Get Mystery Box with random crypto!

መንፈሳዊ ግጥም 'ተዋህዶ' የአምላክ ስጦታ የጥንቲቱ እምነት ሁሉንም በሁሉም የያዘች ሀይማኖት ከቃ | መንፈሳዊ ኪነ ጥበብ ብቻ

መንፈሳዊ ግጥም "ተዋህዶ"

የአምላክ ስጦታ የጥንቲቱ እምነት
ሁሉንም በሁሉም የያዘች ሀይማኖት
ከቃሉ ሳቶዎጣ ከትእዛዛቱ
ስንቱን አብቅጣለች ለክቡር መንግስቱ
የህይዎት ምሰሶ ሁሌም የምትቆም
ፀበልዋ እምነቷ ፈዋሽ ነው ለአለም
ተዋህዶ ብቻ እንከን የሌለባት
ዘላለም የምትኖር ፅኑ የኛ እምነት
የነቢያት ፅናት የሀዋርያት ትምህርት
ይፈልቃል ከውስጧ የጌታ ታምራት
የክርስቶስ ስብከት ፍቅሩ መሰረቷ
በደሙ የገነባት ስረአት ጉልላቷ
ሆኖላት አፀናት እስከዚህ ዘመን
ገና ያኖራታል እያየ በዓይን
ስጦታ ሰጥትዋታል እናቱን እንደ እናት
አማላጅዋስ ቢሆን መጠጊያ ሆናላት
አዕለፍ መላእክት ሁሌ ሚጠብቋት
የቅዱሳን ምልጃ ፍፁም ሳይለያት
ታምና ትኖራለች በፍቅር በፅናት
ይህቺ ተዋህዶ ነች ሀይማኖቴ
ሰው ያለፈለሰፋት የአምላክ ጥበቤ
በእናቴ እቅፍ የጌታ ልጅ አድርጋኝ
አጥምቃ አቁርባ ህይዎት የሰጠቺኝ
ብዝዎች ቢከድዋት ውለታዋን ረስተው
ቢሰድቧት ቢንቋት ቢያቃጥሏት ስቶው
ልጆችዋ በእምነት ለእሳ ተሰውተው
ሰማዕትነትን ተቀብለው ቆርጠው
መስቀሉን መሸከም ለእሱ ህይዎት መስጠትን ከኦርቶዶክስ ውጪ ማንስ ላይ አየነው ።
ቃሉን ስናነበው ይህ ሊሆን ግድ ነው
እውነተኛይቱን የሚመሰክር ነው
እስቲ ይሁን ግድ የለም ለጌታ ትቻለው
ትንቢቱም ይፈፀም መምጫውም ቅርብ ነው
ከጠባቢቱ በር እነሆ ገብተናል
መከራው ስቃዩ መቼ ያስቆመናል
መስቀሉን አንግተን ታቦቱንም ይዘን
ስንሞት ስንሰደድ ስንዎድቅ እንኖራለን
ይህንን ግዜ አምላክ በእውነቱ አየን
በብዙ መከራ ስቃይ ልጅ ተባልን
ፀንተ ደግሞ እንቁም በሀይማኖታችን
እንማር እንመስክር ዋላ ሳይረፈድብን
ሁሌ ማትጠፋ ማትታደሰውን
የሰጠ አምላካችን ክርስቶስ ይመስገን

በዚየን ጊዜ ለመከራ አሳልፈው ይሰጡአቸዋል ይገድሉአቹማል ስለ ስሜም በአህዛብ ዘንድ የተጠላቹ ትሆናላቹ የማትዮስ ወንጌል 24÷9
https://t.me/kinexebebe