Get Mystery Box with random crypto!

የሀገሯ ~ ገመገም ከጥርሶቿ ~ ግርግም፣ ሳቋ ~ ሲያፍገመግም ሳልፍና ~ ሳገድም። አማትሬ ~ | ቅንጭብጭብ

የሀገሯ ~ ገመገም
ከጥርሶቿ ~ ግርግም፣
ሳቋ ~ ሲያፍገመግም
ሳልፍና ~ ሳገድም።


አማትሬ ~ ባየው:
ተሰትረው ~ ኑረው
የቅርብ ሩቅ ~ ሆነው።


ኩንስንስ አመሏ
ጵስጡቂስ ጠረኗ
ኑረት አኳኃኗ፣

ዘንጠፍጠፍ እያለ
ቀልብ እያዋለለ፣


የገዛ ጥላዋ
ብርቅርቅ ገላዋ፣


ውልብ ይልብኛል.....
የድምጿ ሲርሲርታ
ያቃጭልብኛል።


እናማ......

ምናብ ሀሳብ ሲምስ
ሲያወጣ ሲመልስ፣


ጣዕሙን ሊያጣጥም
ምላስ ሲፈረጥም፣


እፀበሉ ግርጌ
ነጠላ አደግድጌ፣

ስለቴን ላስገባ
በእግዜሩ ሙሀባ፣

መጣሁ ከአድባርሽ
እቤተስኪያን ቅጥርሽ፣


የኔ እንዲያ መዋተት
ደርሶ መንከራተት፣

የኔ እንዲያ መውተረተር
ካንቺ ለመሰተር።


እነሆ አካሏን ጎብኝቶ ጠረኗን በምናቡ ምጎ ካጣጣመ በኃላ በዕውኑ አለም ፍለጋውን ማነፍነፉን ቀጠለ።


አንቺ ሆዬ ወዴት አለሽ?


ቅዱስ አርዮስ
የግማሽ ዓለም ጣኦት

።።።።። ።።።።።
t.me/kinchebchabi
t.me/kinchebchabi
t.me/kinchebchabi
t.me/kinchebchabi