Get Mystery Box with random crypto!

#ሁለቱ_ልጃገረዶች #ክፍል_ሁለት ያም ሆኖ ግን በወቅቱ የሚታዩትን የተለያዩ ጥርጣሬ | ጥበበ ሉቅማን/Luqman Tube ️️️

#ሁለቱ_ልጃገረዶች

#ክፍል_ሁለት

ያም ሆኖ ግን በወቅቱ የሚታዩትን የተለያዩ ጥርጣሬዎችና
አለመግባባቶች የሚያስወግድ ብሎም አዲስ የእምነት መንገድን
የሚያመላክት ሌላ ነብይ ወደፊት ከአላህ(ሱ.ወ) ዘንድ ይላካል የሚል ተስፋ በብዙዎች ዘንድ ነበር፡፡ ታዲያ ይህ በብዙዎች አዕምሮ ውስጥ የሚዋልለው ተስፋ በአሚናህና ኸዲጃ ሀሳብ ውስጥም ዘወትር ይመላለሳል፡፡ እናም አሚና እና ኸዲጃ ይህንን ጉዳይ አንስተው በተነጋገሩ ቁጥር ወደፊት ይመጣል ተብሎ የሚጠበቀው የአላህ መልዕክተኛ በእኛ የህይወት ዘመን ውስጥ ይመጣ ይሆን? ይህ ነብይ በሚመጣበት ወቅት ምንኛ የተቀደሰ
ዘመን እንደሚሆን ማየት ያስቸኩላል፤ የሚጠበቀው ነብይ በዒሣ የነብይነት ዘመን እንደተስተዋለው ሰዎች እርስ በእርስ እንዲዋደዱና ፍፁም ቅን በሆነ መንፈስ እንዲመሩ ያደርጋል ልክ እንደሙሳ ሰዎች ልጆቻቸውን ጠንካራ ህግም ተግባራዊ ያደርግ ይሆናል፤ ወይም እንደ ኢብራም ሁሉ ከመግደል እንዲታቀቡና አንዱ ሌላውን ከመስረቅ እንዲቆጠብ የሚያስገድድ ሰዎች ለአንድ አምላክ ብቻ እንዲገዙና እርሱን ብቻ እንዲጠጉ ያስተምርም ይሆናል ግን ህዝቡ ጆሮውን ቢነፍገውስ? በማለት ያስቡ ነበር። ይህንንም ተከትሎ የከዚህ ቀደምቶቹን ነብያት አንቀበልም ከማለት አልፈው አንዳንዶቹን የገደሉ እምቢተኛ ህዝቦች የተከተላቸውን ቅጣት
በማሰብም ሁለቱ ልጃገረዶች በፍርሃት ይጨነቁ ነበር፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ ከብዙ ዓመታት በፊት አላህ ነብዩላህ ኑህን፣ ተከታዮቹን የተለያዩ ፍጡራኖቹንና እንስሳትን ከጥፋት ማዳኑን ያስታውሳሉ፤ ከዚህ አንፃር አላህ በእርሱ አንድነት የሚያምኑ ፍጡራኑን ከመርዳት ወደኋላ እንደማይል በማሰብ ይፅናናሉ፡፡

ከዕለታት አንድ ቀን አሚና በእንቅልፏ የገጠማትን እንግዳ የሆነ
ህልም ለቅርብ ወዳጇ ኸዲጃ ተረከችላት፡፡ አሚና በህልሟ ወንድ ልጅ መውለዷን፤ ልጁም አድጎ የአላህ ነብይ መሆኑን ነበር ያየችው፡፡ በሚያስደንቅ ሁኔታ በዚያው ሌሊት ኸዲጃም በተመሳሳይ እንግዳ ነገር ያለበትን ህልም አየች። ኸዲጃ የአላህ መልዕክተኛ ተደርጎ ከተላከው ሰው ጋር ጋብቻ መመስረቷን፤ ነብዩ የተላከበትን ዓላማ ለመፈፀም በሚያደርገው እንቅስቃሴ ውስጥ በሚገጥሙት የተለያዩ ፈተናዎች የበኩሏን ድጋፍ
ማድረጓን የሚያሳይ ህልም ነበር በእንቅልፏ ያየችው፡፡ ልጃገረዶች
በተለዋወጧቸው እንግዳ የሆኑ የህልም ክስተቶች ግራ ተጋቡ፡፡ ነገር ግን ከህልሞቹ ጋር በተያያዘ አንድ ልዩ የሆነ መልዕክት እንዳለ ውስጣቸው ነግሯቸዋል። እነዚህ ልጃገረዶች ልቦቻቸው የነገሯቸው እውነት ምን ይሆን? ኸዲጃ ለአቅመ ሄዋን ስትደርስ ወረቃ ቢን ነውፈልን ታገባለች በማለት ወላጆቿ ይናገሩ እንደነበር ኸዲጃ ታስታውሳለች። ያም ሆኖ ግን ወረቃ ትዳር የመያዝ እቅድ እንደሌለውና ህይወቱን መንኩሶ እንደሚያሳልፍ ገለፀ፡፡
ሁለቱ ልገረዶች ትዳር መመስረት የሚጠበቅባቸው ወቅት ደረሰ፡፡
ወላጆቻቸውም በጊዜው ተቀባይነት በነበረው ሥርዓትና ደንብ መሰረት ለእያንዳንዳቸው ይሆናሉ ያሏቸውን ባሎች መረጡ፡፡ በዚህ ወቅት ነበር በልጃገረዶቹ ህይወት ውስጥ እጅግ የተለየ ስሜት የተፈጠረው፡፡ህይወታቸው ወደ አዲስና አስደሳች የሆነ ምዕራፍ ተሸጋገረ። አሚና በማህበረሰቡ ዘንድ እጅግ የተከበሩ የነበሩትን የአብዱል ሙጠሊብ ልጅ አብደላህን አገባች። ባልንጀራዋ ኸዲጃ በበኩሏ ወጣት ከሆነው ነጋዴ አቡ-ሐላ ጋር በትዳር ተሳሰረች። ሁለቱም በመሰረቱት አዲስ ጎጆ እጅግ ደስተኛ ሆኑ።

ያም ሆኖ ግን ይህ የደስታ ህይወት ከአሚና ጋር ብዙም ሳይዘልቅ
በአጭሩ ተቀጨ፡፡ ገና ሙሽርነቱን አጣጥሞ ሳይጨርስ ለንግድ ስራ ሩቅ አገር የተጓዘው የአሚና ባል እንደወጣ ሳይመለስ ቀረ። መንገድ ላይ በድንገት ህይወቱ አልፋ የስሪብ ውስጥ ተቀበረ። አባቱ አብዱል ሙጦሊብ አሚናን ለማፅናናት ብዙ ጥረት አደረጉ፡፡ ስለልጃቸው ሚስት ህልምና ሀሳብ ጠንቅቀው የሚያውቁ ከመሆኑም በተጨማሪ የምትወልደው ልጅ አንድ ቀን ትልቅ ቦታ የሚሰጠው የተለየ ሰው እንደሚሆን እራሳቸው ጭምር ህልም አይተው ነበር፡፡

አሚና በባሏ መለየት ሳቢያ የተፈጠረባት መሪር ሐዘን ምንም ዓይነት መሻሻል ሳያሳይ ወራቶች ተቆጥረው ወንድ ልጅ ወለደች፡፡ ዐብዱል ሙጠሊብም ህፃኑን ሙሐመድ የሚል ስም አወጡለት፤ የሙሐመድን መወለድ ምክንያት በማድረግም ድል ያለ ድግስ አዘጋጁ፡፡ ሕፃኑ ያለአባት እንደሚያድግ ለማንም ግልፅ ነበር፡፡
በወቅቱ ጨቅላ ሕፃናት በተለይ የመጀመሪያ ዓመት እድሜያቸውን
በተጨናነቀና አቧራ በሚበዛባቸው ከተሞች እንዲያሳልፉ አይደረግም ነበርና ብዙውን ጊዜ ሕፃናቱ ወደባዲያህ ይላኩ ነበር፡፡ እናም የባዲያህ ሰዎች በጎቻቸውንና ግመሎቻቸውን ለመሸጥ ወደመካ በመጡበት ወቅት አሚናህ ለሕፃኑ ልጇ የምትሆንና ሐሊማ የተባለች ሞግዚት አገኘች፡፡ ሙሐመድም በረሃ ውስጥ ለምትኖረው ለዚህች የባዲያህ ሞግዚት ተሰጠ፡፡

ምንም እንኳ ገና የተወለደ ጨቅላ ሕፃንን ከእናት መለየት ለእናት
እጅግ የሚከብድ ቢሆንም ሕፃኑ ወደ ባዲያ መላኩ ጤናማ በሆነ የአየር ፀባይና በተረጋጋ አካባቢ እንዲያድግ እንደዚሁም በአካባቢ ህዝብ ዘንድ የሚነገረውን ትክክለኛ የአረብኛ ቋንቋ በአግባቡ እንዲለምድ የሚያስችለው በመሆኑ ለህፃኑ መልካም እድገት የተሻለ ነበር።





ል...