Get Mystery Box with random crypto!

ስለ ቻናሉ ቅዱሱ ብልግና ቤት፡ በዓይነቱ ልዩ የሆነ፤ ወሲብ-ነክ መጣጥፎችን ግልጽ በሆነ ቋንቋ ለባ | ቅዱስ ብልግና

ስለ ቻናሉ
ቅዱሱ ብልግና ቤት፡ በዓይነቱ ልዩ የሆነ፤ ወሲብ-ነክ መጣጥፎችን ግልጽ በሆነ ቋንቋ ለባለጌዎችና ለጨዋዎች፣ ለዓይናፋሮችና ለዓይናውጪዎች፣ ዕድሜያቸው አስራስምንትና ከዚያም በላይ ለሆኑ ታዳሚዎች በሚመች መልኩ አቀናብሮ የሚያቀርብ፤ አስተማሪና አዝናኝ ቻናል!

ከወሲብ ጋር የሚዛመዱ ገለጻዎች፦ መታቀብ፣ መመርመር፣ መወሰን፣ መጠቀም። ድንግል፣ ሸርሙጣ፣ ጋለሞታ፣ ባለጌ፣ ጨዋ፣ ልክስክስ፣ አተራማሽ፣ ጭምት፣ ቀበጥ። ቂንጥራም፣ እምሳም፣ ቁላራስ። የቤት ልጅ፣ የቡና ቤት ልጅ፣ ልጃገረድ፣ ወንዳገረድ። የወር አበባ። አስገድዶ መድፈር፣ ጠለፋ፣ አንድ ካንድ፣ አንድ ከብዙ፣ ጋብቻ፣ ፍቺ። መብዳት፣ መበዳት፣ መባዳት፣ መበዳዳት። መነፋፋት፣ መጠባበስ፣ መጠባባት፣ መላላስ። ሹገር ማሚ፣ ሹገር ዳዲ፣ ማማሲታ፣ ባቢ፣ ነፍስ ነገር፣ ወርቅ ነገር፣ ቅምጥ፣ ውሽማ፣ የጭን ገረድ፣ ፍቅረኛ፣ ሚስት፣ ባል። ስትሬት፣ ጌይ፣ ሌዝቢያን፣ ባይ። ሄትሮ፣ ሆሞ፣ ትራንስ። የተቃራኒ ጾታ ግንኙነት፣ የተመሳሳይ ጾታ ግንኙነት፣ የተደበላለቀበት። ቡሽቲ፣ ሉጢ፣ ቀውጢ። ራስን በራስ ማርካት። ማስተርቤሽን። ግብረ ሥጋ፣ ግብረ ሶዶም፣ ግብረ መዳፍ፣ ግብረ አፍ፣ ግብረ ደረቅ። የላይ፣ የታች፣ የቅምጥ፣ የግልብጥ፣ የፍንድድ፣ የፊንጢጣ፣ የቁም፣ የጎን፣ የማንኪያ፣ 69። ኡህህህ፣ አህህህ፣ እህ … እምስ ሀገር ስታምስ፣ ቁላ አፈር ይበላል።

ወሲብ ይጥማል። ወሲብ ይሰለቻል። ወሲብ አይሰለችም። ወሲብ ይመራል። ወሲብ ማርማር ይላል። ወሲብ ሱስ ይሆናል። ወሲብ አደገኛ ነው። ወሲብ ቅዱስ ነው። ነገር ግን በባሕላችን ስለወሲብ በግልጽ መወያየትና ማውራት እንደ ነውር ይቆጠራል። ይህ ደግሞ ለወሲብ ያለንን ጉጉት (curiosity) ጨመረ እንጂ አልቀነሰም። በድብቅ ይበልጥ እንድናሳድደው አደረገን እንጂ እንድንርቀው ወይም እንድንጠላው አላደረገንም። በድብቅ ስለምናደርገው ብዙውን ጊዜ ለከፋ አደጋ እንጋለጣለን።

የሐይማኖት በባሕላችን የጎላ ሚና መጫወት ወሲብን ከሰይጣናዊ ሥራ ጋር እንድናያይዝ አስገድዶናል። በሐይማኖት መነጽር ወሲብ ቅዱስ አይደለም። ወሲብ ኃጥያት ነው—በተለይ ከሕጋዊ ጋብቻ ውጭ ከተፈጸመ። በሐይማኖታዊ ትምህርት ዕይታ ወሲብ ዘርን ከመተካት ያለፈ ጠቀሜታ የለውም። ወሲብን ከዘር መተኪያነት አብልጠው የሚመለከቱትን “ዝሙተኞች”፣ “አመንዝራዎች” እያለ ሐይማኖት ያወግዛቸዋል።

ከሐይማኖታዊ ትምህርት ዓላማዎች መካከል የሰውን ልጅ ፍላጎት (ወይም ስሜት) መግታት፣ መቆጣጠር መቻል ዋነኛው ነው። ኃጥዕን ከጻድቅ የሚለየው ለምድራዊ ፍላጎት ተገዢ መሆኑ ነው። ሐይማኖት እንዳማራጭ የሚያቀርበውን ሰማያዊ ደስታን መጎናጸፍ የሚፈልጉ ሰዎች፣ ምድራዊ ደስታቸውን ረስተው፣ ስሜታቸውን ገተው መኖር ሐይማኖታዊ ግዴታቸው ነው። ከዚያ ሰማያዊ ደስታ ከሚያደናቅፏቸው መሰናክሎች መካከል ተቀዳሚው ወሲብ ነው። ወሲባዊ ፍላጎታቸውን ማሸነፍ መቻል አለባቸው። አብዛኛው ኢትዮጵያዊ በዚህ ዓይነት ሐይማኖታዊ ትምህርት ተቀርጾ ያደገና ህይወቱ ከባሕልና ከሐይማኖት ጋር የተሳሰረ ስለሆነ ወሲብን እንደ ታቡ ማየቱ የሚያስደንቅ አይደለም።

ለነገሩ ተፈጥሯዊ ግዴታ በመሆኑ ወሲብን የሚጠላ አይገኝም። “ተሰናከልኩኝ”፣ “ሰይጣን አሳሳተኝ” እያለም ቢሆን የተመኘውን ሳይቀምስ እንቅልፍ አይወስደውም። በእንቅልፉ እንኳ ሳይቀር “ቢኩ እየገነፈለ” የሚያስቸግረውን ቤቱ ይቁጠረው። ማንም አጉል ጻድቅ ለመምሰል በይፋ ወሲብን ቢያጥላላም ከመጋረጃ በስተጀርባ የሚያደርገውን ግን አድራጊው ራሱ ነው የሚያውቀው።

በርግጥ ፈር የለቀቀ (ልቅ የሆነ) የወሲብ ባሕል ጥሩ አይደለም። ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ጤና-ነክ ቀውስን ሊያስከትል ይችላል። ከግብረገብም አንጻር ተቀባይነት የለውም። ነገር ግን በዚያው መጠን ግልጽነት የጎደለው ጨለማ የወሲብ ዓለምም የራሱ የሆነ ስነልቦናዊ፣ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጉዳት አለው። ለምሳሌ ለኤድስ መስፋፋት የጎላ ሚና ከተጫወቱት ምክንያቶች መካከል የግልጽነት ማነስ አንደኛው ነው።

እንደሚታወቀው አብዛኛው ኢትዮጵያዊ ስለወሲብ ከወላጆቹ ሳይሆን የሚማረው ከወላጆቹ ተደብቆ ነው። ወሲብን አስመልክቶ በአብዛኛው ኢትዮጵያዊ ቤተሰብ ደረጃ ውይይት ይካሄዳል ማለት ዘበት ነው። ሆኖም ስንቱ ልጅ ነው ተደብቆ የወሲብ ፊልም የሚያየው፣ የወሲብ ጋዜጣና መጽሔት የሚያነበው!? አሁንማ እድሜ ለኢንተርኔት ሁሉ በጁ ሁሉ በደጁ—የፈለገውን ጎልጉሎ እያወጣ ማየት፣ ማንበብ ይችላል። ባሕላችን ለወሲብ ያለው አቋም የከረረ ከመሆኑ የተነሳ ልጆቻቸው የፍቅር ልቦለድችን ጭምር እንዳያነቡ ጥረት የሚያደርጉ ቤተሰቦች ብዙ ናቸው። ይህም በቤተሰብና በሀገር ላይ የራሱ ጉዳት አለው። የወሲብ እንደ ታቡ መታየት ብዙ ወጣት ሴቶችን ላልተጠበቀ እርግዝናና ለተለያዩ በሽታዎች ያጋልጣል። ወንዶችም የጥቃቱ ሰለባዎች ናቸው።

በተጨማሪ በወሲብ አለመረካካት የብዙ ትዳሮች መፍረስ ተጠቃሽ ምክንያት ነው። ባሏ ያላረካት ሚስት በድብቅ ሌላ ወንድ ስትይዝ፣ ባልም በበኩሉ ሌሎች ሴቶችን ሲያተራምስ፣ መጨረሻ ላይ ነገሩ ሲጋለጥ ቤተሰባዊ ቀውስ ሲፈጠር ማየት የተለመደ ነው።

ወሲብ ትዳርን ወይም ወደ ትዳር ሊመሩ የሚችሉ ግንኙነቶችን ሊያጠናክር ይችላል። በፍቅር ግንኙነት ደረጃ ወንዱ መርካት እንደሚፈልግ ሁሉ የሴት ጓደኛውን ማርካት መቻል አለበት። ሴቷም ወንዱን ማርካት መቻል አለባት። አንዱ ወገን ረክቶ ሌላኛው ሳይረካ ሲቀር ችግር ይፈጠራል። አብዛኛውን ጊዜ ወንዶች የራሳቸውን ፍላጎት ካሟሉ በኋላ የሴት ጓደኛቸውን ፍላጎት ይረሱታል። ይህ ፍትሃዊ (ወይም fair play) አይደለም። በርግጥ የፍቅር ግንኙነት በወሲብ መረካካት ብቻ የሚለካ ባይሆንም ወሲብ ለፍቅር መሳካት የራሱን አስዋጾ ያበረክታል።

ወሲብ ጥበብ ነው። ተቀብሎ የመስጠት ጥበብ። ፈቃደኛነቱና ግልጽነቱ ካለ ይህንን ጥበብ ማንም ሊካነው ይችላል።

በዚህ ድረገጽ ወሲብን በተመለከተ ብዙ ነገር ለመዳሰስ ታቅዷል። የሚያስተምሩ፣ የሚያዝናኑ የወሲብ ታሪኮችና ቴክኒኮች በስፋት ይዘገባሉ። እነዚህ የወሲብ ታሪኮች፣ ምክሮችና ስልቶች ከተለያዩ ድረገጾች የተለቀሙና ለኢትዮጵያዊ ታዳሚ ይሆናሉ ተብለው የተተረጎሙ ናቸው። ከባሕላችን ወጣ ያሉ ሆኖም በስፋት (ግን በድብቅ) የሚከወኑ ወሲባዊ ልማዶችም ለንባብ ይቀርባሉ—ለምሳሌ የተመሳሳይ ጾታ ግንኙነት።

የተመሳሳይ ጾታ ግንኙነት በባሕላችን የሚነቀፍ ቢሆንም በአሁኑ ሰዓት በድብቅ በሀገሪቱ እየተስፋፋ መምጣቱን የተለያዩ የዜና አውታሮች ዘግበውታል። ከመጋረጃ ጀርባ የሚካሄድ ነገር ቢሆንም መጋረጃውን እየቀደዱ በነጻነት ሊኖሩ ወደሚችሉባቸው ሀገሮች የሚሰደዱ ብዙ ዜጎች እንዳሉን የሚታወቅ እውነታ ነው።

ኢተፈጥሯዊ ወይም ኢሞራላዊ ተደርጎ ስለሚቆጠር የተመሳሳይ ጾታ ግንኙነት በባህሪው እንደ ኢትዮጵያ ባሉ ሀገሮች ተቀባይነት የለውም። ነገር ግን ባሕልና ሐይማኖት እንደተጠበቁ ሆነው፣ ሰዎች (የየትም ሀገር ዜጋ ይሁኑ) ያለፍላጎታቸውና ያለተፈጥሯቸው በተቃራኒ ጾታ ግንኙነት ውስጥ ታስረው ሊሰቃዩ አይገባም። ስለሆነም ስለተመሳሳይ ጾታ ግንኙነት ምንነት ማወቅና መወያየት በሀገራችን ወይም በቤተሰባችን ውስጥ ሊከሰቱ የሚችሉ ወይም እየተከሰቱ ያሉ ቀውሶችን ለመቋቋም ይረዳል። በተለይ ሀገራችን ሙሉ በሙሉ ዲሞክራሲያዊት ስትሆን የግብረሶዶማውያን መብት አራማጆች በግልጽ መውጣታቸው አይቀርምና ከወዲሁ ስለ ተመሳሳይ ጾታ ግንኙነት መረዳት ከጉዳቱ ይልቅ ጥቅሙ የሚያመዝን ይመስላል።