Get Mystery Box with random crypto!

✞ ኪዳነ ምህረት እናታችን ✞

የቴሌግራም ቻናል አርማ kidanemihiret2116 — ✞ ኪዳነ ምህረት እናታችን ✞
የቴሌግራም ቻናል አርማ kidanemihiret2116 — ✞ ኪዳነ ምህረት እናታችን ✞
የሰርጥ አድራሻ: @kidanemihiret2116
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 899
የሰርጥ መግለጫ

✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟
ጺሆንን ክበቧት በዙሪያዋም ተመላለሱ(መዝ 97-12)
✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟

ግሩፓቸንን ለመቀላቀል 👇
@kidanemihiret212121

Ratings & Reviews

1.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

2


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-08-31 09:05:43 የሕይወት አጋሬን እንዴት ልምረጥ

“ፍቅር ይዞኛል” “አፍቅሬአለሁ” ማለት በብዙ ወጣቶች ዘንድ የተለመደ ነገር ነው፡፡ ወጣትነትወንዶች ሴቶችን ሴቶችም ወንዶችን ለፍቅር የሚመርጡበት እድሜ ነው፡፡ በወጣትነት ዘመንበተቃራኒ ጾታ መሳብ፤ የራስን ሰው ለማግኘት ጊዜ ወስዶ ማሰብና መጨነቅ የተለመደ ክስተትነው፡፡ መፈላለግ ተፈጥሮአዊ ቢሆንም ሁሉም ለቁም ነገር ነው ለማለት ግን አያስደፍርም፡፡ በዚህየተነሣ ወጣቶች ተቃራኒ ጾታን ለጓደኝነት የሚመርጡባቸውን ምክንያቶች በሚገባ ማወቅ አስፈላጊ ያቸው ነው፡፡ የተወሰኑትን ምክንያቶች በዚህ ትምህርት ለማየት እንሞክራለን፡፡

1. ወጣቶች የተቃራኒ ጾታ ጓደኛ የሚይዙባቸው ምክንያቶች
ሀ. ጓደኛ የለውም (የላትም) እንዳይባሉ፤
ለ. ሌሎች ሲይዙ በማየት፤
ሐ. ለሩካቤ ሥጋ ፍላጎት (ለዝሙት) (2 ሳሙ 13፡11)፤
መ. በፍቅር ስለወደቁ (ዘፍ. 34፡3)፤
ሠ. የትዳር ጓደኛ ፈልገው (ዘፍ. 29፡18)፤
ረ. ለቁሳዊ ጥቅም ብለው (መሳ. 16፡5)
ሰ. በፉክክር ስሜት፣ ሌሎችም ለማናደድ ሲፈልጉ ወ.ዘ.ተ፡፡

2. የሕይወት አጋርን የምንመርጥባቸው ደረጃዎች፡-ወጣቶች የፍቅር ጓደኛ መፈለጋችሁ ኃጢአት ሳይሆን ተፈጥሮአዊ እና ጤናማ ስሜት ነው፡፡ነገር ግን ይህን የተቀደሰ ፍላጎት ያለ ጊዜው፣ በተሳሳተ ምርጫ እና ጤናማ ባልሆነ ፍላጎት እንዳናበላሸው ጥንቃቄ ማድረግ አለብን፡፡ስለዚህ የሚከተሉትን መመዘኛዎችና ደረጃዎችን ማጤን ትክክለኛ ውሳኔ እንድንወስን ያስችለናል፡፡ እንዲሁም ያለጊዜው ባደረግነው ያልተገባ ግንኙት ወይምበተሳሳተ ምርጫችን እንዳንጸጸት ያደርገናል፡፡

2.1. አካላዊ ብቃት፦
ወንዶች ለአቅመ አዳም ሴቶች ለአቅመ ሔዋን መድረሳችንን፤ ሰውነታችን ሌላ ሰውን ለመቀበል የተዘጋጀ መሆኑን ማወቅ አለብን፡፡

2.2. መንፈሳዊ ብስለት፡-
በመንፈሳዊ ሕይወት ጠንካራ መሆናችንን እንዲሁም ከአንድ ክርስቲያን የሚጠበቅ መንፈሳዊብስለት እንዳለን ለማረጋገጥ ራሳችንን ማየት ተገቢ ነው፡፡ በሕይወታችን ወይም በኑሮአችን ሁሉእግዚአብሔርን እንደምናስቀድም፣ የጸሎት ሕይወታችን ምን እንደሚመስል፣ መጽሐፍ ቅዱስንየማንበብና ለቃሉ ያለንን ፍቅር፣ የመንፈሳዊ ሕይወታችንን ጥንካሬ … ወ.ዘ.ተ ያጠቃልላል፡፡

2.3. የኢኮኖሚ ብቃት፦
ፍቅር ሓላፊነት እና ተጠያቂነት ያለበት ግንኙነት ነው፡፡ ገንዘብ ለዚህ ዓለም ኑሮ አስፈላጊ ነገርነው፡፡ ስለዚህ ከራሳችን አልፈን ሌላ ሰው ማኖር እንዲሁም መንከባከብ የሚያስችል አቅም አለኝ ወይብለን ራሳችንን መፈተሽ አለብን፡፡ ለመተዳደሪያ የሚሆን በቂ ገቢ የሚያስገኝ ሥራ አለን ወይ? የሚለውን ጥያቄ በአስተማማኝ ሁኔታ መመለስ ይገባናል፡፡

2.4. የሥነ ልቡና ዝግጅት ፦
አንድን ሰው ለማፍቀር ከመነሣታችን በፊት ሥነ ልቡናዊ ዝግጅት ማድረግ አለብን፡፡ ፍላጎታችንን መመርመር፣ ሌላ ሰውን ለመቀበል የመንፈስ ዝግጅት ማድረግ፣ በስሜት ሳይሆንበእርጋታና በሰከነ መንፈስ ምርጫችንን ማጤንን አስፈላጊ ነው፡፡

ወጣቶች የሕይወት አጋራችሁን ስትመርጡ እነዚህ ከላይ የተዘረዘሩትን መመዘኛዎች ማሟላታችሁን አረጋግጡ፡፡ ፍቅር የከበረ የእግዚአብሔር ስጦታ መሆኑን ተገንዝባችሁ በስሜታዊነትየፍቅር ጓደኛ ከመምረጥና በኋላ ከመጸጸት ራሳችሁን ጠብቁ፡፡ ከክፉ የጎልማሳነት (የወጣትነት) ምኞት በመራቅና በመሸሽ እያንዳንዱን ጉዞአችሁን በእግዚአብሔር ቃል እየመረመራችሁ እናፈቃዱን እየጠየቃችሁ በመንፈስ የምትመሩ ሁኑ፡፡

https://t.me/kidanemihiret2116
61 views06:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-27 22:25:05
የሲኦልን
49 views19:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-27 22:22:01
51 views19:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-27 22:20:18
እመ አምላክ

@kidanemihiret2116
55 viewsedited  19:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-27 22:15:51
ንዒ ማርያም
57 views19:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-26 09:03:47 መጽሐፍ ቅዱስ እና የሕክምና ሳይንስ


ለወዳጆ ያጋሩ

ቻናሉን ለመቀላቀል


ኪዳነምህረት እናታችን
121 views06:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-25 08:32:59 አንዳንድ ጊዜ የእግዚአብሔር ቃል በመከራ ውስጥ ይመጣል

አንድ ሰው መፍትሔ የሌለው የሚመስል መከራ ሊገጥመው ይችላል። በዚህ ጊዜ የእግዚአብሔር ድምፅ መከራው የገጠመው ጥቂት ኃጢአቶችን ስለ ፈጸመ መሆኑን ከማስጠንቀቂያ ጋር ይነግረዋል። አንዳንድ ጊዜ ደግሞ ቃሉ ንስሓ ከገባህ መከራው ፍጻሜ ያገኛል እያለ ውስጡን ሲመክረው ይሰማል። ከዚህ በኋላ እግዚአብሔር ስለ ንስሓው ሲል ለሰውየው ይራራለታል።

የእግዚአብሔር ድምፅ አንድ ሰው ሲታመም ወይም እርሱ የሚወደው ሌላ ሰው ሲታመም ሊመጣ ይችላል። በዚህ ጊዜ እንዲጸልይ ወይም ስዕለት እንዲሳል የሚመክረውን ድምፅ ከውስጡ ይሰማል ይህ ድምፅ የእግዚአብሔር ድምፅ ነው።

የዮሴፍ ወንድሞች እህል ሊገዙ ወደ ግብጽ ከወረዱ በኋላ በዚያ ችግር ሲገጥማቸው እርስ በእርሳቸው እንዲህ በማለት ተነጋግረው ነበር “በእውነት ወንድማችንን በድለናል እኛን በማማጠን ነፍሱ ስትጨነቅ አይተን አልሰማነውና። ስለዚህ ይህ መከራ መጣብን።” ዘፍ. 42፥21። ከዚህ በኋላ ለዮሴፍ እንዲህ ብለውታል “ለጌታዬ ምን እንመልሳለን? ምንስ እንናገራለን? ወይስ በምን እንነጻለን? እግዚአብሔር የባሪያዎችህን ኃጢአት ገለጠ...” ዘፍ. 44፥16። ኃጢአታቸውን እንዲያስታውሱ ኀላም እንዲገሰጹ ያደረጋቸው የእግዚአብሔር ድምፅ ነው።

ነቢዩ ዳዊት የጌራ ልጅ በሆነው በሳሚ ሲሰደብ የእግዚአብሔር ድምፅ ውስጡን ስላለፈ ኃጢአቱ እየወቀሰው መሆኑን አዳምጧል። ስለሆነም በዙሪያው ለነበሩ ሰዎች “እግዚአብሔር ዳዊትን ስደበው ብሎታልና ይርገመኝ።” 2ኛ ሳሙ. 16፥10 በማለት በግልጽ ተናግሯል።

ረሀብና የመሬት መንቀጥቀጥ በዓለም ሲደርስ የእግዚአብሔር ድምፅ በመላው ዓለም ውስጥ ይሰማል። በዚህ ጊዜ የእግዚአብሔር ድምፅ የሚናገረን “ወደ እኔ ተመለሱ እኔም ወደ እናንተ እመለሳለሁ።” ሚል. 3፥7 እያለ ነው። ይህ ድምፅ በረሀቡ ወይም በመሬት መንቀጥቀጡ ጉዳት ለደረሰባቸው ሀገሮች የሚሆን የእርዳታ ጥሪ ለማሰማት ወይም ሌሎቹ ከእነርሱ ትምህርት በመውሰድ ንስሓ እንዲገቡ ለማድረግ ወይም ከእግዚአብሔር ጋር ለመገናኝት ዝግጅት እንዲያደርጉ ነው።

ስለዚህ ማንኛውም ዓይነት መከራ ውስጥ ስትገቡ ከውስጣችሁ ያለውን የእግዚአብሔር ድምፅ አድምጡት እርሱ ለእናንተ ሊነግራችሁ የሚወደው ምን እንደ ሆነ ታውቃላችሁና።

አብነ ሽኖዳ



https://t.me/kidanemihiret2116
166 views05:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-24 16:44:44 አናቀጸ ሲኦል
ለወዳጆ ያጋሩ

ቻናሉን ለመቀላቀል


ኪዳነምህረት እናታችን
184 views13:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-24 16:44:16 “ልጆቼ ፦ እግዚአብሄርን በእምነት በፀሎት እንሻው ከእኛ የጠፋ ገንዘባችንን ነቅተን ተግተን በብዙ ድካም እንድንሻው እንዲሁ ሃሳባችንን ወደ እግዚአብሄር ልናቀርብ ይገባናል ፤ ልጃችን ቢጠፋብን ፈልገን በቅርብ ያላገኘነው እንደሆነ ሃይላችንን በድካም ድካማችንን በሃይል የምንለውጥ አይደለንምን? የጠፋውን ልጃችንን ስለመፈለግስ እናገኘው ዘንድ የብሱን በእግር ባህሩን በመርከብ የምንዞር አይደለንምን? ፈልገንም ያገኘነው እንደሆነ ዳግመኛ እንዳይጠፋብን ለመጠበቅ እንተጋ የለምን? እንዲህ ከሆነ መሓሪ እግዚአብሄርን በእምነትና በፀሎት እንሻው ዘንድ ምን ያህል ይገባን ይሆን? እግዚአብሄርን ፈልጉት ነጋዴ ወርቅ ቢጠፋበት ወርቁን ያገኘው እንደሆነ ሁሉን ቦታ እንደሚፈልግ እንዲሁ እግዚአብሄርን ፈልጉት፤ እናት ልጇ ቢጠፋባት እስክታገኘው ድረስ አርፋ እንደማትቀመጥ እንዲሁ እግዚአብሄርን ፈልጉት እግዚአብሄርን እሹት ፈልጉት እስክታገኙት ድረስ በእምነት በፀሎት እሹት፡፡”

(ቅዱስ ዮሃንስ አፈወርቅ)
ቻናሉን ለመቀላቀል


ኪዳነ ምህረት እናታችን
183 views13:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-23 12:55:28
ገነት እና ሲዖልን
ትልቁ የቤተክርስቲያናችን መጽሐፍ
ራዕየ ማርያም እንደዘገበው እንመለከታለን።

ለብዙዎቻችን ሲዖልን ከመፍራት ይልቅ
ገነትን እንድንወዳት እና እንድንናፍቃት
የሚያደርግ ቪድዮ ነው።

ተጋበዙልን

ለወዳጆ ያጋሩ ምክንያቱም ብዙዎችን ከስተታቸው እናድናቸው ይሆናል

ቻናሉን ለመቀላቀል


ኪዳነምህረት እናታችን
352 views09:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ