Get Mystery Box with random crypto!

ቀና ለማለት ማጎንበስ አለብህ! ዛሬ የተወለደው ንጉስ ቤተመንግሥት መወለድ ይችላል ግን በበረት ተ | @king motivation💪✊

ቀና ለማለት ማጎንበስ አለብህ!

ዛሬ የተወለደው ንጉስ ቤተመንግሥት መወለድ ይችላል ግን በበረት ተወለደ፣ ከፍ ማለት ይችላል ግን በትህትና ዝቅ አለ፣ በነገስታት ተከቦ ሊወለድ ይችላል በከብቶች ተከቦ ተወለደ፣ አትርሳ ወዳጄ ሰማይና ምድር ያልፋሉ እሱ ግን አያልፍም!

በህይወት አንዳንዴ ቀና ለማለት ማጎንበስ አለብህ፣ ከፍ ለማለት ዝቅ ብለህ ማሳለፍ አለብህ፣ ብርሀን ያለው ህይወት እንዲኖርህ ጨለማውን ታግሰህ ማለፍ አለብህ፣ አሁንም አትርሳ ረጅሙን ሳቅ የሚስቀው በመጨረሻ የሚስቅ ሰው ነው፤ ወዳጄ በመጨረሻ ደግሞ አብረን እንደምንስቅ እርግጠኛ ነኝ። ምስክሬ የዛሬው ልደት ነው!

የሚገርም የገና በዓል ተመኘንላችሁ
@king_faf
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ!