Get Mystery Box with random crypto!

ሥጋት ያንዣበበበት የዶሮ እርባታ ..... የኢትዮጵያ ዶሮ አርቢዎች እና አቀናባባሪዎች ማኅበር መ | ኮኬት

ሥጋት ያንዣበበበት የዶሮ እርባታ .....

የኢትዮጵያ ዶሮ አርቢዎች እና አቀናባባሪዎች ማኅበር መንግሥት ለዶሮ አርቢዎች አፋጣኝ ድጋፍ ካላደረገ በቀጣይ ወራት አንድ እንቁላል ከ20 እስከ 30 ብር ሊሸጥ እንደሚችል አስታውቋል፡፡

የኮቪድ ወረርሽኝ ተከትሎ የሆቴሎች መዘጋት፤ በቅርቡ ደግሞ 'ተከሰተ' የተባለው የዶሮ በሽታ ሳቢያ በዶሮ እና ዶሮ ምርቶች ላይ እገዳ መምጣቱ አርቢዎች ምርቶቻቸውን ለማስወገድ ተገደው እንደነበር የማኅበሩ ሥራ አስኪያጅ አቶ ብርሃኑ ሚሊዮን አስታውሰዋል።

አብዛኛቹ የዶሮ አርቢዎች የባንክ ብድር ያለባቸው መሆኑን ያነሱት አቶ ብርሃኑ መንግሥት ጣልቃ ገብቶ ዘርፉን ከውድቀት ለማዳን የባንክ ብድር ማራዘሚያ እና የግብር እፎይታ እንዲሰጠን እየጠየቅን ነው ብለዋል፡፡

አርቢዎቹ ላሉበት ችግር አፋጣኝ ምላሽ የማይሰጥ ከሆነ  በርካታ የዶሮ እርባታዎች ሊዘጉ እንደሚችሉ ጭምር ነው የጠቆሙት። ይህን ተትሎ በሚፈጠረው የምርት ዕጥረትም እንድ እንቁላል ከ 20 እና 30 ብር ድረስ ሊሸጥ እንደሚችል ሥጋታቸውን ገልጸዋል፡፡

ስለ ጉዳዩ ማብራሪያ የተጠየቁት በግብርና ሚኒስቴር እንስሳት እና አሳ ሀብት ሥራ አስፈፃሚ ወ/ሮ ፅጌሬዳ ፍቃዱ ሚኒስቴሩ እስካሁን ከወራት በፊት ተከስቶ በነበረው የዶሮ በሽታ መከላከል ላይ ትኩረት አድርጎ ሲሠራ መቆየቱን ጠቁመዋል፡፡

በቀጣይ ድጋፍ የሚያስፈልጋቸውን አርቢዎች በመለየት ድጋፍ የሚያገኙበትን መንገድ አንደሚፈልግ ኃላፊዋ ጨምረው አንስተዋል፡፡ (Balageru Tv)

@tikvahethmagazine  @tikvahmagbot