Get Mystery Box with random crypto!

​​ ብቸኝነቴን ...... መልሺልኝ ክፍል ሀያ አራት (24 ) . . . በፖሊስ ጣቢያው የምር | ETHIO BOOKS PDF

​​ ብቸኝነቴን ...... መልሺልኝ

ክፍል ሀያ አራት (24 )
.
.
.
በፖሊስ ጣቢያው የምርመራ ቢሮ ውስጥ ኬብሮንን እየመረመረች ያለችው
ፖሊስ ሌሎቹን ተመለከተች እሱም ለጥያቄው መልስ እንድትሰጠው
በአይኖቿቸው ነገሯት።
" አሁን ዝም ብለህ ወንጀልህን እመን " አለች መርማሪ
" ምንም ወንጀል አልሰራሁም " አላት በድፍረት በኬብሮን
" ዝም በል እራሰህም ከተናገርከው ......"
" እኔ ከተናገርኩት እ ምን ወንጀል ሰራሁ አስገደደቺኝ እንጂ " አላት ኬብሮን
በግርምት አየቺው።
በዚህ ወቅት ሰላም መኪናዋን እያሽከረከረች ፖሊስ ጣቢያ ግቢውስጥ አቁማ
ልትወርድ ስትል ስልኳ ጮሀ የደዋዩን ማንነት አየቺው አድማሱ ነበር ከመኪናዋ
እየወረደች ማናገር ጀመረች ። አድማሱ ቃልኪዳንን አዲስ የምታሰራው ባለ አንድ
ፎቅ መኖሪያ ቤት ውስጥ ያላለቀውን ህንፃ ብቻዋን እየጎበኘች እንደሆነና ምን
እንዲያደርጋት ጠየቃት እሷም አደጋ አስመስለህ እንዲገድላት ነገረቺው እና
በቀጥታ ኬብሮን ወደ የሚመረመርበት እየመጣች ሳለ በር ላይ ተቀምጣ
የነበረቺው ማክዳ አይታት ተደበቀች ሰላምም እንደደረሰች በሩን አንኳኩታ ከፍታ
ገባችና ።
" አንቺ እውነት ለህግ ከቆምሽ የእሱን ፊት የቦክስ መለማመጃ አድርጋው
ቀጥቅጣው ፊቱ እንዲህ ሲበላሽ የት ነበርሽ " አለቻትና አገጩን ይዛ አሳየቻት።
" አንቺ ልጅ ምንድን ነው የምታወሪው እስቲ ቀስ ብለሽ እደጊ ...... አሁን ተይኝ
እኔ እራሴ አሞኛል " አለቻት
" አይ እማ እኔ ብተውሽ እሱ ልብሽ ውስጥ ያለው ፍቅር እሺ ብሎ ይተውሻል እ እ
እናቴ..." በፈገግታ አያየቻት
" አንቺ ምን አይነት ልጅ ነሽ ገና ህፃን ልጅ እኮ ነሽ"
" ማን እኔ ነኝ ህፃን ......." ስትል በሩ ተንኳኳ እና ተከፍቶ ሚካኤል ገባ እና
በፍራቻ ሁለት እጆቹን ወደ ፊት አጣምሮ ቆመና አይን አይኗን ሲያይ ። ሚጣ
አየቺውና።
" እማ ህፃን ልጅ እሱ ነው ....... እይው እንዴት እንደፈራ አያስቅም እማ በጣም
ያስቃል?" አለችው ። ሚኪ በድንጋጤ ኮስተር ብሎ ሚጣን አያት እና ሰርካለምን
አያት።
" ቆይ አትመጣብኝ ብዬህ አልነበር ለምን መጣህ?" አለችው
" እኔ እኮ ግርምምም የምትይኝ እማ የሌለብሽን በሀሪ አጉል ቁጡ ሴት ተናጋሪ
መጥፎ ሴት ለመምሰል የምትሞክሪው ነገር አይገባኝም የዋህ ምስኪን አንጀት
ለማንም ስፍስፍ እንደሚል አውቃለው....." እያለች ሚጣ ስታወራ ሰርካለም
አፍራ በቁጣ ።
" አንቺ ልጅ ምነው ዝም ብትይ ሚጥሚጣ ሆንሽብኝ እኮ "
" እማ ለምን እውነቱ ሲነግርሽ የምትቆጪው ለሰው ሁሉ አንጀትሽ ይሰፈሰፋል
ለምንድን ነው ሚኪ ላይ ከመሬት ተነስተሽ ዘራፍ የምትይበት ይሄ ፍቅር
አይደል?"ስትላት
" አንቺ ልጅ ሂጂ ውጪልኝ ምን የተረገመች ነች " አለች ሰርኬ
" አልወጣም እኔም በሽተኛ ነኝ አልጋ እኮ ይዤያለው አንቺ ዶክተር ነሽ እንዴ እኔን
ማስወጣት አትችይም " አለች በማላገጥ እያሾፈች ሰርካለም ተናዳ ልትናገር
ስትል ሚካኤሌ በመሀል በመግባት።
" ችግር የለም ሰርኬ እኔ እወጣለው በልጅና በእናት መሀል አልገባም ግን አንድ
ጥያቄ መጠየቅ ፈልጌ ነው።"
" እረ ሚኪዬ አባቴ በመሀል አልገባህብንም እሺ ጠይቅ ችግር የለም በአግባቡ
የማይመለስ ጥያቄ የለም"አለች ሚጣ ሁለቱንም አከታትላ እያየች። ሰርካለም
አየሩን በንዴት በሀይል ወደ ውስጧ ሳበችውና መልሳ አወጣቺው።
" ውይ..... ውይ..... በጣም ወሬ አብዝተሻል ልጄ "አለች ሰርካለም ሚጣ
በአዎንታ ፈገግ ብላ ጭንቅላቷን እየነቀነቀች
" ይቅርታ ሰርኬ የመጣሁት ማን እንዳናደደሽ እንድትነግሪኝ ነበር ፍቃደኛ
ከሆንሽ ?" አላት አሁንም በፍራቻ እጁን ወደ ፊት አድርጎ አጣምሮት። ሰርኬ
አየቺው እና።
" ምን አገባህ ማን ስለሆንክ በምን ተናደሽ ነው የምትለኝ " አለች በቁጣ
ሰርካለም። ሚካኤሌ ደንግጦ ቅልስልስ እያለ።
" ማንም አይደለሁም ምንም ፈልጌም አይደለም " አላት
" ስለዚህ ካላገባህ በሽተኛ ነኝ ለምን አትወጣለኝም " አለችው ቀዝቀዝ ብላ።
ሚካኤሌም በእሺታ ጭንቅላቱን ነቅንቆ በአይነ ሱውሩ የሚመራበት ወደ መሬት
ወርውሮ በመዘርጋት ሊወጣ ሲል ሚጣ እጁን ይዛ አስቆመቺውና።
" እንዴ አንተ ወንድ ልጅ አይደለህም ? ... ምንድን ነው እንደ ቄጤማ
ልምጥምጥ የሚያረግህ ቆፍጠን ኮስተር በል የወንድ ወንድነቱ የሚታወቀው
ሴትም የምትወደው እንደዛ ሰትሆን ነው ወጣ እሺ ግባ እሺ ስትል አፍቃሪዋ
ሳይሆን የምትመስለው የበሯ ጠባቂ ነው ........ ለማንኛውም አንዴ እናቴን
ላናግራት እና እጠራሀለው ጠብቀኝ " ብላው እስከ በር ስትሸኘው የነገራትን
ልተነግራት መስሎት ያዝ ሲያረጋት እንዳልሆነ በአይኗ ነገረቺው እና አስወጥታው
በሩን ዘግታ ወደ እናቷ ስትዞር እናቷም አየቻትና ።
" ልጄ በሽተኛ እኮ ነኝ ልትደፊኝ ነው እንዴ?"አለች ሰርኬ
" እማ በሽታውን ለግልሽ ያሺው እኮ እኔም በሽተኛ እኮ ነኝ አንቺስ አቃጥለሽ
ልትደፊኝ ነው "አለች ወደ እሷ እየተጠጋች።
ቃል ኪዳን በአዲስ ገና እየተሰራ ፎቅ ላይ ሁኔታውን እየተዟዟረች ትመለከታለች
አድማሱ ተደብቆ ይከታተላታል ወደ ሁለተኛው ፎቅ ላይ ወጣች ዙሪያውን ዘወር
ዘወር ብላ ስትመለከት አድማሱ ከኋላ ይከተላት ነበር ። አንድ ጫፍ ላይ ተደብቆ
ጠበቃት ከትንሽ ቆይታ በኋላ እሷ ለማየት ስትመጣ ተደብቆ አያትና ተደርድሮ ሄዶ
ገፈተራት ከሁለተኛ ፎቅ ተወርውራ መሬት ላይ በተከመረ አሸዋ እና ድንጋይ ላይ
እየጮሀች ወደቀች ጩሀቷን ሰምተው ጥበቃው እየሮጡ መጡ አያትና
ደንግጠው ጮሁ። ..........
~~~~ ይቀጥላል ~~~~

@Kooblife
@Kooblife

For any comment
@Ethio96bot