Get Mystery Box with random crypto!

' ኤሴቅ ' ክፍል ~፪፻፴፬~ ( 234) በአምባዬ ጌታነህ @adwa_1888 **** ሔዋን የሁ | ቅን ልቦች

" ኤሴቅ "
ክፍል ~፪፻፴፬~ ( 234)
በአምባዬ ጌታነህ @adwa_1888


****
ሔዋን የሁላቸውንም ልብስ የቆሸሸውን ለሰራተኛዋ እየሰጠች ያልቆሸሸውን ደግሞ በስርአት እያስቀመጠች ነው። የሔመንን ክፍልም እያስተካከለች ሳለ አንድ የግል ማስታዎሻ የአልጋዋ ራስጌ ላይ አገኘች። ማስታወሻውን ለማየት ፈራ ተባ ብላ ከፈት አደረገችው። የማስታወሻው ደብተር መግቢያ ላይ በእጅ ፅሁፍ እንዲህ የሚል መልዕክት ሰፍሯል። "Irreversible Life "
A man who once walked as the wind blows.he let out a sigh of relief and put the blow to my heart. የምትል በእንግሊዝኛ የተፃፈች ቃል። ገፁን ገለጠችው። የቀዳማዊ ምስል አለ ከስሩ "the wing of my life"ይልና ገለጥ ስታደርገው "I fly with your wings! I am as far away as you have given me. But now my wings are weak.i can't go anywhere love.help me!! (በክንፎችህ በርሪያለሁ። በሰጠኸኝ ፍጥነት ልክ ርቂያለሁ። ነገር ግን አሁን ክንፎቼ ደክመዋል። አቅም አጥሮኛል የትም መሄድ አልቻልኩም ፍቅር። እርዳኝ!" የሚል ተማፅኖ የተቀላቀለበት ፅሁፍ ነበር። በርካታ ገፆችን ከምስል ጋር የሰፈረባቸውን የፍቅር መልዕክቶች በእንባ እየተሞላች አነበበቻቸው። ምንም እንኳ ሔመን ቀዳማዊን እንደምትወደው ብትገምትም ነገር ግን በዚህ ልክ በዚህ እርቀት ይሆናል የሚል ሀሳብ ፈፅሞ አልነበራትም።ሔመን ለአተመታት በቀዳማዊ ፍቅር ስትሰቃይ ብትቆይም ነገር ግን ሕመሟን ለራሷና ለራሷ ብቻ ነበር ይዛው የኖረችው። ሔዋን ያለችበት እስኪጠፋት ድረስ ተሰወረች።ራሷን ይዛ ለመቆም ሞከረች። ከዚህ ገፅ በላይ መሄድ አልቻለችም። የሔመንን የሕመሜ ቃላት መቀበል እስኪያቅታት ድረስ አመማት። በዚህን ጊዜ ሔመን በፈገግታ ታጅባ ስልክ እያወራች ወደ ቤት ገባችና ስትመለከት ማንም እንደሌለ ስትረዳ "ማንም የለም እንዴ ዝኑ?"አለች። "እትዬ ሔዋን አለች። ያንቺ ክፍል ውስጥ ናት"በማለት ጠቆመቻት። ሔመን ያቋረጠችውን ስልክ ቀጥላ እያወራች ወደ ክፍሏ ስትገባ ሔዋን የእሷን ማስታወሻ አቅፋ እያለቀሰች ነበር። ሔመን ስልኩን ዘግታ በቀስተ ተራመደችና ከእናቷ ጎን ጋደም አለችና እንባዋን አበሰችላት። ሔዋን ሔመንን ለደቂቃዎች ስትመለከታት ከቆየች በኋላ "ልጄ ለምን ይሄን ሁሉ ይሄን ያህል ጊዜ ይዘሽ?" አለች እንባዋን እያፈሰሰች። "ብታውቂ ምን ታደርጊ ነበር? አዎ ቀዳማዊ ላይ ተፅእኖ ትፈጥሪያለሽ። እኔን እንዲያገባ ጥረት ታደርጊያለሽ እሱንም ታስገድጅዋለሽ!"አለች ሔመን ፈገግ ብላ " ልጄ እንደዛ አይሆንም ቢያንስ ሁሉም ነገር በልክ ይሆን ነበር። በዛ ላይ ለእሱም ቢሆን አንቺ ነሽ የምትሻይው። ከማንም በላይ አብረሽው ኖረሻል አድገሻል"አለች ሔዋን። "አይ እማዬ ለእሱ ግን ከእኔ ይልቅ ሐምራዊ ትበልጥበታለች። እኔን ደግሞ በእህትነት ከሐምራዊ በላይ እንደሚወደኝ እንደሚሳሳኝ አውቃለሁ። እሱን ደስተኛ የሚያደርገው ሕይወት እንዲህ ሲሆን ነው። እኔም ቢያንስ በዚህኛው ደስተኛ እሆናለሁ። ባይሆን ኖሮ አንቺ እንዳልሺው ከመጀመሪያው እሱን እንዳገባ ብታደርጉ እሱ ለዘላለም እህት የሚባል ነገር አያውቅም። በእህቶቹ መጥፎ ጠባሳ አለበት። ስለዚህ ቀሪ እድሜውን ከሚሰቃይ እኔ ሕመሙን ብጋራው ይሻላል ብዬ ነው ለራሴ እንኳ ደግሜ ሳልናገር የያዝኩት። ቀዳማዊ ደስታ ብቻ ነው የሚገባው። እኔ ደግሞ የዛ ደስታው አጠልሺ መሆን አልፈልግም ። እኔን በሚገባ ሰርቶኛል። አሁን ያለሁበትን ስብዕናና ማንነት በእሱ ምስል የተገነባ ነው። ተመልከቺ እማዬ አሁን በጣም ጎበዝ ተማሪ ነኝ። ለዚህ ደግሞ ከፍተኛው ምሽጋና የሚወስደው ቀዳማዊ ነው። በሁሉም ነገር ጎበዝና ተፎካካሪ እንደድሆን፣ ሕይወትን በሌላ መነፀር መመልከት እንዳለብኝም ጭምር አስተምሮኛል። ስለዚህ ለዚህ ግብሩና ማንነቱ ደግሞ ሁሌም ሳፈቅረው እኖራለሁ። ነገር ግን የኔ ይሁን ማለቴ አይደለም። ፍቅር ፍቅር የሚሆነው ሁለቱም ተመሳሳይ ስሜት ሲኖራቸው ነው። ያንደኛው ብቻ ከሆነና የሌላኛው ሌላ ጋር ከህነ አይሰምርም። ቀዳማዊ ደግሞ የሚያፈቅራትን እሷም ስለምታፈቅረው ተገናኝተዋል። በነሱ መሀል ደግሞ መግባት ስላልፈለኩና የቀዳማዊ ደስታ ከእኔ ፍቅር ስለበለጠብኝ ሁሉንም ተውኩት"ብላ የእምባ ዘለላዎቿን በጉንጮቿ ላይ ጣለቻቸው። ሔዋን አቀፈቻትና "ለካ ያን ሁሉ ደስታ ስደሰት የነበረው በልጄ እንባና ህመም ኖሯል"አለች። "ተይ እማዬ እንደዛ አትበይ ቀዳማዊም ልጅሽ እኮ ነው። ምንም እንኳ እንዲህ ስትይ ባይሰማሽም ግን እኔ ይከፋኛል። ያራቅሽው ያህል ይሰማኛል። የእሱ ጥፋት ደግሞ ምንም ነገር የለም። የሆነ ነገር ጀምረን እሷን መርጦ ቢሄድስ እሺ ነገር ግን እንደማፈቅረው እንኳ የማያቅን ሰው መኮነን ተገቢ አይደለም እማዬ። ተረጋግተሽ አስቢና ለቀዳማዊ የነበረሽን ቦታ መልሺ። ትንሽ እንኳ ቅይር ብትይበት የምር እማዬ በጣም አዝንብሻለሁ ይከፋኛል። እኔ ቀዳማዊ ድጋሚ በቤተሰቦቹ እንዲያዝን አልፈፍግም። ለእሱ ያላችሁት ያለነው ብቸኛ ቤተሰቦቹ እኛ ነን። የኔ ሕይወት ይህ ጅማሮው ነው እንጅ መጨረሻው እንዳልሆነ በመረዳት ለእሱ ያላችሁ ቦታ እንዳይቀንስ አደራ እማዬ በእኔ ሞት ነው የምለምንሽ። እኔ እንደቀዳማዊ የማፈቅረውን ባይሆንም ምቾት የሚሰጠኝንና የሚያፈቅረኝን ወንድ መርጬ የእናንተን ደስታ እደግመዋለሁ እሺ እማዬ" ብላ ሔመን በልመና ጭምር ጠየቀቻት። "እሺ ልጄ ቃልሽን አከብራለሁ። ግን ደግሞ ይሄን መቀበል እንደሚከብደኝም እንድታውቂልኝ የኔ ቆንጆ"አለች ሔዋን መቋቋመም እያቃታት። ሔመን አባበለቻትና ወጥታ ወደ መናፈሻው ሄደች። ሔዋን አንድ በአንድ የሔመንን ሁኔታ ማስታወስ ጀመረች። የሰርጉ ጊዜ ራሱ ብዙም አልታየችም። ሰፊውን ጊዜ ክፍሏ ውስጥ ነበር ያሳለፈችው። ቀዳማዊን ቤት ስታጣው የምትነጫነጨው ነገር። ስታየው ደግሞ በስስትና በፍቅር አይኗ አይኖቹ ላይ የሚንከራተተውን ነገር አስታወሰች። እንደውም አቶ ሙሉሰው አንድ ጊዜ "ይቺ ልጅ ያለ ቀዳማዊ ሁሉንም ማድረግ አትፈልግም። እኔ አሁን አሁን እያሳሰበችኝ ነው። ያለ እሱ መኖርን የምትለምደው አይመስለኝም! "ብሎ ነበር። "እንዴት አይገባንም? የማንረባ እኛን ቢሉ ወላጆች። እኔን ቢሉ እናት? እንዴት ሁኔታዋን አይቼ ስሜቷን መረዳቴ ያቅተኛል?"አለችና ሔዋን በራሷ ተበሳጨች።
ሔዋን ያለውን ነገር ሙሉ በሙሉ እውነቱን ለሙሉሰው ነገረችው። ሙሉሰው በነገሩ ብዙም አልተገረመም። "እኔ አኳኋኗ አላማረኝም ነበር። ያው ብገምትም ደግሞ የቀዳማዊ ሁኔታ እንደ እህቱ ስለነበር የሚያያት ጉዳዩ በአጭር ይቋጫል ብዬ ነበር። ለማንኛውም ይሄ ያለፈ ምዕራፍ ነው። ሔሚ እንዳለችው ራሷን ለራሷ ነገ ታዘጋጃለች። አሁን ልጅ አይደለችም። ሁሉንም ነገር ግራና ቀኝ ታስተውላለች። ስለዚህ ለራሷ እንተውላት። ራሷ መፍትሔ ትስጥበት"አለ ሙሉሰው።
*
"ግን ቀዳ ኤሴቅ ማለት ምን ማለት ነው?"አለች ሐምራዊ። ቀዳማዊ ትንሽ አሰብ አደረገና ጉሮሮውን ጠራርጎ "የኔ ፍቅር #ኤሴቅ ማለት #የተጣላሁብሽ ማለት ነው። ይቺን ስም ያወጣት በመፅሐፍ ቅዱስ ውስጥ የአብርሃም ልጅ ይስሀቅ ነው። በፍልስጤሙ ሀገረ ገዥ በንጉስ አበሜሌክ ጊዜ የሆነ ታሪክ ነው። ይስሀቅ እየተገፋ እየሄደ በመጨረሻ ላይ ከሁሉመሰ ጋር ተጣልቶ ያገኛትን የውሃ ጉድጓድ ለእሱ ተስማሚ የሆነችለትን የውሃ ጉድጓድ ሰላማዊ ኑሮ እየኖረባት ያለችውን የውሃ ጉድጓድ የሰየማት "ኤሴቅ "ብሎ
ነው። ይቺ ጉድጓድ