Get Mystery Box with random crypto!

ጊዜ ህይወት ጊዜ በሚባል መለኪያ ተሰፍሮ ለሁሉም እኩል ተሰጥቷል። በቀን 24 ሰዓት በሳምን | የስኬት ሚስጢር

ጊዜ


ህይወት ጊዜ በሚባል መለኪያ ተሰፍሮ ለሁሉም እኩል ተሰጥቷል። በቀን 24 ሰዓት በሳምንት 7 ቀን በአመት 365 ቀናት ።

እያንዳንዷን ቀን እንደ ባንክ አካውንት አስበው ጊዜን ደግሞ እንደ ከረንሲ ( ገንዘብ) በጊዜ ማንም ደሃ ማንም ሃብታም የለም፤ ለሁሉም እኩል 24 ሰዓት ተሰጥቶታል።

በህይወት የሃብት ልዩነት የሚፈጠረው በጊዜ አጠቃቀም ልዩነት ነው።

ጊዜውን በአግባቡ ለተገቢው ተግባር የተጠቀመ የፈለገውን ና በህይወት አላማው ይኖራል። ጊዜውን በአግባብ ያልተጠቀመ ደግሞ በትችት ና በህይወት ሩጫ ( ሲደክም) ይኖራል።

ሽርፍራፊዋ ሰከንድ ከህወትህ ላይ ተሸርፋ የተሰጠችህ ናት፤ በአግባቡ ተጠቀምባት።

አሁን ማድረግ ለሚገቡህ ነገሮች ሁሉ: በኋላ፣ ነገ፣ ቀጣይ ሳምንት የሚቀጥለው ወር የሚባል ሰበባ ሰበብ አትስጥ ምክንያቱም ምድር ላይ ያለውን እጅግ በጣም ውዱን ጊዜህን እያባከንክ ነው።
ማድረግ ካለህ አሁኑኑ አድርገው።

ማድረግ ከሌለብህ ደግሞ ማድረግ የሌለብህን ነገር በማሰብ እንቁ ሃብትህን አታባክን።

መልካም ቀን