Get Mystery Box with random crypto!

'ደህንነታችን ዘላለማዊ ነው' ደህንነታችን ዘላለማዊ ነው በሚለው ትምህርት ብዙውን ጊዜ የሚነሳው | ዛሬም ልጅ ነኝ 😊

"ደህንነታችን ዘላለማዊ ነው"

ደህንነታችን ዘላለማዊ ነው በሚለው ትምህርት ብዙውን ጊዜ የሚነሳው ተቃውሞ ይህ አስተምህሮ ሰዎች ድነታቸውን ስለማያጡ እንደፈለጉ እንዲኖሩ ፈቃድ ይሰጣል ወይንም በሀጥያት መኖር ይችላሉ የሚል ነው። ይህ ደግሞ ስናየው እውነት ቢመስልም መፅሀፍ ቅዱሳዊ አይደለም።
አንድ ሰው በእውነት በኢየሱስ ክርስቶስ ከተዋጀ ሀጥያትን ልምምድ ያደረገ ህይወት አይኖረውም።
መፅሀፍ ቅዱስ ደህንነት በፀጋ ብቻ፥ በእምነት ብቻ እና በኢየሱስ ክርስቶስ ብቻ እንደሆነ ይነግረናል።( ኤፌ ምዕ. 2)8፤ ጸጋው በእምነት አድኖአችኋልና፤ ይህም የእግዚአብሔር ስጦታ ነው እንጂ ከእናንተ አይደለም፤9፤ ማንም እንዳይመካ ከሥራ አይደለም።
ሰው በእውነት በኢየሱስ ክርስቶስ ባመነበት ቅፅበት ድኗል እንደገናም ደህንነቱም ዋስትና አግኝቷል። ነገር ግን አንድ ሰው ድነት በእምነት ነው የምንቀበለው ካለ በኋላ ፀንቶ ለመኖር መስራት አለብን ቢል ይህ መፅሀፍ ቅዱሳዊ አይደለም።
ጳውሎስ በገላቲያ መልዕክቱ
" እንዲህ የማታስተውሉ ናችሁ? በመንፈስ ጀምራችሁ አሁን በሥጋ ትፈጸማላችሁን? "(ገላትያ 3:3)
በእምነት ከዳንን ድነታችን ፀንቶ የሚኖረው እና ዋስትና የሚያገኘው
# በእምነት ብቻ ነው። ድነታችንን በራሳችን ጥረት ማግኘት አንችልም። ስለዚህ ድነታችንን በራሳችን ጥረት ማፅናትም አንችልም።
እግዚአብሔር ብቻ ነው ድነታችንን ማፅናት የሚችለው። ( ይሁዳ 24)
የእግዚአብሔር እጅ ነው ማንም እንዳይወስደን አጥብቆ የያዘን።( ዮሀንስ 10:28~29)
የእግዚአብሔር ፍቅር ነው ማንም ከእርሱ ሊለየን እንዳይችል የደረገው ( ሮሜ 8:38~39)
በዘላለም ዋስትና(ያለመጥፋት) ላይ የሚነሳ ማንኛውም ተቃውሞ ድነትን በሰው ጥረት እና አቅም የሚፀና እንደሆነ ማመን ነው።ይህ ደግሞ በፀጋ መዳን ከሚለው ጋር የሚጋጭ ነው። ምክንያቱም የዳንነው በኢየሱስ መልካምነት እንጂ በእኛ መልካምነት አይደለም።(ሮሜ 4:3~8)... ድነታችንን ለማፅናት/ላለመጥፋት የሙሴ ሕግ መጠበቅ ወይንም መስራት አለብን ማለት የኢየሱስ ሞት ለእኛ ሀጥያት በቂ ክፍያ አይደለም ማለት ነው።
# የኢየሱስ ሞት ግን ላለፈው ፥ላሁኑ እና ለወደፊቱ ሀጥያታችን የተከፈለ ከ በቂ በላይ የሆነ ዋጋ ነው። (ሮሜ 5:8 ;1ቆሮ 15:3 ; 2 ቆሮ 5:21)
ታዲያ ይህ ማለት አንድ ክርስቲያን እንደፈለገው መኖር ይችላል እና ድነቱን አያጣም ማለት ነውን?
መፅሀፍ ቅዱስ ለዚህ ጥያቄ መልሱ ክርስቲያኖች እነሱ እንደፈለጉ ሊኖሩ አይችሉም የሚል ነው።
ክርስቲያኖች አዲስ ፍጥረት ናቸው።( 2 ቆሮ 5:17)
ክርስቲያኖች የመንፈስ ፍሬዎች የሚገለጥባቸው ናቸው።( ገላ 5: 19~21)
ክርስቲያኖች ሀጥያትን እንደልምድ አርገው ሊኖሩ አይችሉም።( 1 ዮሀ 3:6~9)
ሐዋሪያው ጳውሎስ ስለዚህ ነገር ሲናገር ፥ ( ሮሜ ምዕ. 6)
1፤ እንግዲህ ምን እንላለን? ጸጋ እንዲበዛ # በኃጢአት_ጸንተን እንኑርን?
# አይደለም ።2፤ ለኃጢአት የሞትን እኛ ወደ ፊት እንዴት አድርገን በእርሱ እንኖራለን?
ስለዚህ የዘላለም ዋስትና የሀጥያት ፈቃድ ማለት አይደለም። የእግዚአብሔር ፍቅር በክርስቶስ ለሚያምኑ ለዘላለም እንደሚኖሩ የሚያረጋግጥ ዋስትና ነው።የእግዚአብሔርን ውድ የድነት ስጦታ ማወቅ እና መረዳት ለሀጥያት ፈቃድ ከመስጠት ጋር ምንም ግንኙነት የለውም።
( ሮሜ ምዕ. 6)14፤ ኃጢአት አይገዛችሁምና፤ ከጸጋ በታች እንጂ ከሕግ በታች አይደላችሁምና።15፤
የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና ሰላም ከእናንተ ጋር ይሁን!!

✞ድነት ያገኘ ሰው ✞
እውነተኛ አማኞች ያገኙት ድነት በምንም ሊጠፋ የማይችል እንደሆነና እማኞች በእግዚአብሔር ፀጋ እና ኃይል በቅድስና በመኖር እስከ መጨረሻ እንደሚድኑና ድነታቸውን የማጣት ፍርሃት እንደማይዛቸው ቃሉ ያስተምራል
ድነት የእግዚአብሔርም ነፃ ስጦታ ስለመሆኑ በተደጋጋሚ ይናገራል፡፡ ሰዎችም በክርስቶስ ከማመን በስተቀር ለመዳን የሚከፍሉት ወይም የሚሰሩት ስራ የለም፡፡
የተቀበልነው ድነት ዳግም ልደትን መፅደቅን ልጅነትን አስገኘልን። ቲቶ 1፡11 ሮሜ 6፡23፤2ጢሞ 1፡9) ይሁንና በዚህ አዲስ ህይወት የተጀመረው ድነትን በተለያዩ ምክንያቶች ሊታጣ ይችላል የሚለው ጥያቄ መመለስ አለበት ለዚህ መፅሀፍ ቅዱሳዊ መልስ ለመስጠት ከሁለት አቅጣጫ ማየት ግድ ነው።
የተቀበልነው ደህንነት ዋስታና
ከእግዚአብሄር አቅጣጫ ፡- የሰዎችን መልካምነት ግምት ውስጥ ሳያስገባ በቸርነቱ ድነትን የሰጠ እግዚአብሄር በጊዜ ሂደት የሰዎችን ባህርይ ተንተርሰን ሃሳብ በመለወጥ በነፃ የተሰጠውን ድነት መልስ አይወሰደውም ፡፡(ፊሊ 1፡6)
ከሰዎች አቅጣጫ ፡- በዳግም ልደት ህይወት የተለወጠ፤ በቅድስና እንዲያድግና ወደ ኋላ የመመለስ ፈተናዎችን እንዲያሸንፍ የሚያስችለውን የመንፈስ ቅዱስ ዕርዳታ በየእለቱ የሚያገኝ፣ክርስቶስ በአብ ቀኝ ሆኖ የሚማለድለት ሰው ይህን ሁሉ ድጋፍ ከእግዚአብሄር እያገኘ ጌታን ሊክድ ወይም በአመፅ ሊኖር አይችልም (ሮሜ 8፡31-39)፡፡
በመጨረሻም የዘላለም ህይወት የሚጠፋ ሕይወት አይደለም ፤የዘላለም ህይወት ያገኘ ሰው የዘላለምን ሞት አይሞትም፡፡ (ዮሐ 3፡15፣ ዮሐ 16፡34፣ ዮሐ 5፡24) ከሞት ወደ ሕይወት ተሸጋገር እንጂ ወደ ፍርድ አይመጣም፡፡ (አንድ ጊዜ የተሻገረ ሰው ተመለሶ ወደ ፍርድ አያመጣም (1የሐ 5፡10-13) 1ጳጥ 1፡3-5) ።
በጌታ በኢየሱስ በማመን የተወለደ ሰው ከተወለደ በኋላ አለመውለድ ወይም መሞት አይችልም፡፡ ዳግመኛ በመወለድ አዲስ ፍጥረት የሆነው ሰው ተመልሶ አሮጌ ፍጥረት ሊሆን አይችልም (1ጴጥ 1፡23) (ያዕ 1፡18) (ዮሐ 1፡3) (2ቆሮ 5፡17)፡፡
የድነታችን ዋስትና እና ጥበቃ
ያዳነን የዘላለም ህይወት በጸጋው የሰጠን እግዚአብሔር እስከ መጨረሻ ሊያድነንና መንግስቱን ሊያወርሰን የታመነ ነው (ሮሜ 8፡29-30) ፣1ቆሮ 1፡8-9 ፣ፊል 1፡6) ፡፡
እግዚአብሔር ከእርሱ የሚለየን እንዳይኖር ይጠብቀናል (የሐ 10፤1-7 ፤10፡28-29 1ጴጥ 1፡5 ፤ ዕብ 13፡20-21 ፤ሮሜ 8፡37-39 ፡፡
ሰውን የማዳን ኃላፊነት የእግዚአብሔር ሲሆን ከድነት በኋላ ድነቱን ጠብቆ የመያዝ በድነታችን መኖር የሰዎች ኃላፊነት ነው፡፡ እግዚአብሔር ድነታችንን ጠብቆ ለመያዝ የሚያስችለንን ፀጋ ሰጥቶናልና።
ድነትን ያገኘ ሰው ኃጢያት እየሰራ አይኖርም (ዮሐ 3፡4፣2ቆሮ5፡18፣ ኤፌ 2፡10)፡፡
ድነትን ያገኘ ሰው በተሰጠው በእግዚአብሔር ፀጋ ይኖራል (ሮሜ 12፤1-2፣ ርሜ 10፡1-3)
የፅድቅ እወነታዎች
እግዚአብሔር ልጁ ኢየሱስ ክርስቶስን በኛ ምትክ መስዋት በማድረጉ እኛ ነፃ ነን፡፡
ፅድቅ የሚገኘው በእምነት እንጂ በስራ አይደለም፡፡
እኛ የእግዚአብሄር ፅድቅ ነን፡፡ (2ቆሮ 5፡21)
ተገቢውን ቅጣት መቀበል የነበረብን እኛ ነበርን፡፡
ፅድቅ ዘላለማዊ እንጂ ጊዜአዊ ስጦታ አይደለም፡፡
በክርስቶስ ፀድቀናል
የፅድቅ አስፈላጊነት
# ሰው ሁሉ ኃጢተኛ በመሆኑ እና በራሱ ጥረት በእግዚአብሔር ፊት ተቀባይነትን ሊያገኝ ስላልቻለ፡፡
“በአንዱ ሰው አለመታዘዝ ብዙዎች ኃጢያተኞች እንደሆኑ እንዲሁ ደግሞ በአንድ መታዘዝ ብዙዎች ፃድቃን ይሆናሉ (ሮሜ 5፡19)፡፡

@lechrstos