Get Mystery Box with random crypto!

✮ً ̰̰̰̰̰̰̃̃̃̃̃̃ከዚህም ከዚያም TUBE✮ًٍٜ͜͡

የቴሌግራም ቻናል አርማ kezim_kezam — ✮ً ̰̰̰̰̰̰̃̃̃̃̃̃ከዚህም ከዚያም TUBE✮ًٍٜ͜͡
የቴሌግራም ቻናል አርማ kezim_kezam — ✮ً ̰̰̰̰̰̰̃̃̃̃̃̃ከዚህም ከዚያም TUBE✮ًٍٜ͜͡
የሰርጥ አድራሻ: @kezim_kezam
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 843
የሰርጥ መግለጫ

💗አሁን ጊዜው የፍቅር🌺 ነው ከእኛ ጋር አብራችሁ በፍቅር እየተደሰታችሁ እየተዝናናችሁ አብራችሁን ቆዩ🙏
🤔እናንተ ለፍቅር 💕 ያላችሁ አመለካከት ምንድነው?
የኔ ፍቅር 💟 ለእኔ ፍቅር ፀጋ ነው 💏
️4 ᴀɴʏ ᴄᴏᴍᴍᴇɴᴛ & ᴄʀᴏss ᴘʀᴏᴍᴏᴛɪᴏɴ📬
💞 @Emodish ❤ @kezim_kezambot
.
.
.
.
.
.
.
.
.
.
.
.
.
.
ትልቅ ነበርን ትልቅም እንሆናለን

Ratings & Reviews

2.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2021-12-28 22:20:01 ​ የአንደበቴ መዝጊያ

አልጋዬ ላይ ሁኜ ስለ አንች እያሰብኩ
የፍቅሬን መግለጫ ቃላት እዬመረጥኩ
በፍቅር ውቅያኖስ ገብቼ እየዋኜሁ
ብዙ ተፈላሰፍኩ በዝምታ ሰመጥኩ
የፍቅሬን መግለጫ ቃላትን አመረትኩ
አሁን አንችን ማግኘት መንገር ብቻ ቀረኝ
ልነግርሽ ወስኜ ከአልጋዬ ወረድኩኝ
የምትወጭበትን ሰአቱን አስልቼ
የምትገኝበት ቦታውን ገምቼ
ፍቅሬን ልገልፅልሽ ልነግርሽ መጣሁኝ
ደምሬ ቀንሸ ሒሳቤን ሰርቼ
በቅቤ ምላሴ ቁልፉን አላልቼ
ሳልሰብረው ልገባ ልብሽን ከፍቼ
ልክ እንዳገኘሁሽ እንደመጣሽልኝ
ልናገር ፈልጌ ቃላቶቹ ጠፉኝ
ብን ብሎ ጠፋ እንደ ወፍ በረረ
የአልጋ ላይ ሀሳቤ ቅዠት ሁኖ ቀረ
ገና አይንሽን ሳዬው መርበትበት ጀመርኩኝ
አንዳች ቃል መተንፈስ መናገር አቃተኝ
የአንደበቴ መዝጊያ ቁልፍ ሁነሽብኝ ።

ብርሃኑ ዘላለም
ከዚህም ከዚያም ከዚህም ከዚያም
ከዚህም ከዚያም
1.1K views༄᭄✮ًٍٜ͜͡𝐃𝐚𝐠𝐢 𝐃✮ًٍٜ͜͡𖣔ꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋ ᭄࿐, 19:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-12-28 06:36:55
ገብርኤል ገብርኤል ስለው ሰምቶ
መጣ ወደኔ ፈጥኖ
ሰንሰለቴን በጠሰው
የአንበሶቹን አፍ ዘግቶ
19
እንኳን አደረሳችሁ
1.1K viewsMerry G, 03:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-12-25 22:37:20 ​••○● ስደቢኝ_ግድየለም ●○••

ስደቢኝ ግድየለም አልቀየምሽም
ደደብ የማትረባ አህያ ነህ ቀሽም
ሲጠሉህ የማታውቅ እልም ያልክ ፋራ
ልክስክስም በይኝ አስቀያሚ ጭፍራ
ከፈለግሽ ደግሞ ደሀ ለቃቃሚ
ብትይኝ ግድየለም እባክሽን ስሚ
.
ከስድቦችሽ መሀል መልካሙን እያየሁ
ፋራ በመሆኔ እጅጉን እኮራለው
አህያ ላልሺኝ ደግሞ አንቺን ተሸክሜ
እስከዛሬ አለሁ ይሄውልሽ ህመሜ
.
ደሀ ነህ ብለሻል ደሀ ነኝ አውቃለው
ሀብታም ስላልሆንኩኝ አመሰግናለው
ምናልባት ግን ሆዴ.....
ገንዘብ ኖሮኝ እኔ በሀብቴ ብኮራ
ስድብሽን ሰምቼ እለይሽ ነ'በራ
ሁሉን ያጣ ሆኜ ብትይኝ ውዳቂ
እንደማልጠላሽ ግን አሁንም እወቂ፡፡


•○● ከዚህም ከዚያም ●○•
ከዚህም ከዚያም ከዚህም ከዚያም
996 views༄᭄✮ًٍٜ͜͡𝐃𝐚𝐠𝐢 𝐃✮ًٍٜ͜͡𖣔ꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋ ᭄࿐, 19:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-12-19 22:30:08 ​ መለያየት ማለት

እየው ትላንትና ከትላንትም በስቲያ
ያዩሽ ሰዎች ሁሉ ከእቅፌ ጉያ
ዛሬን ተራርቀን ብቻዬን ቢያዩኝ
ከድታዋለች ብለው ከንፈር መጠጡልኝ
እባክሽ የኔ ዓለም ፈጥነሽ ንገሪያቸው
ሴትን ማፍቀር እንጂ ማባበል አይችልም ብለሽ አስረጃቸው
ለእኔ እና ለአንቺ እኮ መለያየት ማለት
በሩቅ መፋቀር ነው ያለመተያየት
ያለመተያየት መፋቀርም ማለት
በምናልባት ተስፋ የምትቆም ሕይወት
ዘወትር ዘወትር ምናልባት
ምናልባት እያለች የምትኖር ሕይወት
በተስፋዋ መሀል ጥቂት ደስታ አላት
በተስፋችን መሀል መፋቀሩ ካለን
ናፍቆት አካል ገዝቶ እንተያያለን
ብለሽ ንገሪያቸው
ልቤና ልቡናው ተጣብቋል በያቸው
እንጂ በእኛ መሀል መለያየት ማለት
በሩቅ መፋቀር ነው ያለመተያየት
በሩቅ መሰማማት በድምፅ አልባ ቃላት

ገጣሚ ኤፍሬም ሥዩም


╔═══❖• •❖═══╗
@kezim_kezam
╚═══❖• •❖═══╝
4 any comment
@kezim_kezambot
❥❥________⚘_______❥❥
1.1K views༄᭄✮ًٍٜ͜͡𝐃𝐚𝐠𝐢 𝐃✮ًٍٜ͜͡𖣔ꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋ ᭄࿐, 19:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-12-16 22:26:31 ​​​​​​​​​​

ብልጡ ፍቅርሽ ሲያጃጅለኝ የጫርኩት


የውበት ዳርቻ
የአድማሷን መባቻ።
አንቺን የእኔን ጠሀይ
የተድላዬን ሰማይ።
ልስልሽ ፈለጌ
ምስልሽን አጣሁት
ከምስሌ አድርጌ።

ከስብዕናሽ ጠለል ከሀሳብሽ ከፍታ
አየሁኝ በሳቅሽ ጨረቃ ተከፍታ።
ጨረቃ ጨረቃ
ጨረቃ ጨረቃ
ያቺ ድንቡል ቦቃ
አንቺ ስትፈዢ ይሆን ምትነቃ?

አንቺ እንደሁ አትፈዢ
ከቶ አደበዝዢ
በመውደድሽ ሸጠሽ ታደርጊያለሽ ገዢ።

ያውም በሠላሳ
ያውም በሠላሳ

ክደሸ ስታበቂኝ ምንም እማልመስልሽ
በገደልሽኝ ቁጥር ሳትሞች ምሞትልሽ
በገፋሽኝ ቁጥር ሳትወድቂ ማነሳሽ
በሸጥሽኝ መጠን ልክ ለመክሰር ምገዛሽ
ይሁዳ ነሽ አንቺ እኔ ደግሞ ጌታሽ።

መልአኩ ስብሐት ባይህ

━━━━━━✦✗✦━━━━━━━
ምርጫዎ ስለሆነ እናመሰግናለን

አዘጋጅ፦ ከዚህም ከዚያም TUBE

➳➳ ከወደዱት ለሌሎች ሼር ያድርጉ
1.0K views✮ًٍٜ͜͡𝐍𝐨 𝐦𝐨𝐫𝐞✮ًٍٜ͜͡𖣔ꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋ, 19:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-12-15 21:30:45 ​••○● ቢታነፅ_ቢወቀር ●○••)

እኔም አንድ ሰሞን
ልክ እንደ ሰሎሞን
“ሁሉም ከንቱ ከንቱ ነፋስን መከተል”
ሳይጥሉ መታገል፣ ሳይከብሩ መባተል
አያልሁ አጨልሜ
በራሴ ለግሜ
እፈላሰፍ ነበር።

ከዚያ አንቺን አገኘሁ
በጓሮ በር በኩል፣ ሰሎሞኔን ሸኘሁ
መፈጠሬን ወደድሁ
ነፋስ አሳድጄ
አንድ ቆቅ አጠመድሁ
ከፀሐይዋ በቻች፣ ግልገል ፀሐይ ፈጠርሁ
ለኦናው አምፖሌ፣ ብርሃን አበደርሁ
ማቅ የነበረው ጨርቅ፣ ሸማ ሆኖ ቆየኝ
ከንቱ የነበረው፣ አንቱ ሆኖ ታየኝ።

ለካስ
ጠቢብ ሲያስተምረው፣ መከራ ቢመክረው
አካሉና ልቡ ቢታነፅ፣ ቢወቀር
ሰው አቅሙን አያውቅም፣ ካልወደደ በቀር።

በዕውቀቱ ስዩም

╔═══❖• •❖═══╗
@kezim_kezam
╚═══❖• •❖═══╝
4 any comment
@kezim_kezambot
❥❥________⚘_______❥❥)
949 views✮ًٍٜ͜͡𝐍𝐨 𝐦𝐨𝐫𝐞✮ًٍٜ͜͡𖣔ꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋ, 18:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ