Get Mystery Box with random crypto!

ከመፃሕፍት ጥግ

የቴሌግራም ቻናል አርማ kemtshafet_teg — ከመፃሕፍት ጥግ
የቴሌግራም ቻናል አርማ kemtshafet_teg — ከመፃሕፍት ጥግ
የሰርጥ አድራሻ: @kemtshafet_teg
ምድቦች: ስነ-ጽሁፍ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 281
የሰርጥ መግለጫ

"አንድ ሰው ለልጁም ይሁን ለመላው ማህበረሰብ ከሚሰጠው ስጦታዎች ሁሉ ትልቁ ስጦታ አንብቦ ሰዎችን እንዲያነቡ ማስቻሉ ነው!"
@kemtshafet_teg
@kemtshafet_teg_group

Ratings & Reviews

2.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-07-05 13:17:31
======= **** =======

ልጅነት የለሰለሰ መሬት ፣ ወጣትነት የአዝመራ ዘመን ፣ ሽምግልና ደግሞ የአጨዳ ዘመን መሆኑን አስተውል ።
በሽምግልናህ የምታጭደው የወጣትነትህን አዝመራ ነውና ዛሬ ለምትዘራው ዘር ተጠንቀቅ!

መልካም ቀን
=====ከመፃሕፍት ጥግ=====
213 viewsÑebiyat M., edited  10:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-05 07:53:15
===--- የተግባር ሰው! ---===

በየትኛውም መሥፈርት "እውቀት" ብቻ የሰውን ልጅ ህይወት ቀይሮ አያውቅም ። ሙሉ ጊዜህን እውቀት ለመሠብሠብ አታባክን መቼስ ውድ መኪና ለመግዛት የሚሯሯጥ ፣ ሁሌም ምርጥ መኪና የሚገዛ ግን አንድም ቀን ነድቶ የማያውቅ ሰው ብታይ ምን ሆኖ ነው ማለትህ አይቀርም።

አንተስ የሰበሰበከውን እውቀት መቼ ነው የምትጠቀመው? እቺን አለምን የቀየሯት ያወቁ ሳይሆኑ ያወቋትን ትንሿንም የተገበሩ ሰዎች ናቸው።

ያማረ ማክሰኞ ተመኘሁ

=========//////=========

ግሩፕፓችንን እና ቻናላችንን join አድርጉ

@kemtshafet_teg_group
2,900 በላይ አባል ያለው

@kemtshafet_teg
250 በላይ ሰብስክራይብ ያለው

======== **** ========

የፈለጉትን መፅሐፍት በቤቶ ሆነው ይዘዙን!
"ኤግላ የመፅሐፍት ዲሊቨሪ"
@Egla_Book_Delivery

ኤግላ ኢንቴሪየር ዲዛይን እና ጠቅላላ የፊኒሺንግ ስራ ተቋራጭ በቅርብ ቀን.....
275 viewsÑebiyat M., 04:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-04 21:10:34 ~የሆለታው የምሽት ጉዞ~

ክፍል 1

ታህሳስ 2014 እለተ እሁድ ዛሬ ከቀናቶች ሁሉ ደስ የሚል ቀን ነው። ሁሉ ነገር እንደሞላለት ሰው ፊቴ ላይ ልዩ የደስታ ስሜት ፊቴን ላየሁ ሁሉ የማይደበቅ የደስታ ስሜት ያታያል። ታዲያ ይሄ ሁሉ የደስታ ስሜት ሎተሪ እንደወጣለት፣ ነገሮች እንደተሳካለት ሰው ያደረገኝ በጣም የማፈቅራትን ከሳምንት በላይ በስራ ምክንያት የተለያኋትን ውዷን ፍቅረኛዬን የማገኝበት ቀን ስለሆነ ነው። ታዲያ እዚህም ሆና እኮ ከሳምንት በላይ ሳንገናኝ ቆይተን እናውቃለን። ነገር ግን ይሄን የተለየ የሚያደርገው እሷም እኔም በተነፋፈቅን ቁጥር ስልካችንን አውጥተን ተደዋውለን የናፍቆት ጥማታችንን በድምፆቻችን እናበርደው ነበር። ይሄ ደግሞ ከተመረቀች በኃላ የመጀመሪያ ስራዋ ነው ሊያውም ከ አዲስ አበባ ውጪ። ይሄ አዲሱ ስራዋ ደግሞ ከምሳ ሰዓት እና ማታ ካልሆነ በስተቀር ስልክ ማውራት አንችልም። ስራዋ በስልክ የሚሰራ እና ከብዙ ሰዎች ጋር የሚያገናኝ ስለሆነ እጅግ በጣም አድካሚ ስራ ነው ስለዚህ ማታ በጣም ስለሚደክማት ብዙ አናወራም። ስለዚህ አብረን ካሳለፍናቸው አመታት በተለየ አሁን ላይ ባትናፍቀኝ አይገርምም። በዛ ላይ ወደ አዲሱ የስራ ቦታዋ ወደ ዝዋይ ስትሄድ በእሷ በኩል በተፈጠረ ችግር ምክንያት ፈጣሪ እንዲያግዘን እና በተለየም ደግሞ ደጁን የረገጠ ልመናውን የተናገረ ሁሉ ይፈፀምለታት ሲባል ሰምቻለሁ እና ከረጅም ጊዜ በኃላ ከምስጋና ውጪ ፈጣሪን ከገጠመን ችግር እንዲያወጣን ለመፀለይ ስልኬን ዘግቼ ለ 2 ቀናት ደብረ ሊባኖስ ገዳም ሳልነግራት ሄጄ ስለነበረ ከዛ ስመለስ ነው እሷ ለስራ ወደ ክፍለ ሀገር መሄዷን ያወኩት።
እነዚህ ሁሉ ተደማምረው ስለነበረ ናፍቆቱን የተለየ አድርጎታል። በዛ ላይ ዛሬን ከተገናኘን በኋላ ነገ ጠዋት ደግሞ ወደ ሆለታ ለዚሁ ስራ ትመለሳለች። ስለዚህ አሁንም ተመልሰን ለሳምንት ስለማንገናኝ የዛሬዋን እሁድ ለኔ ልዩ ያደርጋታል።

ከፍቅር ጋር በልብ በጓደኝነት 4 በላይ በፍቅር ደግሞ 2 አመት አሳልፈናል። ታዲያ ሁል ጊዜ የምንገናኘው ልክ 7 ሰዓት ሲል ነው ብዙ ጊዜ ስንገናኝ ሰዓቱ ቶሎ ስለሚሄድብን ከሰዓታችን ላይ ላለመቀነስ በሰዓታችን ነው ምንገናኘው። እኔም በጣም ስለናፈቀችን ከሰዓቴ ቀደም ብዬ ሰፈሯ ደርሻለሁ እሷም እየጠበቀቺኝ ነው። እንደደረስኩኝ ስልክ ደውዬ በሯ ላይ መቆሜን ነገርኳት እና ከደቂቃዎች በኋላ በሩን ከፍታ ወጣች። ገና ሳያት ልቤ ውስጥ የተለየ የፍቅር ስሜት ይሰማኛል። ይገርማል! አመታትን እኮ ብዙ ጊዜያትን አብረን አሳልፈናል ነገር ግን ዛሬም አብረን ብዙ ጊዜያትን ያልቆየን ያህል ያልተቀየረ ልዩ ስሜት ዛሬም ድረስ ይሰማኛል። እውነት ነው በጣም ናፍቃኛለች እሷም እንደዛው ናፍቄያት ነበር። ተቃቅፈን ሰላም ከተባባልን በኋሏ መኪናችንን አስነስተን ከሰፈሯ መውጣት ጀመርን የሚገርመው እሷን ስለማግኘት እንጂ የት እንደምሄድ እንኳን በፍፁም አላሰብኩም ነበር። ምንም ሳናወራ በዝምታዎች እጇን እጄ ላይ እንደተቆላለፍን መኪናውን አስነስቼ እየነዳሁ ከሰፈሯ ወጣን።

ይቀጥላል...

ነቢያት ሙሉጌታ

=========//////=========

ግሩፕፓችንን እና ቻናላችንን join አድርጉ

@kemtshafet_teg_group
2,900 በላይ አባል ያለው

@kemtshafet_teg
250 በላይ ሰብስክራይብ ያለው

======== **** ========

የፈለጉትን መፅሐፍት በቤቶ ሆነው ይዘዙን!
"ኤግላ የመፅሐፍት ዲሊቨሪ"
@Egla_Book_Delivery

ኤግላ ኢንቴሪየር ዲዛይን እና ጠቅላላ የፊኒሺንግ ስራ ተቋራጭ በቅርብ ቀን.....
279 viewsÑebiyat M., 18:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-04 21:10:22
301 viewsÑebiyat M., 18:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-04 18:02:19
214 viewsÑebiyat M., 15:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-04 13:12:10
========== **** ==========

ዓይንህ የፊቱን ቢያይ ልብህ የኋላውን ያስብ....ነገ ላይ እንድትደርስ የትናንቱን አትርሳ... የምትሄድበት እናዳይጠፋህ በፍፁም የመጣህበትን አትዘንጋ!

መልካም ቀን
=====ከመፃሕፍት ጥግ=====
225 viewsÑebiyat M., 10:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-04 09:45:49
=====----- ወስን! -----=====

ህይወትህን እስከመጨረሻው የሚቀይረው አንድ ውሳኔ ሊሆን ይችላል! በቃ ህይወቴን የምቀይረው እኔ ነኝ! ማንንም አልጠብቅም ከፈጣሪ ጋር ለራሴ ያለሁት እኔ ነኝ። ያኔ አይምሮህ ራሱ የምትፈልገውን እንታሳካ ክፍት ይሆናል!
ስለዚህ ወስንና ወደ ተግባር ግባ!

የሀሳብ ሳይሆን የተግባር ሰኞ ተመኘሁ


ሰኞ የአዲስ ነገሮች ሁሉ ለመጀመር እና ለመሞከር የሚመከርባት የተጀመሩትንም በአዲስ ሞራል እና ወኔ ለማስኬድ የምትመረጥ ቀን ናት ተጠቀሙበት!

=========//////=========

ግሩፕፓችንን እና ቻናላችንን join አድርጉ

@kemtshafet_teg_group
2,900 በላይ አባል ያለው

@kemtshafet_teg
250 በላይ ሰብስክራይብ ያለው

======== **** ========

የፈለጉትን መፅሐፍት በቤቶ ሆነው ይዘዙን!
"ኤግላ የመፅሐፍት ዲሊቨሪ"
0963-368686

ኤግላ ኢንቴሪየር ዲዛይን እና ጠቅላላ የፊኒሺንግ ስራ ተቋራጭ በቅርብ ቀን.....
271 viewsÑebiyat M., 06:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-01 20:02:39
ሰላም... ሰላም... የመፅሐፍት ጥግ ቤተሰቦች እንዴት አመሻችሁልኝ? ሰላማችሁ በያላችሁበት ብዝት ይበልልኝ

ከመፅሐፍት ጥግ ግሩኘ እና ቻናል ላይ በተከታታይ የተለያዩ እውነታኛ ታሪኮችን እና የተለያዩ መፅሐፎችን በPdf ከማብራሪያ ጋር እንዲሁም ቁጥራቸው በዛ ላሉ ቤተሰቦች ደግሞ በውስጥ በስመር የተለያዩ መፅሐፎችን አቅሜ በፈቀደ መልኩ ስልክላቹ ቆይቻለሁ።
አሁን ከእሱ በተጨማሪ አዳዲስ አገልግሎቶችን በቅርብ ቀን ጠብቁ ባልኳቹ መሰረት ከአንዳንድ ቤተሰቦች በተነሳ ጥያቄ መፅሐፎችን ቤት ለቤት የማድረስ አገልግሎት እንድንሰጥ ስትጠይቁን ለነበራችሁ ቤተሰቦች ከጃፋር መፅሐፍት መደብር ጋር በመተባበር በምወደው ስም
"ኤግላ የመፅሐፍት ዲሊቨሪ"
በሚል ስያሜ ወደ ስራ ለመግባት ዝግጅታችንን ጨርሰናል።
ወደ እዚህ ስራ እንድንገባ ሀሳባችሁን እና ፍላጎታችሁን ላሳያችሁን ቤተሰቦች ልባዊ ምስጋናን አቀርባለሁ። ከመጪው ሳምንት ጀምሮ ቤት ለቤት የማድረስ አገልግሎቱን የምንጀምር ይሆናል ይጠብቁን።

ነቢያት ሙሉጌታ
ከመፅሐፍት ጥግ አድሚን


ኤግላ የመፅሐፍት ዲሊቨሪ

=========//////=========

ግሩፕፓችንን እና ቻናላችንን join አድርጉ

@kemtshafet_teg_group
2,900 በላይ አባል ያለው

@kemtshafet_teg
250 በላይ ሰብስክራይብ ያለው

======== **** ========

ኤግላ ኢንቴሪየር ዲዛይን እና ጠቅላላ የፊኒሺንግ ስራ ተቋራጭ በቅርብ ቀን.....
451 viewsÑebiyat M., 17:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-30 20:05:30 ​ ሃናን ​

ክፍል-29

#የመጨረሻው_ክፍል

...ያ ሁሉ የሆን በምክንያት ነበር (የፃፍኩት) ምን አልባት በሆነው ነገር ጥቂት ሰው ትምህርት ወስዶበት ሊሆን ይችላል...

...ፍቅር የልብ መገጣጠም ነው! የምታፈቅራት ሴት እንደምታፈቅራት ባትነግራት እንክዋን እስዋም የምታፈቅርህ ከሆነ ፍቅርህ ይገባታል ከአይኖችህ ታነባለች በድምፅህ ቅላፄ የፍቅርህን መጠን ታውቃለች "ምን ያህል ታፈቅረኛለህ?" ብላ አጠይቅህም ምክንያቱም በድምፅህ ቅላፄ የሚወጣው ቃላት ልብዋ ዘልቆ ይገባል በአይንዋ ሳይሆን በልብዋ ታይሃለች በልብ (ከውስጥ) የታየ እይታ ደሞ ምን ጊዜም ሃቅና ግልፅ ነው ለዛ ነው ብዙ ሰው ይሳሳትና በስህተቱ ልክ ልትቀጡት ስትፈልጉስህተቱን ለማስተባበል ይሞክራል "እኔኮ ለማለት የፈለኩት እንደዚ ነው" ወይም "እኔኮ ይሄን የምሰራው ለዚህ ብዬ ነው" በማለት ጥፋቱን ያስተባብላል የሱን ስህተት ከልብ ካያችሁት (በሱ ቦታ ሆናቹ ካያችሁት) ስህተቱ ስህተት ቢሆን እንክዋን ማስተዛዘኛ ትሰጡታላቹ "ይህ ያደረገውኮ ምን አልባት ለዚ ብሎ ይሆናል" ትላላቹ ይህ ነው የልብ እይታ ሚባለው ...(ከፈለጋቹ ፍልስፍና በሉተ)

...አንድ ያልነገርክዋቹ ነገር ላጫውታቹ በፊት ኮሌጅ እየተማርኩኝ ሳለው ጋደኛዬ አህላም ጋደኛችንን ሰሚራን ሁሌም በስህተት ትፈርጃታለች ከወንዶች ጋር ስትሆንና ስትሳሳቅና ስትጫወት ካየች ትናደድባታለች ትቆጣትም ነበር "ለምን ይህን ታደርጊያለሽ አላህን አትፈሪምን?" ትላታለች የሰሚራ መልስ ሁሌም "አንቺኮ አልገባሽም ተይው ምን አልባት አንድ ቀን ትረጂው ይሆናል" ትላትና ትሄዳለች አህላምም ተናዳባት ትተዋታለች ሁለቱም ግን በጣም ይዋደዳሉ እኔንም በጣም ይወዱኛል እንም እንደዛው...

...እንደነገርክዋቹ አህላም ሁሌም ሰሚራት ይህ ልክ አይደለም እንደዚ አድርጊ እያለች ትቆጣታለች ታድያ አንድ ቀን የኔን ልደት ለማክበር ይመስለኛል ቤት መተው ነበር ሰሚራ በለበሰችው ልብስ የተሸማቃለች የደበራት ትመስላለች እውነትም የለበሰችው ልብስ ይከብዳል ማለት ያን ያህል ባያጥርም አጥሮ ግን ነበር በማጠሩ ተሸማቃለች እንደ በፊቱ አትጫወትም ጥግ ቁጭ ብላ ነበር አህላም ያ ቀይ ፊትዋን እሳት አስመስላው ለሰሚራ እንዲ አለቻት "በለው ዛሬ ምነው ለቀቅሽ እንዴ? ምን አይነት አለባበስ ነው?" ብላ ልክ እንደናት ተቆጣቻት በዚ ጊዜ ሰሙ ተናዳ ከሳሎኑ ወጣች እኔም ለአህላም "ምነው አሁንስ አበዛሺው እንዴት እንደዚ ትናገሪያታለሽ ትንሽ እንክዋን ለሞራልዋ አትጨነቂም?" ብዬ ተቆጣዋት አህላምም "ሃኒ ወላሂ እንዲከፋትኮ አልነበረው የለበሰችው ልብስ የሙስሊም አደብ አይደለም በጣም አጥሯል ለዛ ነውኮ" አለቺኝ እኔም "እኮ እንደዚ አልነበረማ" ብያት ተነስቼ ወደ ሰሙ ሄዱኩኝ ሰሙን አይዞሽ ውዴ ብዬ አፅናናዋትና አቀፍጅዋት በዚ ጊዜ ልብ የሚነከ ፈፅሞ ያልጠበኩትን ንግግርን ነገረቺኝ፦

"ሃኒ ሳላውቅ ቀርቼኮ አይደለም ችግር ያለብኝ ሰው ነኝ ከወንዶች ጋር እንደዛ ምሳሳቀውና ምጫወተው ፈልጌው አይደለም ወንዶችን በጣም እፈራለው የሆነ ነገር ካረጉኝ ብዬ እሰጋለው የዘውትር ጭንቀቴ ወንዶች ካሁን አሁን ምን አረጉኝ የሚለው ነው ለዛ ነው ከወንዶች ጋር ቀርቤ እንደነሱ ምሆነው ቢያንስ እንክዋን እቺማ ዱርዬ ናት ብለው እንዲርቁኝ ወይም ስለኔ እንዳያስቡ ስለምፈልግ ነው...

...ዛሬ የለበስኩት ቀሚስ ደሞ በሰዎች እይታ ዱርዬ መስዬ ለመታየት ነው ምክንያቱም ለዱርዬ ሴቶች ማንም ቦታ አይሰጥም በተሌ ወንዱ" አለቺኝ በአነጋገርዋና በአስተሳሰብዋ በጣም አዘንኩኝ ሰሙ እንደዚ አይነት ሰው አትመስለኝም ነበር በራስ መተማመንዋ የገነነ ጀግና ሴት አድርጌ ነበር ምስላት ታድያ ያሰብኩት ያሰብኩት አልነበረም ሰሙ ሌላ ታሪክ ውስጥ ገብታ ነበር ...

...ለአህላምም ሁሉንም አጫወትኩዋት አህላምም ደነገጠች ያኔ ሳተውቅ በተናገገረቻት ነገር አዘነች አህላም አንባቢ ስለነበረች አንድ መፃፍ ሰጠቻት (ጠብታ ማር) የሚል ርዕስ ነበር ይህ መፃፍ ከአላህ በኃላ በራስ መተማመንዋን መለሰላት...

..ከሃሜቱ እንውጣ, ብዙዎቻችን የሆነ ጉድለት አለብን ያንን ለመሸፈን ብለን በዙ ያልተገቡና መሆን የሌለባቸውን ነገራቶች እናደርጋለን የምናደርገው ነገር ልክ እንሁን ወይም ስህተት አናውቀውም በቃ በሰዎች ፊት የበታችነት ስሜት እንዲሰማን አንፈልግም(ይህ ልክ ነው) ነገር ግን ከልክ ያለፈ ጥርጣሬና ፍራቻ ከውስጣችን እናውጠ ሁለተኛው ማንነታችንን እናዳምጠው ሁለተኛው ማንነታች ፍፁም ልክ ነው ሁለተኛው ማንነታችን መሪያችን ነው (ተረገግቶ አስቦ የተናገረ... ) ይባል የለ ስትረጋጋና ስታስብ ከሁለተኛው ማንነትህ ጋር ትነጋገራለህ ሁለተኛውም ማንነተህ ደሞ ቅኑን መንገድ ይጠቁምሃል...

የኔ ታሪክ እዚ ጋር አብቅቷል ማናችንም መጀመሪያችን ላያምር ይችላል ይህ የኛ ጥፋት ሳይሆን የፈጣሪያችን ውሳኔ ነው ስለዚ መጨረሻችንን ለማሳመር ሁላችንም እንሞክር, እንጣር ወደ ጌታችን እንቅረብ እመኑኝ ወደ ጌታው የቀረበ ሁሉ ልዩዎች ናቸው ሁሉ ነገራችን እያማረ ይመጣል ውዶቼ አንሰሳት ማለቴ አይደለም ስህተትን አናብዛ ስህተቶቻችን መማሪያ ይሁኑን... ውድዋ እህቴ ውዱ ወንድሜ ሰለ ነጊያችን እናስብ ጊዜያዊ ነገር ሁሉ ለተራ ሰዎች እንጆ ለኛ አይነቱ (ለሙስሊም) የተገቡ አይደሉም ጌዜያዊ ነገር እንዳያምረን እንዳያታለንም...

#ተፈፀመ


አብራችሁኝ የቆያቹ ሁሉ ከልብ አመሰግናለው
የሃናን ታሪክ እንዴት ነበር? እስቲ በውስጥ መስመሬ ንገሩኝ ምን ተማራቹበት...?
@Nebiyat_M

ነገ በአዲስ ታሪክ "የሆለታው የምሽት ጉዞ" በሚል ከቀናቶች ባንዱ ቀን የገጠመኝን በመጀመሪያ ፁሁፌ እንገናኛለን መልካም አዳር ተመኘሁ

=========//////===========

ግሩፕፓችንን እና ቻናላችንን join አድርጉ

@kemtshafet_teg_group
2,900 በላይ አባል ያለው

@kemtshafet_teg
250 በላይ ሰብስክራይብ ያለው

========== **** ==========

ባለፈው ቃል በገባሁላችሁ መሰረት "የሆለታው የምሽት ጉዞ" ከቀናቶች ባንዱ ቀን የገጠመኝን የመጀመሪያ ፁሁፌን "የሃናን" እውነተኛ ታሪክ እንዳለቀ የሚጀመር ይሆናል አብራችሁኝ ቆዩ
270 viewsÑebiyat M., 17:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-30 20:03:24
202 viewsÑebiyat M., 17:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ