Protein powders ከእንስሳት ወይም ከእፅዋት ማለትም እንደ ወተት፣ እንቁላል፣ ሩዝ ወይም አተር ካሉ ምግቦች የሚሰሩ የፕሮቲን ምንጭ ናቸው። የ Protein powder ጥቅም: -የሰውነት ክብደትን ይቀንሳል -ለጡንቻ እድገት እና ጥንካሬ ይረዳል -የተጎዳ ጡንቻን ለመጠገን ይረዳል Protein powder ከመጠቀማችን በፊት ምን ያህል ፕሮቲን ለሰውነታችን እንደሚያስፈልግ ማወቅ አለብን። ከምግባቸው ውስጥ በቂ ፕሮቲን የማያገኙ ሰዎች ወይም የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ለሚያደርጉ ሰዎች በቀን ከ25-50 ግራም እንዲወስዱ ይመከራል። ይሁን እንጂ ብዙ የፕሮቲን መጠን መውሰድ የለብንም። የፕሮቲን መጠን በሰውነታችን ውስጥ ሲበዛ የምግብ መፈጨት ችግር (የሆድ መነፋት፣ የጨጓራ ህመም እና የሆድ ቁርጠት) ያመጣል። https://korojo.app/download 1.3K views08:13