Get Mystery Box with random crypto!

​​. ❦የልቤ ትርታ❦ ✼አሳዛኝ የፍቅር ታሪክ✼ | Kjphotoandmusic 🇪🇹

​​. ❦የልቤ ትርታ❦

✼አሳዛኝ የፍቅር ታሪክ✼

#ክፍል_6

... ጌድዮ መቅደስ የሱ በሽታ ተጋብቶባት ነው ካሉት ቡሀላ ሂወት አስጠልቶታል መኖር ሰልችቶታል በቃ ሰሞኑንማ በዚህ የተነሳ በሽታው ብሶበታል።....መቅደስ ግን ይህን የማይመስል ወሬ አልሰማችም ብትሰማማ ምንኛ ባዘነች ነበር ሆኖም አሁንም ከሱ አልተለየችም።
......ጌዲዮ ዶርም ውስጥ ሆኖ እንደለመደው እራሱን እየጠየቀ ብቻውን እያወራ ነው ለምን እማራለሁ? ማንን ልጠቅም? ማንን ልረዳ? ደግሞ እኔን ሰው ብሎ ማነው የኔን እርዳታ የሚፈልግ? ማንም ማንም የለም ማንም ከዛም ትምርቱን ለማቆም ወሰነ ቢሆንም ለራሱም የማይክዳቸው ሁለት እውነታዎች ከለከሉት አንድኛው ምክንያቱ መቅደስን አፍቅሯታል ሌላው አደራ አለበት አልቻለም በሁለት መንገድ ተጠመደ ከዛም ጮክ ብሎ መቅደስ ለምን አፈቀርኩሽ ለምን ቀረብሽኝ እያለ ይወቅሳት ጀመር ባዚህን ጊዜ ዶርም ውስጥ ማንም ባይኖርም በለጠው የተባለ የክፍሉ ተማሪ በር ላይ ቆሞ እየሰማው ነበር።
.......መቅደስ ስትወድቅ የተቦጫጨረው ፊቷ ሙሉ ለሙሉ ባይጠፋም አሁን ጤነኛ ነች ያው እንደተለመደው እሷ ሰአዳ ብርሀን ወይንሸት ሆነው ካፌ ቁጭ ብለው ሻይ ቡና እያሉ ነው ወይንሸት ፈፅሞ በፍቅር አታምንም እሷን የሚገዛት ገንዘብና መልክ ነው በዚህ ፀባይዋ ከሶስቱም ጋር አትስማማም በተለይ መቅደስ ሁሌ ሰው እንድትሆን ትመክራታለች እሷ ግን በቀኝ ሰምታ በግራ ታፈሰዋለች መጨፈር ሺሻ ጫት መቃም ከሹገር ዳዲዎች ጋር መውጣቱዋ የታወቀ ፀባይዋ ነው።እናም እየተጨዋወቱ እያለ ዮናስ እየተንጎባለለ መጣ...
ሁሉንም ሰላም ካላቸው ቡሀላ አብሯቸው ተቀመጠ ከዛም ግን ለምን ወጣ ብለን ምሳ አንበላም አላቸው ወይንሸት ተቅበጥብጣ እሺ አለች እነብርሀንም የግቢ ምግብ ስለሰለቻቸው ተስማሙ መቅደስ ግን ለመሄድ አልፈለገችም ቢሆንም በውለታ ስለታሰረች ፈገግ ብላ ጥያቄውን ተቀበለች።
.......ከዛም ይዟቸው ከግቢ ሲወጣ አሁንም ጌዲዮ አየ ዮናስ ተንኮሉ መቅደስ መቅደስን እየታከከ ነው የሚሄደው።ከጌዲዮ አጠገብ የነበሩ ሁለት ልጆችም አይተው ስለመቅደስና ስለዮናስ ማውራት ጀመሩ አንተ ግን መቅዲ ዮናስን አፈቀረችው አይደል? ... አረ አይመስለኝም ..ተው እንጂ ዮናስን እዚህ ግቢ የማታፈቅረው ሴት አለች ልትለኝ ባልሆነ...በርግጥ ቆንጆ የተባሉት ሁላ ያፈቅሩታል ግን እሱ የሚፈልጋቸው ግዜ ማሳለፊያ አይደል እንዴ?.....ባክህ መቅደስም ተከይፋበታለች ታስታውቃለች ጌዲዮ ለመስማት ተሳነው ከተቀመጠበትም ተነስቶ ወደለመደው ጫካ ሄደ ......
ዮናስ ምሳ ጋብዟቸው ሲያበቃ ለምን አንድ ሁለት እያልን ስንቀውጠው አናመሽም አላቸው ይህን ጊዜ ሰአዳ በሉ እኔን ሸኙኝ አለቻቸው መቅደስም አረ እኔም ጥናት አለብኝ አላመሽም አለች መቅደስ እንድትቀር ወይንሸትና ብርሀን ለመኗት እሷም አይሆንም አለች ከዛ ብርሀን መቅዲ ካላመሸች እኔም አልፈልግም አለች ከዛም በቃ ልሸኛችሁ ብሎ ወደ ግቢ ወሰዳቸውና ከወይንሸት ጋር ተመለሱ።
......ልክ እነመቅደስ ወደውስጥ ሲገቡ እነሱም መታጠፊያውን መንገድ ሲይዙ ወይንሸትና ዮናስ ተቃቅፈው እየተላፉ ሲላቸው እየተሳሳሙ መንገድ ጀመሩ ዮናስና ወይንሸት መቅደስ የማታውቀው ድብቅ ግንኙነት አላቸው ሁለቱም የጥቅም ሰው ስለሆኑ ይስማማሉ ባለፈውም መቅደስ የወደቀችው የጌዲዮ በሽታ ተላልፎባት ነው የሚለውን ወሬ ዮናስ ነው በወይንሸት አፍ ያስለኮሰው ምክንያቱም ሁለቱ እንዲለያዩ ይፈልጋል ዮናስ ጌዲዮንን በነገር ግቢውን ሊያስለቅቁት ለወይንሸት ብር ሰጥቶ አሳምኗታል።
......ይኸው በወይንሸት ስብከት በተደጋጋሚ ዮናስና መቅደስ እንዲገናኙ ሲገናኙም ጌዲዮ እንዲያይ እያደረገች ነው።
....ጌዲዮም የሚሰማው የመቅደስ እና የዮናስ የተቀናበረ የውሸት ፍቅር እውነት ነው ብሎ ሊቀበል እየተገደደ ነው።
....በተለይ ባለፈው አቅፎ ሆቴል ሲያስገባት ካየ ቡሀላ ትምርት በቃኝ እሷን እያየሁ ከምቃጠል ባቋርጥ ይሻለኛል ብሎ ከትምርቱ ሊሰናበት ወስኗል።
.........ጌዲዮ መቅደስን እንዳትጠጊኝ ስለኔ አይመለከትሽም ካላት ቀን ቡሀላ ዘወር ብላም እንዳላየችው ነው የሚያውቀው...አሁንም እራሱን ጠየቀ እውነት አፍቅራኝ ቢሆን አትንኪኝ ስላልኳት እኔን ትታ ሌላ ወንድ ጋር ባትሄድ ነበር አለ።
ከዛም ፍቅሯን መቋቋም ሲያቅተው ካይኗ ብርቅ ይሻለኛል ብሎ ትምህርቱን ሊሰናበት ወደደ መፅሀፎቹን ብቻ ሰብስቦ ለማንም ሳይናገር ወደ መጣበት ሊመለስ ግቢውን ለቆ ወጣ ልክ የግቢውን በር ሲያልፍ አደራ መብላቱን ፍቅሩን ማጣቱን አስታውሶ በቆመበት ወደቀ መቅደስም ከሩቅ አይታው እየሮጠች መጥታ በፊት እንደምታደርገው ክርቢት ምናምን አጭሳ ሰውነቱ ሲረጋጋ ሳይነቃ ልታመልጠው ልትነሳ ስትል አድርጎት የማያውቀውን ወዲያው ነቃ መቅደስ ውሀ ሆነች እንዳይመታት ሁለት ጉንጮቿን በእጆቿ ያዘች ተንቀጠቀጠች ጌዲዮ ግን በልቡ አይኖችሽ ስንቅ ይሁኑኝ ብሎ ፍዝዝ ብሎ አያት አይኖቹ እንባን አፈሰሱ መቅደስ ሳታውቅ ፍቅሯ ተሰናብቷት መንገዱን ቀጠለ መቅደስም ሁኔታው ግራ አጋብቷት ሳታውቀው በቆመችበት ባይኖቿ ሸኘችው...

ይቀጥላል...

ታሪኩ ቶሎ እንዲቀጥል VOTE አርጉ፡፡

❥.................. ⚘ ...................❥

ከወደዱት ሼር ያድርጉ

,,,,, ,,,,,
••●◉●••
Share:-@kjphotoandmusic