Get Mystery Box with random crypto!

' ' ይቅርታ . . . ይቅርታ' ይቅርታ እናቴ . . . አደባባይ መሀል ላቆምኩት | ቅንድል ኢትዮጵያ

' " ይቅርታ . . . ይቅርታ"

ይቅርታ እናቴ . . .
አደባባይ መሀል ላቆምኩት ንፍገቴ
ሳመሽ ሌትሽ አልፎኝ - ስውል ቀንሽ አልፎኝ
ጠገብኩ እልሻለሁ ረሀብሽ ተርፎኝ !
ይቅርታ አባቴ . . .
አደባባይ መሀል ላቆምኩት ስስቴ
ከልጅነት ወኔ ለላቀው ሞገስህ
ከሞቴ ገዘፈ , ልጄ ፊት ማነስህ

ይቅርታ ወንድሜ . . .
አደባባይ መሀል ላቆምኩት ህመሜ
ከአቻ መንገዳችን ለናቅኩት ማጣትህ
ስጠኝ ማለት ከብዶህ ስጥል ለማንሳትህ

ይቅርታ እህቴ . . .
አደባባይ መሀል ላቆምኩት ሽንፈቴ
አጥሬን አጥሬን ስል ለጣልኩት አበባሽ
በሳቄ ትራፊ ለሚፅናናው እምባሽ

ይቅርታ . . . ይቅርታ አያቴ
ከሰማይ ለሰፋው አውላላው ንፍገቴ
አቅፎ ላሻገረኝ የቅንቀልባው ትከሻ
ከቀኔ ስኳረፍ ለገፋሁት ማምሻ . . . . .

ይቅርታ ይቅርታ ይቅርታ ይቅርታ


EYAYU FENGES (አጀንዳዬን) - GIRUM ZENEBE
@kendelM