ትንታዊ ገዳም የተሠራው በድንጋይና ጭቃ እንዲሁም በውስጡ የተለያዩ ጥንታዊ የብራና መፅሓፍ ያለው እና አዲስ ፋዋሽ ፀበል በቅ/ዳዊትና በቅ/ጊዮርጊስ ስም ወጥቷል።
የአሁኗ በላያ የድሮ የአውራጃው ስያሜም በለያ ነበር::
አሁን ከአውራጃ ወርዶ ምሥለኔ ወይም ቀበሌ ሆኖል:: በምትኩ ምንም ያልነበረው ዳንጉር ወረደ ሆኗል:: ይህ የሆነው በቀ/ ኃ /ሥ ዘመነ መንግስት ነበር::
በላያ ድሮ ግዛቱ በጣም ሰፊ ነበር::
በአንድ ወቅት በዘመነ መሳፍንት ግዛቱ ቋራን ፣ ደምቢያን ፣ ጉባን እና አቸፈርን ጨምሮ አንድ ላይ ነበሩ ይባላል::
የፋሲልን ግንብ የመሰሉ ግንቦች በበላያ እና በጉባ መኖራቸው የዚህ ፍንጭ ይመስለኛል::
የበላያ ድንበሩም በምሥራቅ አገው ምድር አውረጃ ዋና መናገሻዋ ደንግላ ከተማ ኪልቲ ወንዝ: በምዕራብ አሶሳ የሐጂ ሸጎሌ ሀገር እና የአሁኑ ቤንሻንጉል እና ሱዳን::በሰሜን ጎንደር፣በደቡብ መተከል አውራጃ መናገሻዋ ቻግኒ ነበር::
አፄ ኃይለ ሥላሴም በመጽሐፋቸው በላያን አውራጀ ብለው ፅፈዋል::ዋና ከተማው "ንጉሠ ዳዊት ተብሎ የሚጠራው የአሁኑ ቀበሌ ነበር ይላሉ ትላልቆቹ!
ከዛሬ 600 እና 700 ዓመታት በፊት " ዳዊት" የሚባሉ መናኝ -ንጉሥ መንነው መጥተው ገደም አድረገው አንደ መሠረቱ እና እዛው ኖረው እዛው ንጉሠ ዳዊት ቤ/ክ ውስጥ እንደ ተቀበሩም በአፋ-ታሪክ ይነገራል::
ስለ በላያ ማወቅ የሚፈልግ ሰው ከአለ" ዜና ኢትዮጵያ ከአንደኛ ፒኦሪ አስከ ላሊበላ" የሚል መጽሐፍ
በመምህር ቆሞስ አባ ክንፈ ገብርዔል ገ/ኢየሱስ: የተዘከረ :
እንዲሁም " አምሰለ ገነት " የሚል በክቡር ተክለፃዲቅ መኩሪያ የተፃፉ መፅሐፍትን ማንበቡ መልካም ነው::
በተጨመሪ በንጉሥ ዳዊት የሚጠሩ ብዙ ቦታዎች አሉ::
ለምሣሌ- አዛ ዳዊት: አዛ ማለት በአካባቢው ቋንቋ በአገውኛ አዛዥ፣ንጉሥ ወይም መሪ ማለት ነው::
ጃን ወምበር( የጃንሆይ ወምበር)፣ጃን ማለትም ጃንሆይ ወይም ንጉሥ ሆይ ማለት ነው::
በአከባቢው ያሉት ከዛሬ ከ500 እና 600 በፊት የተቆረቆሩት- አብያተ ክርስቲያናት
1: ንጉሠ ዳዊት ወ ጊዮርጊስ- ገዳም ቀበሌ
2: ቅዱስ ሚካኤል- ሳንጃ ሚካኤል ቀበሌ:
3: ተክለሃይማኖት - ባርክቶች ተለሃይማኖት:
4: ቅ/ማርያም- አንከሻ ማርያም:
5: ከቅ/ጊዮርጊስ ጋር ተደርባ የነበርች ቅ/ኪዳነምህረት በኋላ እራሶን ችላ ቻምቺ ኪደነምህረት ሄዳ ተተክላላች::
6: ደቅ እስጢፋኖስ ገደም- ደንጉር:
7: ቅ/ማርያም ገደም- ዳንጉር አካባቢ:
8: ቅ/ ገብርኤል- በዳንጉር የጥንቶቹ ናቸው ::
እስከ አሁኑ ሰአት ተተክሏ እያገለገለ ይገኛል።
ይህ ቦታ በወቅቱ አንቱ የተባሉ ለጎጀም ገጂ እንዲሁም ለዣንሆይ ታማኝ አገልጋይ የነበረው የፊታውራሪ ዘለቀ ሊቁ መከና መቃብርም እዛው ከቤተክርስቲያን አጥር ስር አለ።

√በዚህ የሚነሱ አወዛጋቢ ለሆነው ነገር መልሱ ፅላቱ የአፄ ዳዊት የኢትዮጵያዊው ነው ሲሉ እንዳልሆነ ፅላቱን በዓይን ከአዩት አባቶች በተገኘ ምስክርነት ፅላቱ የእስራኤል ንጉሦ የልበ አምላክ ዳዊት መሆኑን ተረጋግጧል።
በኢትዮጵያ ደረጃ በበላያ ብቸኛው የእስራኤል ንጉሦ የልበ አምላክ ዳዊት ገዳም ነው
ቦታውን ድረስ በመሄድ በረከት እንድታገኙ በአክብሮት አሳስባለሁኝ።

ዛሬ ታሪኩን ልንገራችሁ ብቻ ሳይሆን እገዛ እንድታደርጉልን ለመጠየቅ ነው።
በአካል መሳለም መሄድ የሚፈልግ ወይም ለበለጠ ማብራሪያ 0918469330 በቴሌግራም ማውራት ትችላላችሁ ።
ስለዚህ ማገዝ በገንዘብ መርዳት የምትፈልጉ በዚህ አካውንት እንድትረዱን እያሉ እንማፀናለን።
ስም:-ንጉስ ዳዊት ገዳም ህንፃ አሰሪ ኮሚቴ
በንግድ ባንክ ነው ቁጥሩ 1000446526204


ቀሲስ ስንታየሁ የኔዓባት
እንጅባራ አገው ምድር!
ሐምሌ 23/2014ዓ/ም
635 viewsቀሲስ ስንታየሁ የኔአባት, 11:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-30 14:21:57
409 viewsቀሲስ ስንታየሁ የኔአባት, 11:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-30 01:11:58
227 viewsቀሲስ ስንታየሁ የኔአባት, 22:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-30 00:46:55 ዛሬ 31ኛ ዓመት ልደቴ ነው።
የእድሜ እኩሌታ ደርሰን ፩ ዓመት ዓለፈን።
====
ዘንድሮ ልደቴን ቀን የማስበው ደስታና ሀዘን በቀለቀለ መንፈስ ነው ።ወላጅ አባቴን ባአጣሁት በ4ወር እንዲሁም ልጄ ባናን ስንታየሁን በወለድኩት በ10ኛው ወር
ሀዘን እና ደስታ በተቀላቀለ ስሜት ሁኜ ነው የማሳልፈው
ልክ ዛሬ ከ31ዓመት በፊት በእለተ ማክሰኞ 1983 ዓ/ም ከውዷ እናት ካሉኝ ከተወለዱት ልጆች ሁሉ መጨረሻ ልጅ ሁኜ ተወለድሁኝ ።
6እህቶቼ እና 3ወንድሞቼ የተወለዱበትን ማህፀንም ዘግቼ መጨረሻ ና አስረኛ ልጅ ሁኜ በዚህች እለት ተወለድኩኝ ።
እናቴ በዚህ ዓለም ስኖር ዘጠኝ ወር ያህል የተሸከምሽኝን ሦስት ዓመት በጀርባሽ አዝለሺኝ ለስድስት ዓመታት ጡጦችሽን ይጄ የጠባሁት ቀርቶ በዚያን ዛሬ 31 ዓመት አመሻሽ ላይ በምጥ ተጨነቅሽባትን የአንድ ሰአት ጭንቀት ያህል ራሱ ውለታሽን ልመልስልሽ አልችልምና እናቴ ኑሪልኝ ።እናቴ ከማህፀን አምጣ ብትወልደኝም አባቴም እንደ እናቴ በማህፀኑ ባይሸከመኝም ሳልወለድ ጀምሮ በጭንቅላቱ እያንሰለሰለ ከተወለድኩኝ በኋላም ከእርሻ ውሎ ደክሞ እያለም በትክሻው አዝሎኝ አሳድጎኝ ውዳሴ ማርያምን በቃል እያስጠናኝ አይዞህ እያለኝ እያስተማረኝ የአያትህን መስቀልና ዳዊት ያዝ እያለኝ እንዲሁም የተሰለ ሰይፍ እንድሆን በቀን የአስኳላን ለሊት የአብነት ትምህርት እንድማር ሲመክረኝ አይዞህ እያለኝ የሃይማኖቴን ትምህርት ከአስኳላው ጋር አያይጄ እንድማር ላደረገኝ፣ የሀገር አድባር ሽማግሌ የደግነት አርአያ ሁኖ በምክር አሳድጎኛልና አባቴ ነፍስህን ይማርህ።
√√√√√√
እንዲሁም አባቴ እና እናቴ እንዲህ አድርገው አሳድገውኝ ለወግ ለማዕረግ ሊያበቁኝ ሲያስቡ ሴት አጭተው ሊያጋቡ ሲሉ በነበረኝ አለመረጋጋት ና ጭንቀት ዛሬ ሦስት ዓመት ጥር ፯/፳፻፱ዓ/ም ላገባ ብዬ በአስበኩት ሰአት እንደ መለአክ ከየት ተገኘች ሳትባል ሩቅ ሁና ቅርብ እንደለ ሰው አይዞህ ብላ እየመከረችኝ ለትዳር ህይዎት እንድበቃ ላደረገችኝ ለቃል ኪዳን እናቴ ለአልማዝ መኰነን በለሽበት ምስጋና ይድረስሽ!
====
ልክ ዛሬ ከ31ዓመት በፊት በእለተ ማክሰኞ 1983 ዓ/ም ከውዷ እናት ካሉኝ ከተወለዱት ልጆች ሁሉ መጨረሻ ልጅ ሁኜ ተወለድሁኝ ።በወቅቱም ደርግ ሊወጣ ኢህአዴግ ሊገባ ብዙ ግርግር ሁኖ አባቴ ተስቃይቶ ስለነበር ስሜንም ስንታየሁ ብለው አወጡልኝ።
√√√√√√
በህይወቴ ራሴን አወቅሁ ካልኩበት ብዙ ነገርንም አየሁኝ ።
አሁን ግን የእድሜ እኩሌታ የሚባለውን 31ኛ ዓመት አስቆጠርኩኝ።
እድሚዬንም አጋመስኩ እኔም ከህፃንነቴ ከነፈሰው ጋር መንፈሴን በመተው ወደ ቁምነገሩ እናት ሀገር ኢትዮጵያን እና ልጅነትን ወደ አገኘሁባት ወደ አሳደገቺኝ እናት ቤተክርስቲያን ለአግልግሎት በስፋት የምነሳበት ለማገልገል ከልቤ የምቆርጥበት ጊዜዬ ነው ።ስለዚህ ከፊቴ የምወጣው ደገቱ እና የምወርደው ቁልቁለት በጣም አድካሚ እና አሰልቺ ስለሆነ ከእኔ የበረታችሁ አይዞህ እያላችሁኝ እንዲሁም እየመከራችሁኝ ወደ ዘለዓለማዊ መኖሪያችን እስከምንጠራ ቀሪ ጊዜውን እንድንቀጥል በተለይም በአግልግሎቴ ከጎኔ እንድትቆሙኝ በእግዚአብሔር ስም እጠይቃለሀ።
ይህንንም እንድሰራ እነዛ በዛጒዌ ዘመን የነበሩ ቅዱሳን ነገሥታት የአባቶቻችን የእነቅዱስ ላሊበላ ፣የእና ቅዱሰ ይምርሃነ ክርስቶስ ፣የእነ ናአኲቶለአብ እና ገ/ማርያም አምላክ ይርዳኝ።
በወጣትነትህ ለአግልግሎት የተመረጥክ ቅዱስ ጊዮርጊሰ ሆይ አንተ እርዳኝ።

ቀሲስ ስንታየሁ የኔአባት
እንጅባራ --ኢትዮጵያ
ሐምሌ 22/2014ዓ/ም ከምሽቱ 6፡20ተፃፈ
230 viewsቀሲስ ስንታየሁ የኔአባት, 21:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-27 18:37:45 1ኛ. አባ ጀምበሬ / ወልደ ሰንበት/
2ኛ. አባ ደጉ /ገብረ ማርያም / ይባላሉ፡፡
እነዚህ አባቶች መጀመሪያ ከሚገኘው መናንያን ከሚኖሩበት ከግልጹ ከጉም ኢየሱስ ገዳም ለብዙ ዘመናት የኖሩ ሲሆኑ አንደኛው አባት አባ ጀንበሬ /ወልደ ሰንበት/ የዚያው አካባቢ ተወላጂ የሆኑት ከሩቅም ከቅርብም ሀገር ወደ ሥውሩ ገዳም ብሔረ ሕያዋን መካነቅዱሳን ጉምሳዊት ወደ ተባለው ቦታ መንገድ መሪ ሆነው ሲያመላልሱ፣ ከዚያም ያሉትን በማስተናገድ ሲረዱና ሱባኤ ገብተው ተስፋ አግኝተው ለሰውም ተርፈው ኅይለ አጋንንትን፣ ድምጸ አራዊትን ድል ነሥተው ለምዕመናን ብዙ ትሩፋት ሲያደርጉ የኖሩ ትሩፋታቸውም ውኃ ቀድተው ፣ከጫካ እንጨት ሰብረው አቅመ ደካማ የሆኑ አበውን ሲረዱ ኑረው “ክቡር ሞቱ ለጻድቅ በቅድመ እግዚአብሔር” እንዳለ ልበ አምላክ ቅዱስ ዳዊት ያለምንም ፃዕር በ፻፴ ዓመታቸው ዐርፈዋል፡፡
ኹለተኛው አባት አባ ደጉ /ገብረማርያም/ የተባሉት አባትም እንደ አባ ጀንበሬ ኹሉ ብዙ ትሩፋት ሲያደርጉ ለአቅመ ደካሞች አበው ምግብ በማቅረብ፣ ምግብ በማብሰል ሲረዱ ኑረው ዐርፈዋል፡፡
ከጎንደር ክፍለ ሀገር የመጡ አንድ መምህር በዚሁ ድንቅ በሆነው ቦታ ሱባኤ ገብተው እያለ የማኅሌቱን ድምጽ ሰምተው ድምጽ ወደሚሰሙበት እንደ ሄዱና ማኅሌቱ ደምቆ እንዳለ የሚያገለግሉም ቅዱሳን አባቶች እንደኾኑ በሥውር ያለችው በቅዱሳን የምትገለገለዋ ቤተ ክርስቲያንም የኪዳነ ምሕረት ታቦት እንደ ኾነች ሲናገሩ እሳቸው ግን እዚያ ለመኖር እንደማይችሉና ዕጣ ፈንታቸው ወደ ዓለም ወጥተው ስለ ክርስቶስ መመስከርና የእግዚአብሔርን ቤተሰብ ማፍራት መሆኑ እንደተነገራቸው የክርስቶስን ቃል በመመስከር ላይ እያሉ ፈጣሪያቸው እንደሚጠራቸው የተነገራቸው መኾኑን ሲነግሩን በዚያ ሥውር ቦታ ያሉት ቅዱሳን ምግባቸው መዐዛ ገነት እንደ ሆነና በየመቶ ዓመታቸው እንደሚታደሱም አስረድተዋል፡፡
አባ ጊዮርጊስ የተባሉት አባትም እዚሁ ቦታ ፵ ዘመን ዘግተው ከቆዩ በኋላ ዕረፍታቸው ጎንደር ክፍለ ሀገር አላፋ ጣቁሳ ከተባለው ቦታ እንደሚሆንና ከዐረፉበትም ቦታ ለሕሙማን ፈውስ የሚሆን ውኃ እንደሚመነጭ ተነግሯቸው ከተባለው ቦታ ሂደው እንደ አረፉና ከዚያም ቦታ ብዙ ሕሙማን የሚፈወሱበት መዋት /ፍል ውሃ/ እንደ ተገኘ ታሪክ ይመሰክራል፡፡
መምህር ድሜጥሮስ የሚባሉ የመጽሐፍ መምህር ከመርጡለ ለማርያም ገዳም መጥተው ሱባኤ ገብተው እያሉ የያሬድ ሦስት የሠረገላ መንኮራኩሮችን እንዳዩ መስክረዋል፡፡ እነዚህም መንኮራኩሮች አንዱ ወደ ብር ሸለቆ /አባ ጨው ገዳም/፤ ኹለተኛ ወደ አንከሻ ወረዳ ሙላ ተክለሃይማኖት ገዳም፣ ሦስተኛው ደግሞ ወደ ዋልድባ ገዳም የሚወስዱ እንደኾኑ ከመሰከሩ በኋላ የእኔ ብጽዓት ትኹን ብለው ለቤተ ክርስቲያን አንድ የብራና መጽሐፍ፣ መዝሙርና መዋሥዕት አበርክተዋል፡፡ ይህ የሠረገላ መንኮራኩር ድምጽም ከበረሃው ተራራ ጫፍ ላይ ለማንኛውም ሰው ይሰማል፡፡ ይህን ተአምረኛ ቦታ ያዩ የታደሉ ብዙ ሰዎች የአካባቢ ነዋሪዎችም ሆኑ ሱባኤተኞች ዕፁብ ነው ዕፁብ ነው እያሉ ያደንቃሉ፡፡ በዚያ ቦታ በሥውር ያሉ ቅዱሳን ለአንዳንድ ዕድለኞች ተከሥተውላቸው ሲናገሩ “የቅዱሳኑ ብዛት ወደ ቤተክርስቲያኑና ወደ በረሃው ሲመላለሱ ሲታዩ በዚህ ዓለም ሰው ያለ አይመስልም” ይላሉ፡፡ የእግዚአብሔር ሥራ ዕጹብ ድንቅ ነው በማለት ብዙዎች በአንክሮ የተመለከቱትን መስክረዋል፡፡ ይህ ነገር እስከ ዛሬ ለታደሉት ይከሠታል፡፡
አንድ አጋጄ ጂማ የተባለ አዳኝም ከዚያው ቦታ አደን ከሄደበት ርቦት የሚበላ ነገር ሲፈልግ ከአንድ ቦታ ላይ ያፈሩ እንኮይና ዘንባባ አይቶ ጠጋ ብሎ ከቆየ በኋላ ከየት መጣ ሳይባል “አይበቃህም አንተ” የሚል ድምጽ ሰምቶ ደንግጦ ሲቆም ይበላው የነበረው ዘምባባ በሰው ላይ የበቀለ ስለነበር ጉዞውን እንደ ጀመረ ማየቱን ይመሰክራል፡፡ ብዙ አባቶችም ሠሌን የበቀለባቸው ደጋጎች መኖራቸውን ይናገሩ ነበር፡፡
እማሆይ ወለተ ማርያም የተባሉ የዚያው አካባቢ መነኩሲት ነበሩ፤ እኒህ መነኩሲት ዐብይ ፆም በገባ ጊዜ ቤተሰቦቻቸው ከሱባኤ መያዣው በረሃ እንዲወስዷቸው ከአስረዱ በኋላ ቤተሰቦቻቸውም የእማሆይን ትዕዛዝ አክብረው ይወስዷቸዋል፡፡ ቤተሰቦቻቸው የሥቅለት ዕለት ተመልሰው ሂደው እማሆይ ወለተ ማርያምን ስትሰግድ በሩቁ አይተዋት በቀረቡ ጊዜ ከዚህ መጣ የማይባል ደመና ጋረዳቸውና ከዚያ በኋላ ቤተሰቦቻቸው በዓይነ ሥጋ ሊያዩዋቸው አልቻሉም፤ የእማሆይን ድምጽ ግን ይሰሙ እንደነበርና ሰዎችም እየተጯጯኹ ወደ በዓታቸው በገቡ ጊዜ “አይዟችሁ ለመልካም ነውና አትሸበሩ” የሚል አጽናኝ ቃል የተጻፈበት ወረቀት አግኝተው ተመልሰዋል፡፡
እማሆይ ገነት የሚባሉ መነኩሲት ከገዳሙ ውስጥ የሚኖሩትን ሁለት መነኮሳዪያት ማለትም እማሆይ አጸደ ማርያምና እማሆይ ወለተ ሃና የተባሉትን ለበረከት ያህል ወደ ቤታቸው ይዘዋቸው ሲሄዱ የአንደኛዋ እጃቸው እፍር እፍር ያለ ስለሆነ እማሆይ ገነትን መቀነቴን አስታጥቂኝ ሲሏቸው አስታጠቋቸው እንደ ጨረሱ ሁለቱንም መነኮሳዪያት የሚሽከረከር ዐየር መጥቶ እንደ ወሰዳቸውና እስኪሠወሩ እንዳዩአቸው እስከ ዛሬ ድረስ ይመሰክራሉ፡፡
ሁለት ወንዶች ከዕበያ /ዳንጉር ማርያም/ ገዳም መጥተው ጉም ኢየሱስ ገዳም ከገቡ በኋላ ከገዳሙ ነዋሪ እማሆይ አልጋነሽ /ወለተ ሰንበት/ የውኃ መቅጃ ለምነው ወደ ሱባኤ መግቢያ በረሃ ሂደው ከገቡ በኋላ አንደኛው የወሰዱትን ቅል ለእማሆይ አልጋነሽ አስረክበው ሲሄዱ “ጓደኛህሳ” ተብለው ሲጠየቁ “እኔ ነኝ እንጂ ኃጢአተኛው እሱማ እዚያው ተስፋ አግኝቶ ቀረ እኔ ነኝ እንጂ ኃጢአተኛው” እያሉ እያዘኑ ተመልሰዋል፡፡
አባ ዘርዐ ቡሩክ /ገብረ ኪዳን/ የተባሉ ለብዙ ዘመናት እዚህ ቦታ የቆዩት ከሱባኤ መግቢያ ቦታ ወተት የሚፈስበት ቦታ አየሁ ብለው መስክረዋል፤ የቦታውንም ደግነት እጅግ ያደንቁ ነበር፡፡ የዚህ ብሔረ ሕያዋን መካነቅዱሳን ጉምሳዊት ሱባኤ መያዣ ሥውር ገዳም በመባል የሚታወቀው በዚህ ዘመን ተመሠረተ መስራቹ እገሌ ነው ተብሎ የሚታወቅ አይደለም፡፡ የዚህ ቦታ ታሪክና በዚህ ቦታ እግዚአብሔር ለሰው ልጅ የሚሠራው ሥራ ግን ዕፁብ ና ድንቅ ነው፡፡

የቻናሉ ሊንክ https://t.me/kSintyehu
የመወያያው ሊንክ https://t.me/YichusaTube
ሰብስክራይብ ለማድረግ የዩትዩብ ሊንክ https://www.youtube.com/channel/UCAGGkLhokHIprgEC4xJhW9g
ይቹሳ ማለት በአገውኛ ቋንቋ እናቴስ ማለት ነው ።
አግልግሎትን ለመደገፍ ያነግሩኝ።

ቀሲስ ስንታየሁ የኔ አባት
ጥር ፬ቀን፳፻፲፫ዓ/ም
አገው ምድር --ጉም ኢየሱስ ገዳም
300 viewsቀሲስ ስንታየሁ የኔአባት, 15:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-27 18:37:45 በገዳመ ቆሮንቶስ ጉም ኢየሱስ ገዳም ስለሚገኘው ብሔረ ሕያዋን መካነቅዱሳን ጉምሳዊት ሱባኤ መያዣ ቦታ አጭር ዳሰሳ
በቀሲስ ስንታየሁ የኔ አባት የተፃፋ
============
ብሔረ ሕያዋን መካነቅዱሳን ጉምሳዊት ሱባኤ መያዣ ሥውር ገዳም ለመሄድ ማኅበረ መነኮሳት በአንድነት ከሚኖሩበት ገዳም ከደረሱ በኋላ ደጅ ተጠንቶ ሲፈቀድ ከገዳሙ አንድ መንገድ መሪ ተቀብሎ ነው መሄድ የሚቻለው፡፡ የገዳሙ መነኮሳት በአንድነት ከሚኖሩበት ገዳም በኋላ ጫካ ለጫካ ኹለት ሠዓት ያህል ከተጓዙ በኋላ መናኞች ሱባኤ የሚገቡባቸው ከድንጋይ ተፈልፍለው በበር ተከፋፍለው ከድንጋይ የተሰሩ ቤቶች ግድግዳቸውም ጣሪያቸውም ድንጋይ የሆኑትን ያገኛሉ፡፡
በዚህ ቦታ ሱባኤ የሚገቡ ሰዎች ውኃ የሚጠጡት ሱባኤ ከሚገቡበት ተራራ ሥር ከሚገኘው ውኃ ነው፡፡ ይህ ውኃ በክረምት አይበዛም አይደፈርስም በበጋም አይጎድልም መልኩ ሰማያዊ ነው፤ አይቀየርም ማየ ሕይወት ይሉታል፤ በጣም ፈዋሽ ነው፡፡ በዚህ ሥውር መካነ ቅዱሳን ቦታ ከጥንት ጊዜ ጀምሮ ሱባኤ ለመግባት ከታላላቅ ገዳማት ከማኅበረ ሥላሴ፣ ከዋልድባ፣ ከደብረ ዳሞና ከሌሎችም ታላላቅ ገዳማት ኹልጊዜ ለሱባኤ የሚመጡ ቡሩካን አበው አሉ፡፡ በዚህ የፍጹማን መኖሪያ በሆነው ብሔረ ሕያዋን መካነቅዱሳን ጉምሳዊት ሱባኤ መያዣ ድንቅ የሆኑ የልዑል እግዚአብሔር ሥራዎች ይፈጸማሉ፡፡ ምድራውያን መላእክት የሆኑ አግብርተ እግዚአብሔር ቅዱሳንም በዚሁ መጠነ ሰፊ በሆነ የጉም ኢየሱስ የደን መሬት ክልል ለመንገደኞች፣ለእረኞች፣ ለአውሬ አዳኞች ይገለጻሉ፡፡ በዚህ የጉም ኢየሱስ ሰፊ የደን ክልል ለብዙ ሰዎች የከበሮ፣ የማኅሌት ድምጽ ይሰማቸዋል፡፡ መዐዛ ዕጣን ይመስጣቸዋል፡፡ ውኃ ሲጠማቸው ከሱባኤው መግቢያ ለመጠጣት ሔደው ጫጫታና ጨዋታ በሚጀምሩበት ጊዜ ሰዎቹ በአካል ሳይታዩ በቃል ሰብዓዊ አትንጫጩ፣ አትረብሹ፣ ኽፓን በማለት ምክረ ተግሳጽ እንደሚያሰሟቸው ከቦታው የደረሱት ሁሉ ይናገራሉ፡፡ “ኽፓን” ማለትም በአከባቢው በሚነገረው አገውኛ ቋንቋ “ዝም በሉ” ማለት ነው፡፡
በዚያው ብሔረ ሕያዋን መካነቅዱሳን ጉምሳዊት ሱባኤ መያዣ ሥውር አካባቢ የጸሎት መጽሐፍ፣ ልብስና ጭራ ወድቆ ይገኝበታል፡፡ ይኸውም ባሎቻቸው ካህናት የነበሯቸው ፫ቱ እናቶች ባሎቻቸው ከዚህ ዓለም በሞት ቢለዩባቸው መንኩሰው በንጽሕና በቅድስና ገዳመ ቆሮንቶስ ጉም ኢየሱስ ደጅ ከጠኑ በኋላ በወዲህኛው ወደ ተአምረኛው ብሔረ ሕያዋን መካነቅዱሳን ጉምሳዊት ሱባኤ መያዣ ሥውር ገዳም በመሄድ እዛው ቅዱስ ቦታ ላይም በመቆየት ሱባኤ ገብተው ፵ ቀን ከጨረሱ በኋላ በ፵ኛው ቀን እነዚህ እናቶች ሱባኤ ከገቡበት ዋሻ ብርሃን ሞልቶ ቀስተ ደመና ተተክሎበት በመታየቱ በጎን በኩል ሱባኤ የገቡት መናኞች ይህን ተአምር ዐይተው ለመረዳት ወደ እናቶች በዓት ቢሄዱ እነዚያን እናቶች ሳያገኟቸው ልብሳቸውን ብቻ አግኝተው ተመልሰዋል፡፡
እነዚያ 3ቱ እናቶች፡-
1ኛ. እማሆይ ወለተ ማርያም የዓለም ስማቸው አደሪት ወልደማርያም
2ኛ. እማሆይ ወለተ ኢየሱስ (ከሌላ ቦታ የመጡ መነኩሴ)
3ኛ. እማሆይ ወለተ ሰንበት (ከሌላ ቦታ የመጡ መነኩሴ) ናቸው፡፡
እማሆይ ወለተ ማርያም የዓለም ስም አደሪት ወልደማርያም የዚሁ የአርጃ ቀበሌ ተወላጅ ሲሆኑ ለዚህ ማስረጃ የእማሆይ ወለተ ማርያም (አደሪት) የልጅ ልጃቸው ከቦታው እስከ አሁን ድረስ ይገኛሉ፡፡
ሌላው በገዳሙ ከተደረጉ ገቢረ ተአምራት ውስጥ አንድ አባ ከሀሊ የተባሉት ባሕታዊ ፊታውራሪ ደረሶ ተሰማ የሚባሉት የገዳሙን ቤተ ክርስቲያን በሚሠሩበት ጊዜ የቤተ ክርስቲያኑ መሠረት ሲመሠረት አንድ የመሠረት ድንጋይ ለ፳ ሰዎች አልነሣቸው ብሎ የቀረውን እኒህ አባት ግን ሰዎችን ፈቀቅ አድርገው ብቻቸውን አንሥተውታል፡፡ ለግዙፋን ፳ ሰዎች አልነሣ (አልቻል ያላቸውን) ለአንድ በጉልበት ለደከመ መነኩሴ መነሣት መቻሉ ለተመለከቱት ሰዎች ኃይሉ የሰው ሳይሆን የእግዚአብሔር መሆኑን የዚህ ተአምር ሥራ አስገንዝቧል፡፡
ሌላው ደግሞ አባ ገብረ ጻጽቅ ከሸዋ ክፍለ ሀገር ከአንኮበር፣አባ ገብረ ሥላሴና አባ ገብረ እግዚአብሔር ከዋልድባ ገዳም፣አባ ገብረ ሚካኤል ከማኅበረ ሥላሴ ገዳም ወደዚህ ቦታ ምዕራፈ ቅዱሳን ወደ ተባለው ገዳመ ቆሮንቶስ ጉም ኢየሱስ ገዳም በአንድ መንፈስ ተመርተው መጥተው ወደ ገዳሙ ከደረሱ በኋላም ከገዳሙ ማኅበረ መነኮሳት ወደ ተአምረኛው ብሔረ ሕያዋን መካነቅዱሳን ጉምሳዊት ወደ ተባለው ሱባኤ መግቢያ የሚወስዳቸው መሪ ጠይቀው ከገዳሙም መሪ ተሰጥቷቸው ሔደው ሱባኤ ከያዙበት በዓታቸው ላይ ሱባኤ ከጀመሩበት ፵ኛው ቀን ላይ ቀስተ ደመና ተተከለ በዓታቸው በብርሃን ተሞላ መዓዛው ይመስጥ ጀመረ መሪ አድርገው የወሰዷቸው አባትም አብረዋቸው ስለነበሩ ቀስተ ደመና ከተተከለ በኋላ በዓታቸው ሔደው ቢመለከቱ ቅዱሳኑን አላገኟቸውም፡፡ የ3ቱን አባቶች ጭራቸውን የ4ኛውን አባት ግን መጽሐፈ ብርሃን አግኝተው ይዘው መጥተው ለገዳሙ ያስረከቡት እስከ ዛሬ ድረስ ከቦታው ይገኛሉ፡፡ እነዚህ አባቶች ይዘውት የነበሩትን ጭራዎችና መጽሐፈ ብርሃን አግኝተው ለገዳሙ ያስረከቡት አባቶች፡-
255 viewsቀሲስ ስንታየሁ የኔአባት, 15:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ