Get Mystery Box with random crypto!

የብዕር ጠብታ✍📒📖

የቴሌግራም ቻናል አርማ ketbeb_mender — የብዕር ጠብታ✍📒📖
የቴሌግራም ቻናል አርማ ketbeb_mender — የብዕር ጠብታ✍📒📖
የሰርጥ አድራሻ: @ketbeb_mender
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 2.24K
የሰርጥ መግለጫ

╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩╩═╝
💚 .....ታማኝነት በጥበብ መፅሐፍ ውስጥ
የመጀመሪያው 💛
ምዕራፍ ነው ! ❤️
✔️•═•••🍃🌺🍃•••═✔️
ለአስተያየት @Yetomah_Bot

Ratings & Reviews

4.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2021-09-24 20:26:39 ወግ ይድረሰኝ


ሚስት ፈልጉልኝ ቀበጥ - ቅብጥ ያለች፣
ለኑሮ ለፍቅር - ፍፁም የምትመች።

ሁሌ የማስብላት - እኔ ከ "እኔ" በላይ፣
ሳቅ ደስታዋን እንጂ - ክፋቷን የማላይ።

እኔም ልክ እንደ ሠው
መቼም ወጉ ደርሶኝ፣
እንደ ገጣሚዎች...
ፍቅርሽን አፍቅሬ - ሚዛን አሳንሶኝ፣


ላንቺ ያለኝን ፍቅር
ባለችኝ ወረቀት እንድሞነጫጭር
ቶሎ ነይ ሔዋኔ....
እስቲ ወግ ይድረሰኝ - ልግጠም ስለ ፍቅር


አልአዛር
@DONAY
ኦርያሬስ
፭ - ፲፪
፮:፳፪ ቀን...

@ilovvll
@ilovvll
1.8K views17:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-09-10 22:07:58
The last day of 2013

2014 የብርሀን ዘመን እንዲሆንልን
ችቦ በማብራት ምሽቱን አድምቀነዋል

ቢለማም ቢከፋም በፈጣሪ እርዳታ ለ አዲስ ቀን እና ለአዲስ አመት ልንበቃ ሰአታት ቀርተውናል

2013 ግን ስለይክ በእንባ ነው

#ግጥም_ቃና
@ilovvll
@ilovvll ቤተሰብ ይሁኑ
2.3K views19:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-08-31 19:03:25 ​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​ ♡:。.。 እዮሪካ 。.。:♡

ክፍል 23

ደራሲ - አብላካት



እኔም ከእነሱ መሀል እየነጠልኩኝ ማውራት ስለ ማልፈልግ አቤልንም ከዚህ በኋላ እኔን ብሎ እንዳይመጣ ነገርኩት.... ምክንያቱም ሳባን አውቃታለው ማናቸውም እንዲያዋሩኝ አትፈልግም እሱንም ከምታኮርፈው እኔው ብሸሽ ይሻለኛል። ሰዓቴን አመቻችቼ ስራዬንና ትምህርቴን እኩል ማስኬድ ችያለው። ገንዘቡ ያስፈልገኛል ሁሉም የእናቴን እጅ ነው እሚጠብቁት ሰርቶ እንኳን ይሄንን ልቻል እሚል የለም ሁሌም ብር ባስፈለጋት ቁጥር ከእንጀራ አባቴ ጋር መጨቃጨቋ ሰላሜን ይነሳኛል... አባቢ በህይወት እያለ ደልቶን ባንኖር እኔ እና እናቴ ግን የጎደለብን ምንም ነገር አልነበረም ምንም ሰርቶ ቢሆን እኔን ከጓደኞቼ እኩል እናቴንም ከጎረቤቶቿ አያሳንሳትም ነበር። ዛሬ ላይ ግን የየአማን እና የሊድያ የትምህርት ክፍያ ሲደርስ የወር አስቤዛ ሲያልቅባት ማጠፊያው ሁሉ ያጥራታል.....ለአንድ ለራሴ አላንስም ግን ደግሞ እናቴን በዚህ ሁኔታ እራስሽ ተወጪው ልላት አልችልም ፤ ገና ድሮ ለማግባት ስትወስን ትክክለኛው ሰው እንዳልሆነ ደጋግሜ ስነግራት የሷን ኑሮ ይኖሩላት ይመስል ሁሉም ጎረቤት የምን እራስ ወዳድነት ነው... ያንቺ አባት ከሞተ እናትሽ ህይወቷን አትኑር እንዴ እያሉ አፍ አፌን ይሉኝ ነበር....የኔ ፍራቻ ይሄ ነበር ዛሬ እናቴ ያለችበት ሁኔታ ለእሷ አይገባትም። ድሮ አግቢ አግቢ ብለው ገፋፍተው እዚህ መናጢ ላይ የጣሏት ሰዎች ዛሬ አንድ ኪሎ ሽንኩርት አይገዙላትም። ለምንድነው በሰው ህይወት ፈላጭ ቆራጭ እምንሆነው..... እናቴን የተመቀኘኋት ይመስል ሀሳቤን ሲያጣጥሉ ነበር አሁን ግን ብቻዋን ናት ያኔ ምን ነበር ያላችሁት ብዬ ዛሬ ላይ ብጠይቃቸው እርግጠኛ ነኝ መልሳቸው እሚሆነው ለሷ ብለን እንጂ አላስገደድናት ነው እሚሉኝ።

የኔን ህይወት እምኖረው እኔ ነኝ እናት እና አባቴ እንኳን የተሻለ እንዲገጥመኝ መመኘት እና መጥፎ እና ጥሩውን ሊነግሩኝ እንጂ ሊወስኑልኝ አይገባም.....የሰዎችን ሀሳብ አላጣጥልም እቀበላለው ግን ደግሞ ማንም የወሰነልኝን አልኖርም.... ነገ እኔ ብቸገር አብሮኝ እሚቸገር የለም እንዲህ አድርጊ እንዲህ ሁኚ ያለኝ ሁሉ ከንፈር ከመምጠጥ የዘለለ ምንም አያደርግልኝም። ውሳኔያችን ነጋችን ላይ ችግር እንደማይፈጥር ቆም ብለን ማሰብ አለብን ሰው ስላለን ስላበረታታን ብቻ የነሱን ሀሳብ ተቀብለን መተግበር የለብንም ባይ ነኝ። ፈረስ ያደርሳል እንጂ አይዋጋም ሰውም በል በል ብሎ ከመሀል ያደርስል እንጂ አብሮ አይዘልቅም።

ከክላስ በኋላ ወደ ስራ ሄጄ ስራዬን ስጨርስ ማይለፍ እራት ጋብዞኝ ደስ የሚል ጊዜ አሳለፍን....ወደ ቤት ሸኝቶኝ ሲመለስ ሊድያን ከሆነ መኪና ስትወርድ አየኋት። ሰውየውን እንደምንም ለማየት ስሞክር በእድሜ ገፋ ያለ ሰው ነው....ሹገር ዳዲ እሚባለው አይነት.... ለተራ ገንዘብ ብሎ እራስን ክብርን እንደ መሸጥ ምን ውርደት አለ ..... አንዳንዴ እንደ እህት ብትቀርበኝ እና ይህ ነገር እንደማይጠቅማት ብነግራት ብዬ እመኛለው.....እራሷን ስታጣ ዝም ብዬ መመልከቴን ሳስብ ክፉ የሆንኩ ይመስለኛል....ምንም ቢሆን የእናቴ ልጅ ናት ክፉዋን ማየት መስማት አልፈልግም። መኪናው ከሄደ በኋላ ወደ ግቢ ልትገባ ስትል እጇን ያስኳት....

"ያምሻል እንዴ አስደነገጥሽኝ እኮ! ምንድነው ?" አለችኝ...
"ማነው ሰውየው ?" አልኳት....
"ማንም አደለም ደሞ ማንስ ቢሆን ምን ያገባሻል!?"
"እሱ እኮ አባትሽ ይሆን ገና ልጅ እኮ ነሽ ለምን እንደ እድሜ አትሆኚም !"
"እራስሽን እንደ ታላቅ እህት ቆጥረሽ እየተቆጣሽኝ ባልሆነ ። ትሰሚኛልሽ የፈለኩትን ከፈለኩት ሰው ጋር መሆን እችላለው ይሄ አንቺን አይመለከትም " አለችኝ.....
"እዮልሽ ሊድያ ከዚህ እምታተርፊው እራስን ማጣት ነው እባክሽን እንደዚህ መሆንሽን አቅም"
"ነገርኩሽ እማይመለከትሽ ነገር ውስጥ ጥልቅ አትበይ። ምነው አንቺ ከዚህ የተሻለ ውሎ እምትውዪ አስመሰልሽው ከማንም ጋር ስትልከሰከሺ አደል እንዴ እምትውይው!" ብላ ንግግሯን ልትቀጥል ስትል ገፍትሬያት ወደ ውስጥ ገባሁኝ።



ይቀጥላል....

ቀጣዩ ክፍል 100 ሲደርስ ይለቀቃል እያነበባችሁ አስተያየታችሁን አድርሱኝ...


ለአስተያየት - @Yetomah_Bot


✯┄┅┅✿❀ ❀✿┅┅┄✯
@Ketbeb_Mender
@Ketbeb_Mender
✯┄┅┅✿❀ ❀✿┅┅┄✯
3.0K viewsedited  16:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-08-26 09:09:06 ሆዴን ጅብ በበላው፣
አንጀቴን ባራሰው፤
የማያገኘውን እንዴት ይመኛል ሰው?

#የግጥም_ቃና

@ilovvll
@ilovvll ቤተሰብ ይሁኑ

ሰናይ ግዜ
2.6K views06:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-08-17 20:23:21 ​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​ ♡:。.。 እዮሪካ 。.。:♡

ክፍል 22

ደራሲ - አብላካት


ወደ ቤት መሄድ እያስጠላኝም ቢሆን እራት ልጋብዝሽ ሲለኝ እምቢ ብዬ ቤቴ አደረሰኝ። ተሰናብቼው ወደ ውስጥ ገባሁኝ....እናቴን በረንዳው ላይ ቁጭ ብላ ሳያት እሮጬ ሄጄ እግሯ ስር ተደፋሁኝ....

"ምነው ልጄ ምን ሆንሽ ?" አለችኝ
"ይቅርታ አድርጊልኝ እናቴ አጥፍቻለው አንቺ መምታትሽ ልክ ነበር"
"ልጄ እኔ እኮ አንቺን መምታት ቀርቶ በሙሉ አይኔ እንኳን ለማየት እምሳሳልሽ እንቁ ልጄ ነሽ...እኔ እማቃት ልጄ ከባለጌ ጋር የምትመላለስ ተራ ሰው አደለችም...አንቺ ለራስሽም ለሰውም ክብር ያለሽ ጨዋ ነሽ....ማንም እየተነሳ የንግግር መርዙን በረጨብሽ ቁጥር መልስ እየሰጠሽ ከሄድሽ ትጎጂብኛለሽ ብዬ እንጂ እኔ ለነሱ ወግኜ አልነበረም። ያም ሆኖ ግን መምታት አልነበረብኝም እኔንም ይቅር በይኝ"
" አይ እናቴ አንቺ ልክ ነሽ በሰዓቱ ይቅርታ ማለት አይጠበቅብሽም" ብዬ ጉልበቷን ሳምኳት...
"በይ አሁን እራት ሰርቻለው እንግባና ላቅርብልሽ" ብላኝ ወደ ውስጥ ገባን....ሰላም ተሰማኝ እድሜ ለአባ ያዕቆብ ....አንዳንዴ ስናጠፋ እሚያርመን መንገድ ሲጠፋን እሚመራን ሰው ከጎናችን መኖሩ አንድም እንዳንወድቅ አንድም እንዳንስት ይረዳናል። እናቴ ያቀረበችልኝን እራት በልቼ ለነገ ለትምህርቴ እሚያስፈልገኝን ነገር ለማዘገጃጀት ወደ ክፍሌ ገባሁኝ። ነገ እነ ሳባን ሳያቸው ምን ሊሰማኝ እንደ ሚችል ሳስብ ግን ውስጤ ተረበሸ....ግን ደግሞ እነሱ የራሳቸውን ውሳኔ ከወሰኑ እኔም ነገሮችን ችላ ብዬ ማለፍ እንዳለብኝ አባ ያዕቆብ ነግረውኛል። እቃዎቼን እያስተካከልኩኝ ስልኬ ጠራ ይስሐቅ ነበር..... ከሁሉም ይበልጥ በእሱ ነው የተናደድኩት ከማንም በላይ አስተዋይ እና ለነገሮች እማይቸኩል ነው ብዬ እማስበው እሱን ነበር ዛሬ ግን ሊሰማኝ እንኳን ፍቃደኛ አልነበረም። አንዳንዴ ሰዎች ባሰብንበት አይውሉም.....በተቃራኒው ለሳቢ ይወግናል ብዬ እማስበው አቤል ከእኔ ጎን ነበር። በእርግጥ ሁላችንም እርስ በእርስ ያለን ፍቅርም ክብርም እኩል ነው.... ማንም ማንንም አያስበልጥም ቃላችንም ይሄ ነበር ነገር ግን ዛሬ.....ብቻ ይሁን እስቲ ሁሉም እሚሆንበት የራሱ ምክንያት አለው። እቃዬን አስተካክዬ ስጨርስ ለማይለፍ ደወልኩለት...ምን ልለው እንደሆነ ግን አላውቅም ብቻ ግን ውስጤ ደውዪለት የሚል ስሜት ስለተሰማኝ ነው የደወልኩት።

"ሰላም አመሸሽ ቃልዬ ?"
"ይመስገን። እንዴት አመሸህ ?"
"ደህና ነኝ አልተኛሽም እንዴ ?"
"አይ እቃ እያስተካከልኩኝ ነበር። ለቀኑ ላመሰግንህ ፈልጌ ነው የደወልኩት ከረበሽኩ ይቅርታ"
"አይ አልረበሽኝም እንደውም ድምፅሽን ስለ ሰማሁኝ ደስ ብሎኛል። ምስጋናም አያስፈልግም"
"እሺ በቃ ይሄንን ለማለት ነበር ጠዋት ስለምነሳ ልተኛ ሰላም እደር"
"እንዳልሽ ሰላም እደሪልኝ እወድሻለው" ....የሆነ ነገር ልቤ ላይ ተሰማኝ ደስ አለኝ
"እኔም እወደሀለው ቻው" ብዬ ስልኩን ዘጋሁት። ለምን እየፈራሁት እንደሆነ ባላውቅም ግን መውደዴን አልጠራጠርም። ላጣው አልፈልግም ከእሱ ጋር ስሆን ሰላም ይሰማኛል ሌላ አለም ውስጥ እንዳለው አድርጌ ነው እምቆጥረው። መልካም ሰው ነው ንፁህ ልብ አለው ፤ የአብዛኛው ሴት ምርጫ ነው። እወደዋለው አዎ የኔ እንዲሆን እፈልጋለው ምናልባትም ማለት ካለብኝ አፈቅረዋለው ግን ደግሞ እንዳላጣው እፈራለው...... ብቻ እስቲ አሁንም ስለ ሁሉም ነገር ፈጣሪ ያውቃል። በጠዋት ለመነሳት ብዬ ተኛሁኝ። ሊነጋጋ ሲል እንደመባነን አልኩና ከእንቅልፌ ነቃሁኝ በመስኮት በኩል ጀምበሯን እያየሁ እራሴን ለማነቃቃት ሞከርኩኝ ልብሴን ለባብሼ ከክፍሌ ስወጣ....ሳሙኤል ፊት ለፊት ቆሟል.... በውስጤ በቸር አውለኝ አልኩኝ። ላልፈው ስል እጄን እንደመያዝ አለ....ወደ ኋላ ሸሸት እያልኩኝ....

"ምነው ?" አልኩት
"ብር ፈልጌ ነበር" ...አለኝ። አለማፈሩ ገርሞኝ ትክ ብዬ አየሁት
"እና እኔ ጋር አስቀምጠሀል እንዴ ለምን እኔን ትጠይቀኛለህ ?"
"ለማዘር አንቺ ብር እንደምትሰጫት አውቃለው ስለዚህ ቢኖርሽ ነው እና ለኔም እንድትሰጪኝ ነበር አታስቢ እሚመለስ ነው" .... የአንዳንድ ሰው አይናውጣነት ግን ለከት የለውም የታንሽ ታናሹ ሆኜ ከእኔ ብር ሲጠይቅ ከዛም አልፎ እኔን ለመስደብ ላይ ታች እሚል ልጅ ዛሬ ሲቸግረው እኔ ጋር መምጣቱ ያስገርማል ኧረ ያበሳጫል...
"እኔ ምንም ብር የለኝም። ይቅርታ እረፍዶብኛል" ብዬው ወጣሁኝ.....የግቢው ብር ጋር ስደርስ...
"ኧረ እንደዚህ ነው ያገናኘናል ጠብቂ" አለኝ.... አሁን ከሚያደርገኝ የከፋ ምን ሊያደርግ ፈለገ። ምንም መልስ ሳልሰጠው ከግቢ ወጣሁኝ..... አንዳንድ ሰዎች አስፈላጊነታችን እሚታያቸው ቀን ሲጎድልባቸው ነው። ለስራ አለቃዬ ክላስ ከመግባቴ በፊት መደወል እንዳለብኝ ትዝ ሲለኝ ደወልኩለት....

"ሰላም አደርክ ስዩም ?"
"ደህና ነኝ። እንዴት አደርሽ ?"
"ፈጣሪ ይመስገን። ይቅርታ ስዩም ቀድሜ መንገር ነበረብኝ ግን እኔም ትላንት ነው ያወኩት ዛሬ ትምህርት እጀምራለው እና ስራውን ምን ማድረግ እንዳለብኝ ልጠይቅህ ነበር"
"አታስቢ አቶ ማይለፍ ትላንትና አሳውቆኛል። እናም ስራሽን ከትምህርት እንደወጣሽ መተሽ መስራት ትችያለሽ።" አለኝ......
"እእ እሺ ስዩም አመሰግናለሁ። መልካም ቀን" ብዬ ስልኩን ዘጋሁት። ማይለፍ ለኔ ብሎ እሚያደርግልኝ ነገር ሁሉ ከቀን ቀን እየጨመረ ነው...ባዘንኩኝ ቁጥር ከጎኔ አይጠፋም ከማንም በፊት ለምፈልገው ነገር ደራሽ ሆኖኛል። ምን ላድርግ በፍቅር ልክሰው ሲገባ እኔ ግን በችግር አረንቋ ተከብቤ ጊዜ እንኳን ሰጥቼ ደስተኛ አላደረኩትም እያልኩኝ ከእራሴ እየተሟገትኩ ስሄድ አስፓልቱ ዳር ጋር መኪናውን አየሁት..... እሮጬ ስሄድ መኪናው ውስጥ አልነበረም ተበሳጭቼ ልመለስ ስል ከኋላ መቶ አቀፈኝ እና በጆሮዬ "አፈቅርሻለሁ" አለኝ.... "እኔም አፈቅርሀለው" ብዬ ተጠመጠምኩበት..... ደስታ ተሰማኝ.....እፎይታ .... የመኪናውን በር ከፍቶልኝ ገብቼ ትምህርት ቤት አደረሰኝ።

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ብዙ ትዝታዎችን ያሳለፍኩበት.....ወደ እረፍት ከምውጣታችን በፊት ከግጓደኞቼ ጋር ደስተኛም ነበርን በዛውም ልክ ብዙ ውጣውረዶችን አሳልፈናል ግን ሁሉንም አብረን ነው የተወጣናቸው። ዛሬ ግን ብቻዬን ነው ያለሁት....ግቢ ውስጥ ሁሉም በእኛ ጓደኝነት ይቀናል... ከተማሪ እስከ አስተማሪ ስል እኛ እማያወራ የለም....ነገሮች በዚህ መንገድ እንዲሄዱ ፍላጎቱ አልነበረኝም.....ግን ደግሞ ሁሉም እሚሆንበት የራሱ ምክንያት አለው መቀበል ባልፈልግም መሆኑ እማይቀር ነው። ወደ ክላስ ስገባ እነሳቢ የበፊት ቦታችን ላይ ተደርድረዋል። ምንም ሳልሰራ እንደጥፋተኛ ሰው በሙሉ አይኔ ለማየት ፈራኋቸው አጠገቤ ያለው ወንበር ሄጄ ተቀመጥኩኝ ።

አንዳንዴ ሳንሳሳት ሳናጠፋ እኛ ትክክል ሆነን ሳለ ሰዎች እንደጥፋጠኛ ሲቆጥሩን አምነን እንቀበላለን። በውስጣችን እውነት እያለ ስህተት እንዳልሰራን እያነው ወቃሾቻችን ፊት ስንሆን ለምን የጥፋተኝነት ስሜት እንደሚሰማን አይገባኝም። ከአቤል በስተቀር ማናቸውም ሊያናግሩኝ አልመጡም....



ይቀጥላል....

ቀጣዩ ክፍል 100 ሲደርስ ይለቀቃል እያነበባችሁ አስተያየታችሁን አድርሱኝ...


ለአስተያየት - @Yetomah_Bot



✯┄┅┅✿❀ ❀✿┅┅┄✯
@Ketbeb_Mender
@Ketbeb_Mender
✯┄┅┅✿❀ ❀✿┅┅┄✯
3.6K views17:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ