Get Mystery Box with random crypto!

​​. ❦የልቤ ትርታ❦ ✼አሳዛኝ የፍቅር ታሪክ✼ | Kjphotoandmusic 🇪🇹

​​. ❦የልቤ ትርታ❦

✼አሳዛኝ የፍቅር ታሪክ✼

#ክፍል_3

... በክፍል ሁለት እንደምታስታውሱት መቅደስና ዮናስ ካፌ ቁጭ ብለው እያወሩ ሳለ ነበር ጌዲዮ ባጋጣሚ መጥቶ አይን ላይን የተፋጠጡት....

.......መቅደስ ከመቀመጫዋ ተነሳች ጌዲዮም በነበረበት ቆሞ እሷን እያየ ጭንቅላቱን ያዘ መቅደስ በድንጋጤ ሙክክ ብላለች እንደው አይተው ሲገምቷት ባሏ ከሌላ ወንድ ጋር የያዛትን ሴት ነው የምትመስለው ጌዲዮ ሰውነቱን እንደማንቀጥቀጥ አደረገው ይህን ጊዜ ሊያመው እንደሆነ አወቀች መቼም መቅደስ የግቢው ቅፅል ስሟ የጌዲዮ የግል ነርስ ሆኗል በፍጥነት እየተንቀጠቀጠች ቦርሳዋን ከፈተች..... ዮናስ ምንም እንዳልተፈጠረ ምን ሆነሽ ነው እንኳን አላላትም ምክንያቱም ጌድዮን አይቶታል መቅደስም ቦርሳዋን ጠረንቤዛው ላይ ዘረገፈችው ይህን ጊዜ ዮናስ ብዙ ሴቶች ወደሱ እያዩ ስለነበር ሼም ያዘው ለመነሳትም አቃጣው መቅደስም በሚርበተበተው አንደበቷ ማማማ ማን ነበር ያያያ..ልከኝ...አ..ው..ዮ.ናስ.እእ..ባክህ..ክርቢት..ካካ..ለህ ይዤ ነነ.በር እ..ኮ.ጠፍኝ አለችው ዮናስም ከቦርሳዋ ከዘረገፈችው እቃ ወደ ክርቢቱ እያመለከተ ያውልሽ አላት መቅደስም ክርቢቱን ልታነሳ ስትቸኩል የብርጭቆውን ጁስ ዮናስ ላይ ደፋችበት ዮናስ በጣም ጮኸ ግን አልሰማችውም ይቅርታም ሳትለው ክርቢቱን ይዛ ወደ ጌዲዮ በረረች........

......ከዛም ህመሙ ሳይብስበት ክርቢቱን አጫጭሳ ሰውነቱን አረጋግታ ደግፋ ከወንዶች ማደሪያ በር ላይ አድርሳው ተመለሰች ስትመለስ ዮናስም ወደማደሪያው እየሄደ ተገጣጠሙ ከዛም በጣም ይቅርታ አለችው በርግጥ በሰአቱ ስትደፋበት ብዙ ሴቶች ቢስቁም የለበሰውን ቲሸርት ሲያወልቀው ግን እንኳን ደፋችበት ያሉት በዝተዋል የዮናስ ደረት ላይን ያሳሳል ለነገሩ ምን አለበት ከትምርቱ ይልቅ ለሰውነቱ ቅርፅ ሲል እስፓርትን ነው የሚወደው እናም ይቅርታ እንዳደረገላት ነግሯት በሌላ ጊዜም ተገናኝተው እንድትክሰው ቃል አስገብቷት ተለያዩ።

.......ቦርሳዋንም አስተናጋጇ አስተካክላ ስለጠበቀቻት ይዛ ወደዶርሟ ሄደች ግራ የገባት ግን የሷ መደንገጥ ሳይሆን የጌዲዮ እሷን ከሌላ ጋር ስላያት የህመሙ መቀስቀስ ነው እውነት ይወደኝ ይሆን ብላ አሰበች ደግማም አረ አይመስለኝም እያለች በሁለት ሀሳብ ተይዛ ብቻዋን ታወራ ጀመር።
......ጌዲዮም እንደልማዱ መፅሀፉን ይዞ ጋደም ብሎ በሀሳብ ተውጧል የዶርም ጓደኞቹም አንድ ላይ ቁጭ ብለው እያወሩ ነበር ጌዲዮም ከተለምዶ ውጪ ጮክ ብሎ አንድን ሴት ከሌላ ወንድ ጋር ስላየሀት ምን ያናድዳል ብሎ ጠየቃቸው ሁሉም በድንጋጤ ወደሱ ዞሩ ቀልዱን ነው እንዳይሉ ጌዲዮ እንኳን ሊቃለዳቸው የግዜር ሰላምታንም ሰቷቸው አያውቅም ከምሩንም ነው እንዳይሉ እሱ ስለሴት ከመቼ ወዲ ሲያስበው ነው ብለው ወደራሳቸው ሲመለሱ አሁንም መልሱልኛ አላቸው የሚመልሱት ጠፋቸው ከዛም አንድኛው ፎንቃ ይሆናላ አለው ጌዲዮም ምን ማለት ነው አለው ከዛም እንደምንም ተደፋፍሮ ፍቅር ይዞህ ይሆናል ታዲያ ፍቅር ያናድዳል እንዴ ሲላቸው እየውልህ ጌዲ አንተን ስለፍቅር ለማስረዳት ከሀ መጀመር አለብን ሲለው አንድኛው ጓደኛቸው እንደመሳቅ ብሎ ዝም ለማስባል በቁንጥጫ መዠለገው ልጁም ዝም አለ ጌዲዮም ወደ ሀሳቡ ተመለሰ።

........ከዛም በሌላ ቀን መቅደስን የሚያፈቅራት አስተማሪ ሆን ብሎ ጌዲዮን እንድጠላው ለማድረግ መፅሀፍ ላይ የሌለውን ስለሚጥል በሽታ አስከፊነት ጌዲዮን ምሳሌ አድርጎ ማስተማር ጀመረ። መቅደስ አበደች ክፍሉን ባንድ እግሩ አቆመችው አስተማሪው ላይ የስድብ ናዳ አወረደችበት
ተማሪው ሁላ ግራ ገባው የሷ ፍቅር እስከምን ድረስ ነው.....አስተማሪው እንደሚከሳት አሳውቆ ከክፍል አስወጣት ሄዋንም አብራት ወጣች ከወጡም ቡሀላ መቅደስ ግን ምን እየሆንሽ እንደሆነ ይታወቅሻል አለቻት መቅደስም አዎ ይታወቀኛል ሲጀመር ይህ ትምርት መፅሀፍ ላይ የለም ሲቀጥል አንድን አገር አቀፍ ጎበዝ ተማሪን ምሳሌ ማድረግ የለበትም በቃ ጌዲዮን ማንም በክፉ ሲያነሳው መስማት አልፈልግም ብላ እጆቿን እያወራጨች ማልቀስ ጀመረች ሄዋንም የምትላት ግራ ገባት በቃ አሁን አስተማሪውን ይቅርታ በይና ወደክፍል ግቢ አለቻት እሷም ይቅርታ ብላ ጮኸችባት እንደውም ብቻዬን ተይኝ ብላ እያለቀሰች ከዩኒቨርሲቲው ግቢ ወጣች.....

.....በንጋታውም ይህ ወሬ ተባዝቶ ጌዲዮ የተኛ መስሏቸው ጓደኞቹ ሲያወሩ ሰማ። ጌዲዮም ምንም ሳይል ከመኝታው ተነስቶ ወደሴቶች ማደሪያ ሄደ በር ላይም ብርሀንን አገኛት ከዚያም መቅደስን ጥሪልኝ አላት ብርሀንም በፍርሀት እየተንቀጠቀጠች ወደ ዶርም እሮጠች በሩን በርግዳ መቅደስ መቅደስ አለቻ እሷም አቤት ስትላት እያለከለከች ጌዲዮ በር ላይ ሆኖ እየጠራሽ ነው አለቻት መቅደስም የምትገባበት ጉድጓድ ጠፋት ቁጭ ብድግ ትል ጀመር ለነገሩ እንኳን እሷ ጓደኞቿም ደንግጠዋል ከዛ እንደምንም ተረጋግታ ሄደች ገና ፊትለፊቱ ስትቆም ጌዲዮ አይኑ እንባ አቅርሮ ነበር..

.....ከዛም ጮክ ብሎ ስሚ መቅደስ ከዚህ ቡሀላ ስለኔ ምንም አይመለከትሽም ብወድቅ ምንም ብሆን አንቺ አይመለከትሽም ገባሽ መቅደስም አይኗን በንባ ሞልታ ትሰማው ጀመር ...ቀጠለ በቃ እኔ መውደቅ አዲሴ አይደለም ማንንም አልፈልግም እንኳን የበሽተኛ ምሳሌ የፈለጉትን ያርጉኝ ጌዲዮ ባይኑ የሞላው እንባ እንደጎርፍ ይወርድ ጀመር ሁሉም ተማሪ ከሩቅ ሆኖ ያያቸዋል ከዛሬ ጀምሮ ወድቄ ስነሳ አጠገቤ ባይሽ እመታሻለሁ ስለኔ እንድትጎጂ አልፈልግም ብሏት እያለቀሰ ከግቢ ወጣ መቅደስም በቆመችበት ቦታ ተቀመጠች ጓደኞቿም መጡ አቅፈውም ያባብሏት ጀመር እሷ ግን ለቅሶዋ ጨመረ ቅስሟም ተሰበረ....

አንድ የነበረኝ ሰበብ አንተን ለማየት
ህመምክ ነበረ የሰጠኝ ብርታት:
ፍቅሬን ባልነግርክም ቁጡነትህ ከብዶኝ
መውደቅክ ነበረ መፅናኛ የሆነኝ:
ዛሬ ግን ጨክነክ አትደግፊኝ አልከኝ
አረ መላ በሉኝ ሰዎች ምን ይዋጠኝ:...

ይቀጥላል...



❥.................. ⚘ ...................❥

ከወደዱት ሼር ያድርጉ

,,,,, ,,,,,
••●◉◉●••
Share:-@kjphotoandmusic
በታሪኩ ዙሪያ comment አድርጉልን