Get Mystery Box with random crypto!

#ቅንጭብጭብ_ኢትዮጵያ . . #ከማስታዎሻየ_ማህደር!! . . #ሌላ_ዓለም!! (ክፍል አንድ) . . | ቅንጭብጭብ

#ቅንጭብጭብ_ኢትዮጵያ
.
.
#ከማስታዎሻየ_ማህደር!!
.
.
#ሌላ_ዓለም!!
(ክፍል አንድ)
.
.
.. ትናንት ህዳር 8/2015 ዓ.ም "አርባተንሳ" ክብረ በዓልን ልታደም ወደ ገጠራማው መንደር ካ'ንድ ወዳጄ በቀረበልኝ ጥሪ መሰረት ወርጀ ነበር። ወዳጀ ካለኝ ቦታ ደርሸ ካገኘሁት በኋላ ያው እንደተለመደው 'ቅርብ ነው ደርሰናል!' እያለ ሰፈር ለሰፈር ትንሽ ተጉዘን ከቤታቸው ደረስን የቤቱ ግቢ በላም በጥጃዎችና በእርሻ የተከበበ ነው። ግቢው በር ላይ የተቀመጡ ሰዎችን ሰላምታ ሰተን ወደ ቤቱ ዘለቅን.. የቤቱ አባወራ ከሳሎኑ ጥግ ይዘው ተቀምጠዋል..ቅድሚያ እርሳቸዉን ሰላምታ ሰተን በቤቱ ያሉ እንግዶችንም ጨበጥናቸው እና የበግ ቆዳ ከተጎዘጎዘበት መደብ ቁጭ አልን። ወዳጄ ቀልጠፍ አለና ወደ ኩሽናው ዘልቆ እህቱን ምግብ እንድታመጣ አዘዛትና "ክቡር ዘበኛ" እሚባለዉን ብርጭቆና በጆክ ጠላ ይዞ መቶ ከፊቴ ቆመ.. እኔም ከቤቴ እንደበላሁና ያው ጠላም እንደማልጠጣ በመናገር አስቤ የመጣሁት "ወተት ለመጠጣት!" እንደሆነ አስታወስኩት! ቢሆንም 'ካልበላህ ወተት የለም!' እሚል እይታ አሳይቶኝ ለራሱ ጠላዉን ቀድቶ ቁጭ አለ። በልቤም አንድ ቁርጥ አንስቼ እበላና ወተቴን እጠጣለሁ ብየ መጠበቅ ያዝኩ ታዲያ የወዳጄ እህት በሰሃን(ባቲ) የሰማይ ስባሪ እሚያክል እንጀራ በድንች በስጋ ወጥ ይዛ መታ አስረከበችኝ!! 'ኧረ በዝቷል ይተርፋል!' ብልም ሰሚ ስላላገኘሁ ወደ ወዳጄ አባት ፊቴን መልሸ 'አባት ይባርኩልኝ?' አላኳቸው(አክባሪ ለመባል) ምን ዋጋ አለው! 'ለወንድ አይባረክም! ዝም ብለህ ብላ!' ብለው ጨነገፉኝ። ኩርኩሜን ተቀብየ ከወዳጀ ጋር የቀረበልኝን ምግብ መብላት ጀመርኩ.. ወዳጄ ምግቡን አቋርጦ ወደ ኩሽናው ተወነጨፈና በግራም ሰሃን እርጎ ይዞ መጣና እንጀራዉን መሸከም ያቃታት ሰሃን(ባቲ) ላይ እርጎዉን አጥለቀለቀው.. በላየላይ የወረደዉን መና እያጣጣምኩ በላሁ.. ታዲያ በየ መሃሉ አባወራው በመገረም ለምን ጠላ እንደማልጠጣ እየደጋገሙ ይጠይቁኛል! እኔም የተለያዩ መልሶችን እነግራቸዋለሁ.. ወዳጄና እህቱም እንጀራና ወጥ እያመጡ ጨምር እያሉ ከድንች በስጋው ወጥም ከእርጎና ከንጀራዉም ይከምሩብኛል.. 'ኧረ በቃኝ!' ብልም የቤቱ አባዎራ ጨምሮ እንግዳቹ ሁሉ 'ትንሽ ብላ እንጅ!' እያሉ አጨናነቁኝ እኔ ግን ተሎ መሃላ ዉስጥ ገብቼ ድርቅ በማለት እጄን ታጠብኩና ቁጭ አልኩ..መቼም የገጠር ሰዎች እማይበላ እማይጠጣ አይወዱም።
.
.
ይቀጥላል..


Aman YTZ
@amanYTZ23

join and share
@YelbeDrset
@YelbeDrset

inbox me @amanYTZ23