Get Mystery Box with random crypto!

#ሁለቱ_ልጃገረዶች           ክፍል ሦስት በመጀመሪያ ሙሽርነቷን በቅጡ ሳታጣጥም ባሏን | ጥበበ ሉቅማን/Luqman Tube ️️️

#ሁለቱ_ልጃገረዶች


          ክፍል ሦስት

በመጀመሪያ ሙሽርነቷን በቅጡ ሳታጣጥም ባሏን በሞት ተነጠቀች
እሁን ደግሞ ምንም ያህል እቅፏ ውስጥ አስገብታ ፍቅሩን ያላጣጣመችው ልጇ ከአጠገቧ ርቆ ሄዷል። በመሆኑም ሙሐመድ ከተወለደ በኋላ የነበሩትን ዓመታትም አሚና ያሳለፈችው ደስታ የሚባል ነገር እርቋት ነበር። ያም ሆኖ በመልካም ሁኔታ ከሚያድገው ጠንካራና ጤኖማ ልጅ  በተያያዘ ወደፊት የሚገጥማትን እጀግ ደስታ የሞላበትን ህይወት እያሰበችም ትፅናና ነበር፡፡ ከዚህም ሌላ በወቅቱ ምንም አይዞሽ የሚላት
ወገን የሌላት ብቸኛ ሴት ሳትሆን በባሏ ቤተሰቦች ከፍተኛ ፍቅርና ርህራሄ እየተሰጣት ከእነርሱው ጋር ተቀላቅላ የምትኖር መሆኗም ሐዘኗን እንድትረሳ ያደርጋት ነበር፡፡

እንዲያም ሆኖ ግን የሙሐመድ ሞግዚት ሕፃኑን በየጊዜው እናቱ
ዘንድ እያመጣች ታስጎበኛት ነበር። በነዚህ ወቅቶች ታዲያ ጨቅላው ሙሐመድ በሚያሳያቸው እንግዳ የሆኑ ባህሪያት ዘወትር የምትደነቀው ሞግዚቷ በየጊዜው የምትታዘባቸውን እውነታዎች ለእናቱ ታጫውታት ነበር። ሙሐመድ እርሷ ዘንድ ከመጣ በኋላ በጎቿና ግመሎቿ በእጥፍ መጨመራቸው ከአሁን ወዲያ ምንም ዓይነት የዱንያ ችግር ሊገጥማት እንደማይችል ሁኔታው ሁሉ እጅግ ተዓምር እንደሆነባት ሞግዚቷ ለአሚና ተርካላታለች፡፡ አንድ ቀን እንዲያውም ሕፃኑ ሙሐመድ ከቤት ውጭ እየተጫወተ ሳለ አንድ መላዕክ አጠገቡ መጥቶ ልቡን እንዳጠበለት የተነገራት መሆኑንም ለአሚና አውርታላታለች፡፡ አሚና እነዚህን ተዓምራት በሰማች ቁጥር ታዲያ ልቧ ከአካሏ የሚወጣ እስኪመስል ድረስ ይነጥራል፤ ወደ ልጃገረድነት የእድሜ ትዝታዎቿ በመንጎድም ገጥሟት
የነበረውን እንግዳ የሆነ ህልም ታስታውሳለች የዚያን ጊዜው ግራ
የሚያጋባ ህልም እውን እየሆነ መሆኑን በማጤን ታስባለች፡፡

ከአራት ረጅም ዓመታት ቆይታ በኋላ በህይወቷ ውስጥ አዲስ ስሜት ተፈጠረ፡፡ ዘወትር ትናፍቀው የነበረውን ልጇን በእቅፏ አስገባች፡፡ ከዚያን ጊዜ ጀምሮም ደስተኛ ሆነች። አሚና ለሙሐመድ ዘወትር ስለአባቱ ትተርክለት ነበር፡፡ እድሜው ስድስት ዓመት ሲሞላ አሚና ሙሐመድን ወደ የስሪብ ይዛው ሄደች፡፡ በዚያ የሚኖሩ ዘመዶቿን ጎበኘች ልጇም የአባቱን ቀብር እንዲያይ አደረገች፡፡ ነገር ግን ልጇን ይዛ ወደ መካ ስትመለስ ሌላ አዲስ ነገር ግን የሚያሳዝን የህይወት እውነት ተከሰተ። አሚና በሰላም ከወጣችበት መካ ሳትመለስ መንገድ ላይ ቀረች፡፡ በድንገት ህይወቷ አለፈ። ገና ይህንን  ምድር ሳይቀላቀል  አባቱን የተነጠቀው ሙሐመድ መቅመስ የጀመረውን የእናቱን  ፍቅርና እንክብካቤ በወጉ ሳያጣጥም እናቱንም አጣ። በዚህም የተነሳ የሙሐመድ የህይወት መንገድ በድጋሚ መንገዱን ለመቀየር ተገደደ። ሙሐመድ በአያቱ አብዱል ሙጠሊብ ጥበቃ ስር መኖር ጀመረ።

የአሚና አብሮ አደግና የልብ ወዳጅ የነበረችው ኸዲጃም የተለየች
ውጣት ነበረች። ገና ሕፃን ሳለች ጀምሮ የነገሮችን እውነታ የመከታተልና የማወቅ ጉጉቷ ከእድሜዋ የላቀ ነበር ሁልጊዜ አባቷ ከሌሎች ነጋዴዎች ወይም ወንድሞቿ ጋር የስራ ጉዳዮችን በማንሳት በሚወያዩበት ወቅት በአትኩሮት በመከታተል በአዕምሮዋ ትይዝ ነበር። አንዳንዴ እንዲያውም በዚህ ዓይነቶቹ አጋጣሚዎች በምትከታተለው ውይይት ውስጥ ሳይገቧት የሚቀሩና ግር የሚሏት ጉዮች ሲገጥሟት የመጠየቅ ልምድም ነበራት፡፡

በዚህ የማወቅ ጉጉቷና ፍላጎቷ ሁሌም የሚደነቁት አባቷ ታዲያ
የምትጠይቃቸውን ነገር ሁሉ በአግባቡ ነበር የሚያብራሩላት፡፡
ኸዲጃ በተለያዩ የህይወት ጉዮች ዙሪያ በምትሰጠው ጠቃሚ
ምክሮችና አዳዲስ ሀሳቦች የወጣትነትና የመጀመሪያ ባሏ አቡ ሐላልንም ያስደንቀው ነበር፡፡ ኸዲጃ በወጣትነት እድሜዋ ከመሰረተችው ትዳሯ የመጀመሪያዎቹ ዓመታት ሁለት ወንድ ልጆችን አፍርታለች። ያም ሆኖ ግን ባሏ አብሯት የቆየው ለተወሰኑ ዓመታት ብቻ ነበር። በህልፈተ ሞት ኸዲጃን ተሰናበታት፡፡

የመጀመሪያ ባሏን በሞት ያጣችው ኸዲጃ ያለባል የቆየችው እጅግ አጭር ለሆነ ጊዜ ብቻ ነበር። ከጥቂት ጊዜ በኋላ ሌላ ባል አገባች።
ሁለተኛው ባሏ አጢቅ እንደ እርሷ ሁሉ ሩህሩህ ልብ ያለው! ተመሳሳይ ፍላጎትን የሚጋራ ጥሩ ሰው ነበር፡፡ ኸዲጃም አዲሱ ባሏን በተለያዩ ጉዳዮች ማገዝን የዘወትር ተግባሯ አድርጋ ነበር አብራው የምትኖረው፡፡ ኸዲጃ ትዳር እንደመሰረተች በነበረው የመጀመሪያ ዓመት ላይ ሴት ልጅ ወልዳ እንኳ ባሏን በሥራ ከማገዝ የተቆጠበችበት ጊዜ አልነበረም፡፡ በሚኖራት ትርፍ ጊዜ ደግሞ ወደ ካዕባ በመሄድ ፀሎት ታደርግ ነበር። ኸዲጃና ቤተሰቡ በመተጋገዝ፣ በመተዛዘንና በደስታ ዓመታትን ካሳለፉ በኋላ ግን አንድ ፈተና ገጠማቸው። መካ ውስጥ ክፉ ወረርሽኝ ተከሰተ።

ብዙ ሰዎችም በወረርሽኙ ተይዘው ለበሽታ ተዳረጉ በወረርሽኙ ሳቢያ በርካቶች ሞቱ ያም ሆኖ በመድኃኒት እገዛ የተወሰኑ ሰዎች በሽታውን በማሸነፍ ህይወታቸውን ማትረፍ ተቻለ። የወረርሽኙን መከስት ተከትሎ ኸዲጃና ባሏ ሆስፒታል አቋቋሙ። በራሳቸው ወጪም ሐኪም ቀጥረውና የሚያስፈልጉ መድኃኒቶችን ገዝተው አያሌዎችን ከሞት ታደጉ፡፡ ባልና ሚስቱ በሆስፒታሉ የሚረዱ ታካሚዎችን በመንከባከብ ይሳተፉም ነበር። ጥቂት ቆይቶ ወረርሽኙ ከመካ ቢጠፋም የኸዲጃ የትዳር ጓደኛ አጢቅ ታመመ፡፡ እናም ሚስቱን ከሶስት ልጆች ጋር ጥሎ ሞተ። በዚህም የተነሳ ኸዲጃ በዋነኛነት በባሏ ይካሄድ የነበረውን የንግድ ሥራ ኃላፊነት መረከብ ግድ ሆነባት። ባሏ በህይወት በነበረበት ወቅት በሥራው እያገዘችው ስላሳለፈች ልጆቿ አድገው ኃላፊነቱን እስኪረከቡ ድረስ የንግድ ስራውን በራሷ አቅም መቀጠል አልከበዳትም ነበር፡፡ በአካባቢው ህብረተሰብ ዘንድ ሴት ነጋዴን ማየት የተለመደ ስላልነበር በመጀመሪያ ላይ አንዳንድ አሉታዊ አስተያየቶች ይሰነዘሩ ነበር፡፡ ቆይቶ ግን የኸዲጃን ነጋዴ መሆን እየለመዱትና እየተቀበሉት መጡ፡፡ ኸዲጃ የሚገጥሟትን መሰናክሎች በአግባቡ በማለፍ የባሏን መዋዕለ ንዋይ ተጠቅማ የንግድ ሥራውን በአጥጋቢ መልኩ መምራት ቻለች። ሴት ከመሆኗ ጋር የሚገጥሟትን ፈተናዎችንም እየተጋፈጠች አሳለፈች፡፡ ኃብቷን በባለቤትነት ለመያዝ በመቋመጥ ለጋብቻ ይቀርቡ የነበሩ የግለሰቦች ጥያቄዎችንም በትዕግስትና በብልሃት አሸነፈች፡፡ ኸዲጃ ከነበረችበት ሁኔታ ጋር በተያያዘ ግን አንድ ልትወጣው ያልቻለችው ነገር ገጥሟት ነበር፡፡ በዚያ ዘመን ሴቶች ለንግድ ሥራ ወደሌላ ሩቅ አገር መጓዝ አይችሉም ነበር፡፡ ኸዲጃ ለዚህ ሥራ ማድረግ የምትችለው ተወካይ መቅጠር ብቻ
ነበር። እናም ኸዲጃ ይህንን ስልት በመጠቀም ነበር የሩቅ አገር የንግድ ተግባሯን የምትፈፅመው። ሁል ጊዜ በየዓመቱ ወደሶሪያ በሚደረገው የነጋዴዎች ጉዞ ላይ እርሷን ሆኖ የንግድ ስራውን የሚያካሄድ ወጣት በመቅጠር ከነጋዴዎቹ ጋር አብሮ እንዲጓዝ ትልክ ነበር። ያም ሆኖ ግን ኸዲጃ በውክልና የምታካሄደው
የንግድ ተግባር ብዙውን ጊዜ አትረካም ነበር፡፡ ኸዲጃ እርካታውን ያጣችው ወጣት ወኪሎቿ ብልህነትና ብቃት ጎድሏቸው ስራውን በአግባቡ...