Get Mystery Box with random crypto!

ቀን 01/09/2015 ዓ/ም የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የ 6ኛ እና 8ኛ ክፍል | ኮተቤ ብርሃነ ህይወት ትምህርት ቤት

ቀን 01/09/2015 ዓ/ም

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የ 6ኛ እና 8ኛ ክፍል ከተማ አቀፍ ፈተና ቀናት ይፋ አደረገ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የፈተና ዝግጅትና አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ዲናኦል ጫላ የ 8ኛ ክፍል ፈተና ሰኔ 19 እና 20 እንዲሁም የ 6ኛ ክፍል ፈተና ሰኔ 26 እና 27 እንደሚሰጥ ተናግረዋል።

አያይዘውም ቢሮው ከተማ አቀፍ ፈተናዎቹን ውጤታማ በሆነ መልኩ ለመስጠት ከፍተኛ ዝግጅት ሲያደርግ መቆየቱን የተናገሩ ሲሆን ትምህርት ቤቶች ተማሪዎቹን የበለጠ ማዘጋጀት እንዲችሉ ከከተማና ክፍለ ከተሞች ጋር በጋራ በመሆን የሞዴል ፈተናዎችን እንዲሰጡ አሳስበዋል።

በ2015 ዓ.ም 75ሺህ 100 የ8ኛ እንዲሁም 75ሺህ 78 የ6ኛ ክፍል ተማሪዎች ከተማ አቀፍ ፈተናውን እንደሚወስዱ የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ መረጃ ያመለክታል።

Share for your friends
@ShewaferaGetaneh
@ShewaferaGetaneh
@ShewaferaGetaneh