Get Mystery Box with random crypto!

🌿🌷🕊ቤ࿆ ተ࿆ _ ማ࿆ ር࿆ ያ࿆ ም࿆ 🌿🌷🕊

የቴሌግራም ቻናል አርማ kidstarsema6 — 🌿🌷🕊ቤ࿆ ተ࿆ _ ማ࿆ ር࿆ ያ࿆ ም࿆ 🌿🌷🕊
የቴሌግራም ቻናል አርማ kidstarsema6 — 🌿🌷🕊ቤ࿆ ተ࿆ _ ማ࿆ ር࿆ ያ࿆ ም࿆ 🌿🌷🕊
የሰርጥ አድራሻ: @kidstarsema6
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.22K
የሰርጥ መግለጫ

👨‍🦳👨‍🦳👴👴የዱሮውን ዘመን ዐስብ፥የብዙ ትውልድንም ዓመታት አስተውል አባትህን ጠይቅ፥ያስታውቅህማል ሽማግሌዎችህን ጠይቅ፥ይነግሩህማል። ዘዳግሞ 32÷7👨‍🦳👨‍🦳👴👴

Ratings & Reviews

5.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

2

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-08-22 20:44:02 ላንተ ላንቺ ነው

አንድ አባት ሁሌ በቅዳሴ በኪዳን ሁሌ ቤተ መቅደስ ያገለግሉ ነበር። ከእለታት አንድ ቀን በምስጋና እንዳሉ በተመስጦ ቁጭ ብለው ያለቅሱ ጀመረ እንባቸው መሬት ጠብ..ጠብ አለ። ምእመኖቹ ጨነቃቸው ምን ሆነው ይሆን ብለው አዘኑ። መምህሩ ባፋቸው የሚሉት ነገር አላቸው። ጠጋ ብለው አደመጧቸው "
#ጌታዬ_ሆይ_እባክህ_ለቅዱስ_ስጋህና #ለክቡር_ደምህ_አብቃኝ" ነበር የሚሉት።

ምእመናኑ ተገርመው አባ ምነው ምን እያሉ ነው ብለው አፋጠው ያዟቸው። እርሳቸውም "አንተን ለማገልገል ለስጋና ለደምህ አብቃኝ" እያልኩ ነው። አሏቸው። ምእመኖቹም አባታችን ይህን ያክል ዘመን እያገለገሉ እንኳን ለርሰዎ እኛን እያቆረቡ እንዴት እንድህ ይላሉ አሏቸው።


እርሳቸውም "
#የመስቀሉ_ፍቅር_ገብቶኝ ለሰው ሳይሆን ለራሴ ብየ የማገለግልበት ስጋና ደሙንም ፍቅሩ ገብቶኝ የምቀበልበትን ቀን ነው የምለምነው" ብለው መለሱ።

ወዳጆቼ


ብዙ ጊዜ እንዲህ አይነት ክርስትና በየሰፈሩ አለ። ለስው የምንሰራ ወይም ግዴታ ተጥሎብን የምናገለግል ብዙ ነን። "አገልግሎት ማለት የፈቃደኝነት ባርነት ነው" እንዲሉ በእንዲህ መልኩ መጓዝ ሲገባን ሰው አይተን ጀምረን በሰው አገልግሎት ያቆምን ብዙ ነን። አንዳንዶቻችን፦ ቤተ ክርስቲያን መሄድ፣ መፆም፣ መስገድ፣ መፀለይ፣ መቀደስ፣ መዘመር፣ መስበክ፣ነጠላ መልበስ ግዴታ አልያም ህግ ነው ብለን የምንተገብር ብዙ ነን።
#መቼ_ነው_ግን_ፍቅሩ_ገብቶን_ስለፍቅሩ እነዚህን የምንተገብራቸው። ሰው ያየናል ይደረስብናል ብለን ሃጢአትን ከመስራት የምንከለከል ብዙ ነን።


አምላክን ፈርተን ሲኦል እንገባለን ብለን ክፉ ነገርን ሁሉ እንተዋለን። ግን ስለ ፍቅሩ ብለን ፍቅሩ ገብቶን ሃጢአት የሆነውን ሁሉ የምንተወው መቼ ይሆን? ወገኖቼ እየሰበክን እየዘመርን እያስቀደስንና እየቀደስን ያልዳን አለንና እርሱ ፍቅሩን ይሳልብን።።።። ሌላ ምንም አልላችሁም

https://t.me/betelhem29
https://t.me/betelhem29
https://t.me/betelhem29
92 views17:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-22 20:44:02
#ፍቅር_ከለለኝ_ከንቱ_ነኝ

#ሐዋርያው_ቅዱስ_ጳውሎስ

በሰዎችና በመላእክት ልሳን ብናገር #ፍቅር ግን ከሌለኝ እንደሚጮኽ #ናስ ወይም #እንደሚንሽዋሽዋ ጸናጽል ሆኜአለሁ።

ትንቢትም ቢኖረኝ #ምሥጢርንም ሁሉና እውቀትን ሁሉ ባውቅ

ተራሮችንም እስካፈልስ ድረስ እምነት ሁሉ ቢኖረኝ #ፍቅር ግን ከሌለኝ ከንቱ ነኝ።

ድሆችንም ልመግብ ያለኝን ሁሉ ባካፍል ሥጋዬንም ለእሳት መቃጠል አሳልፌ ብሰጥ #ፍቅር ግን ከሌለኝ ምንም አይጠቅመኝም።

ፍቅር ይታገሣል፥

ቸርነትንም ያደርጋል፤

ፍቅር አይቀናም፤

ፍቅር አይመካም፥ አይታበይም
የማይገባውን አያደርግም፥ የራሱንም አይፈልግም፥

አይበሳጭም፥ በደልን አይቆጥርም፤
ከእውነት ጋር ደስ ይለዋል እንጂ ስለ ዓመፃ ደስ አይለውም፤


ሁሉን ይታገሣል፥ ሁሉን ያምናል፥ ሁሉን ተስፋ ያደርጋል፥ በሁሉ ይጸናል።
ፍቅር ለዘወትር አይወድቅም።።።።


1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 13 ÷1_8

እግዚአብሔር ለሁላችንም ፍቅርን ያድለን ከዚህ ሌላ የሚያስፈልገን ነገር የለም።።
82 views17:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-18 18:47:55 የደብረ ታቦር ምሳሌነት

የወንጌል ምሳሌ ነው፡፡ ተራራ ሲወጡ በጣም ያስቸግራል፤ ከብዙ ድካምና ውጣ ውረድ በኋላ ተራራውን ጨርሰው ከላይ ሲወጡ ግን አባጣ ጎባጣውን ሜዳና ገደሉን ያሳያል፡፡ ወንጌልንም በሚገባ ከተማሯት ጽድቅን ከኃጢአት ለይተን እንድናውቅ ታደርገናለች፡፡

ለቤተ ክርስቲያን ምሳሌ ነው፡፡ በደብረ ታቦር ምስጢረ ሥላሴ እንደተገለጠ በቤተ ክርስቲያንም የቅድስት ሥላሴ አንድነትና ሦስትነት ይነገርባታል፡፡ ተራራ መሠረቱ ከመሬት አናቱ ከሰማይ እንደሆነ ሁሉ፤ ቤተ ክርስቲያንም መሠረቷ በምድር ሲሆን ራሷ በሰማይ ነው፡፡ የቤተ ክርስቲያን አገልጋዮቿ የተጠሩት ከምድር (ከዓለም) ሲሆን ክብራቸው ግን በሰማይ ነው፡፡ ቅዱስ ጳውሎስ ‹‹እኛስ ሀገራችን በሰማይ ነውና›› እንዲል /ፊልጵ. 3፥20/፡፡

የደብረ ታቦር ተራራ ይህን ሁሉ ምስጢር የያዘ በመሆኑ በክርስትና ታሪክ ትልቅ ቦታ አለው፡፡ ደብረ ታቦር ምሥጢረ መለኮት የተገለጠበት፣ ከዘጠኙ የጌታችን ዐበይት በዓላትም አንዱ ነው፤ በምእመናንም ዘንድ ቡሔ ይባላል፡፡


 ቡሄ

ቡሄ ማለት ብራ፣ ብርሃን፣ ደማቅ ማለት ነው፡፡ ጌታችን ብርሃነ መለኮቱን የገለጠበት በዓል የሚዘከርበት እና ለበዓሉም ችቦ ስለሚበራ የብርሃን በዓል በማለት የቡሄ በዓል እንላለን፡፡

ወቅቱ የክረምት ጨለማ አልፎ የብርሃን ወቅት፤ ሰማይ ከጭጋጋማነት ወደ ብሩህነት የሚለወጥበት፤ የመሸጋገሪያ ወቅት ነው፡፡ “ቡሄ ከዋለ የለም ክረምት፤ ዶሮ ከጮኸ የለም ሌሊት” እንዲሉ፡፡ በሌላ በኩልም “ቡኮ/ሊጥ” ተቦክቶ ዳቦ የሚጋገርበት “ሙልሙል” የሚታደልበት በዓል በመሆኑ ቡሄ ተብሏል፡፡


 ጅራፍ

 በደብረ ታቦር በዓል በትውፊታዊ መልኩ የሚታየው ምስጢር በኢየሩሳሌም ስለሚሆነው የጌታችን ምስጢራዊ ሞቱ ነው፡፡ ጅራፍ መገመድ እና ጅራፍ ማጮኽ ሁለት ዓይነት ምስጢር ይዞ የሚከወን ትውፊታዊ ተግባር ነው፡፡ የመጀመሪያው ግርፋቱንና ሞቱን እናስብበታለን፡፡ እንዲሁም ድምፁን ስንሰማ የባሕርይ አባቱን የአብን ምስክርነት ቃል፣ እንደ ነጎድጓድ ድምፅ ያስታውሰናል፡፡


ችቦ



 ችቦ የጌታችንን ብርሃነ መለኮት መገለጥ የሚያመለክት ነው፡፡ በመሆኑም ችቦ ለኩሰን በዓሉን እናከብራለን፡፡

https://t.me/betelhem29
https://t.me/betelhem29
 https://t.me/betelhem29
184 views15:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-18 18:47:55
ሙሴና ኤልያስ ለምን ተመረጡ

 #ሙሴንና_ኤልያስን ወደ ደብረ ታቦር እንዲመጡ ያደረገበት ምክንያት የባሕርይ አምላክ መሆኑን እንዲመሰክሩ ነው፡፡

ሙሴን ከመቃብር ተነሥቶ ስለጌታችን እንዲህ የሚል ምስክርነት ሰጥቷል፡-

“እኔ ባሕር ብከፍልም፤ ጠላት ብገድልም፤ ደመና ብጋርድም፤ መና ባወርድም እስራኤልን ከክፋታቸው መልሼ ማዳን ያልተቻለኝ ደካማ ነኝ፤ የእኔን ፈጣሪ እንዴት ሙሴ ይሉሃል? የሙሴ ፈጣሪ እግዚአብሔር ይበሉህ እንጂ!”

ኤልያስም ደግሞ ከብሔረ ሕያዋን መጥቶ

“እኔ ሰማይ ዝናብ እንዳይሰጥ ብለጉም፣ እሳት ባዘንብም፣ እስራኤልን ከክፋታቸው ማዳን የማይቻለን ነኝ እንዴት የእኔን ፈጣሪ ኤልያስ ነህ ይሉሃል? የኤልያስ ፈጣሪ እግዚአብሔር ይበሉህ እንጂ!” ብለው የባሕርይ አምላክነቱን በደብረ ታቦር ላይ መስክረዋል፡፡ በማቴ.16፡14 ላይ “አንዳንዱ መጥምቁ ዮሐንስ፥ ሌሎችም ኤልያስ፥ ሌሎችም ኤርምያስ ወይም ከነቢያት አንዱ ነው ይላሉ አሉት።” ይላልና፡፡

ሙሴና ኤልያስ የተመረጡበት ሌላው ምክንያት ሙሴ “ጀርባዬንም ታያለህ፤ ፊቴ ግን አይታይም”  ተብሎ ስለተነገረለት /ዘጸ.33፡23/ ኤልያስ “በኋለኛው ዘመን ምስክሬ ትሆናለህ” ስለተባለ ያንን ለመፈጸም ነው፤ ካገቡት ሙሴን ከደናግል ኤልያስ ያመጣቸው መንግሥተ ሰማያት በሕግ የተጋቡ ሕጋውያንና ሥርዐት ጠብቀው የሚኖሩ ደናግላን እንደሚወርሷት ለማስተማር ሁለቱን መርጧቸዋል፡፡

https://t.me/betelhem29
https://t.me/betelhem29
https://t.me/betelhem29
107 views15:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-18 18:47:55 አዕማደ (የምስጢር) ሐዋርያት ለምን ተመረጡ?

አዕማደ ሐዋርያት ተብለው የተጠሩት ጴጥሮስ፣ ያዕቆብና ዮሐንስ ናቸው፡፡ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ጴጥሮስ፣ ዮሐንስና ያዕቆብን “አዕማድ ሐዋርያት” እያለ ጠርቷቸዋል /ገላ. 2፥9/፡፡ ስያሜውን ያገኙበት ዋናው ምክንያት የኢየሩሳሌምን ቤተ ክርስቲያን በሓላፊነት ያስተባብሩ ስለነበረ ነው፡፡ ከዚህን በተጨማሪ ጌታችን በኢያኢሮስ ቤት ልጁን ሲፈውስ፣ በጌቴ ሴማኒ ሲጸልይና በደብረ ታቦር ምስጢረ መለኮቱን ሲገልጥ ከእሱ ስላልተለዩና ይዟቸው ስለሔደ ነው /ማር.5፥37-43/፡፡

ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን ሦስቱ ደቀ መዛሙርት የተመረጡበትን ምክንያት ሲያትቱ እንዲህ ብለዋል፡፡ ሦስቱ ደቀ መዛሙርት ሹመት፣ ሽልማትና ክብር ፈላጊዎች ነበሩ፡፡ ከዚህ ሃሳብ እንዲወጡ ከብልየታቸው እንዲታደሱ ለይቶ አውጥቷቸዋል፡፡ ቅዱስ ጴጥሮስ ለድኅነተ ዓለም የመጣው በሕማማቱ በሞቱ ቤዛ የሚሆነን አምላክ “#ልሰቀል_ነው ባላቸው ጊዜ “#አይሁንብህ” ብሎት ነበር፡፡ እንዲህ ያለው ሃሳብ የጠላት እንጂ የሰው ልጆች ሊሆን አይችልም ከሞቱ በቀር ድኀነት ሊያስገኝልን የሚችል የለምና፡፡ ደቀ መዝሙሩ ግን ከሞተ ክብሬ ምንድን ነው ብሏልና “አይሁንብህ” አለ፡፡ /ማቴ. 16/

በሌላም ስፍራ እንዲሁ “ሁሉን ትተን ተከተልንህ እንግዲያስ ምን እናገኝ ይሆን?” በማለት ይጠይቃል፡፡ /ማቴ.19/፡፡ ጌታ ግን ዋጋችሁ ሰማያዊ ክብራችሁ ዘላለማዊ ነው ሲል እስከ ፍጹማን መዓርግ /ነጽሮተ ሥሉስ ቅዱስ/ አድርሶ ብርሃነ መለኮትን ገልጦ ተስፋውን ነገራቸው፡፡

ሁለቱ ወንድማማች ደቀ መዛሙርትም #እናታቸውን_ልከው_ሹመት_ሽልማት መዓርግ ለምነዋል፡፡ ስለዚህም ጌታችን በደብረ ታቦር “በኢየሩሳሌም ስለሚሆነው ነገር” ስለሞቱ እንዲነጋገሩ አደረገ፡፡ ሞቱ እርግጥ ሆነ ማለት ነው፡፡ አባቱም “ኦሆ በልዎ ለክርስቶስ”፤ እሺ በሉት እርሱን ስሙት፡፡ ሞቱ እርግጥ በመሆኑ ከልባቸው እንዲጠፋ መርጦ ወደ ቅዱስ ተራራ ይዟቸው ወጥቷል፡፡

“እኔ እግዚአብሔር አልለወጥም” እንዲል /ሚል 3፥6/ በእርሱ ዘንድ ወረት የለም፡፡ አስቀድሞ ከተዓምራቱ ከምሥጢሩ አይለያቸውም ነበርና ብርሃነ መለኮትን ለማየት አበቃቸው፡፡ ደቀ መዛሙርቱም ለማወቅ፣ ለመማር፣ ለመጠየቅ ያሳዩት ትጋት ምስጢር ተገልጦላቸዋል፡፡ ይህ ምስጢር ለሦስቱ ደቀ መዛሙርት ተገልጦ የሚቀር አይደለም፡፡ እስከ ዓለም ፍፃሜ እግዚአብሔር ለመረጣቸው ሲገለጥ፣ በመረጣቸውም ሲነገር የሚኖር ነው፡፡

 ደቀ መዝሙሩ ጴጥሮስ “አልክድህም አልተውህም” የሚለው /ማቴ. 26፥35/ ቢወድደው አይደለምን? ፍቅሩን መግለጡ ለክብር አብቅቶታል፡፡ ሁለቱ ደቀ መዛሙርትም “ጽዋዬን ልትጠጡ አትችሉም” ቢላቸውም /ማቴ. 20፥22/ አንዳችን በቀኝ ሌላችን በግራ ሆነን አብረንህ እንሞታለን ሲሉ በምስጢር ለምነዋል፡፡ ሞታቸውን ከሞቱ ጋር መደመራቸው ፍቅራቸውን መግለጣቸው ነው፡፡

https://t.me/betelhem29
https://t.me/betelhem29
https://t.me/betelhem29
87 views15:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-18 18:47:55
#ደብረታቦር


ደብረ ታቦር ከገሊላ ባሕር በምዕራባዊ በኩል 10 ኪሎ ሜትር ርቆ የሚገኝ ተራራ ሲሆን፤ ከፍታው ከባሕር ወለል በላይ 572 ሜትር ይሆናል፡፡ በዚህ ተራራ ላይ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ብርሃነ መለኮቱን እንደሚገልጽ ምሳሌና ትንቢት ተነግሯል፡፡

ልበ አምላክ ቅዱስ ዳዊት በትንቢቱ “ታቦርና አርሞንኤም በስም ደስ ይላቸዋል” ብሎ የተናገረው ትንቢት እንዲፈጸም ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ተአምራቱን በዚህ ተራራ ላይ ገልጧል /መዝ. 88፥12/፡፡

ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ደቀ መዛሙርቱን በቂሳርያ “የሰውን ልጅ ማን ይሉታል?” ብሎ ከጠየቃቸው ከስድስት ቀን በኋላ አዕማድ ተብለው የሚጠሩ ሦስቱን ሐዋርያት ይዞ ወደ ረጅም ታቦር ተራራ ወጣ፡፡ በፊታቸውም ተለወጠ ፊቱም እንደ ፀሐይ በራ ልብሱም እንደ ብርሃን ነጭ ሆነ፡፡ እነሆም ሙሴና ኤልያስ ከእርሱ ጋር ሲነጋገሩ ታዩአቸው፡፡ ቅዱስ ጴጥሮስ መልሶ ጌታችን ኢየሱስን ጌታ ሆይ በዚህ መሆን ለእኛ መልካም ነው፡፡ ብትወድስ በዚህ ሦስት ዳስ አንዱን ለአንተ አንዱን ለሙሴ አንዱን ለኤልያስ በዚህ እንሥራ አለ፡፡ በዚህ ጊዜ ብሩህ ደመና ጋረዳቸው፡፡ ከደመናውም በእርሱ ደስ የሚለኝ የምወደው ልጄ ይህ ነው፡፡ እርሱን ስሙት የሚል ድምፅ ተሰማ፡፡ ሐዋርያት ይህንን ሰምተው የጌታችንን መለኮታዊ ክብር አይተው በፊታቸው ወደቁ እጅግ ፈርተው ነበር፡፡ ጌታችንንም ተነሡ አትፍሩም አላቸው፡፡ በዚህ መልኩ አምላክነቱን ገለጠላቸው /ማቴ. 17፥1-10/፡፡

https://t.me/betelhem29
https://t.me/betelhem29
https://t.me/betelhem29
82 views15:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-18 11:24:12
መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የሰውን ልጅ ማን ይሉታል ብሎ የጠየቀው ለምን ነበር ??


ሙሴና ኤልያስን ወደ ደብረ ታቦር እንዲመጡ ያደረገበት ምክንያት ምን ነበረ???

አዕማድ ተብለው የሚጠሩትን ሶስቱን ሐዋርያት ጴጥሮስ፣ያዕቆብ፣ ዩሐንስ ለምን ወደ ደብረ ታቦር ተራራ ይዞ ወጣ????

የጅራፉ፣ የሙልሙሉ፣ ምሳሌ ምንድነው????

ሁሉንም መልሱን ዛሬ ማታ ይጠብቁን።።

https://t.me/betelhem29
https://t.me/betelhem29
https://t.me/betelhem29
116 views08:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-17 18:04:24

127 views15:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-17 18:04:24

130 views15:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-16 06:08:28 #የፍልሰታ_ስጦታ!... እውነተኛ ታሪክ (...የፍልሰትዋ ተአምር...) ከቅርብ ዓመታት በፊት ነው! በግብፅ ይኖር የነበረው ወጣት ምንም እንኳን ገና በወጣትነቱ በትምህርት፣ ሃብትና ትዳር "የተሳካለት ሰው" የሚባል ቢሆንም ከጥቂት ቀናት በፊት ግን ይመካበት የነበረውን ትዳሩን ጥያቄ ውስጥ ገብቶበታል:: ባላወቀው ምክንያት የሚወዳት ባለቤቱ ከወገብ በታች ፓራላያዝ ትሆናለች:: እርስዋን…
147 views03:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ