Get Mystery Box with random crypto!

~የሆለታው የምሽት ጉዞ~ ክፍል 5 ከነገ ጀምሮ ማድረግ ያሉብኝን ሁሉ ማሰብ ጀመርኩኝ 1ኛ) | ከመፃሕፍት ጥግ

~የሆለታው የምሽት ጉዞ~

ክፍል 5

ከነገ ጀምሮ ማድረግ ያሉብኝን ሁሉ ማሰብ ጀመርኩኝ 1ኛ) አልኩኝ ቤተሰቦቿን ግንኙነታችንን ሁሉም ቢያውቁም እኔ እና እሷ ግን እነሱ ከሚያስቡት በላይ በጣም እንደምንፈቃቀር እና መለያየት በፍፁም እንደማንችል የት እንደሆነ ባላውቅም አግኝቻቸው በክብር ቁጭ ብዬ አናግራቸዋለሁኝ አልኩኝ። 2ኛ) ለጉዞው እና ለፕሮሰሱ ከዚህ በፊት ያወጡትም ወጪ ስለሚኖር ያሉኝን ሁለት መኪናዎች ሸጬ ያወጡትን ወጪ በሙሉ መልሼ ለለፉበት እና ከሀሳባቸው ደግሞ ስላሰረዝናቸው ተንበርክኬ እና ጉልበት ስሜ በክብር ይቅርታ እጠይቃለሁ።
3ኛ) እኔ እና እሷ እስከዛሬ ስናስበውን የነበረውም አብረን የመኖር ሀሳቦች፣ ለማድረግ ያሰብናቸውን ሀሳቦች ሁሉ፣ ትምህርቷንም መማር በፈለገችበት ፊልድ የፈጀውን ይፍጅ የኔ ስራዬ ቢቀዘቅዝ እንኳን ተቀጥሬ እየሰራሁ እየተጋገዝን ማስተርሷን ትጀምራለች፣ በተረፈችን ትንሽ ብር ደግሞ የተለያዩ በኔም በሷም በኩል የተለያዩ ቢዝነሶች እንጀምራለን፣ እሷ የምትፅፋቸው ፁሁፎች እኔም እያገዝኳት ብዙ በመፅሕፍትን እናሳትማለን በክብርም ታላላቅ ታዋቂ ሰዎች እና የሷ ቤተሰቦች በተገኙበት እናስመርቃለን ያኔ ሁሌም እንደማስበው እና እንደምመኘው በዙሪያዬ ካሉት ከማውቃቸው ሰዎች፣ ከጓደኞቿ፣ ከቤተሰቦቿ በላይ ከፍ እንድትል እንደስከዛሬው ሁሉ የበለጠ እጥራለሁ፣ የራሳችንን ቤት እኔና እሷ ባወራንበት መልኩ ከከተማ ወጣ ብለን እስከምንሰራ ድረስ ተከራይተን ወተን የራሳችንን ኑሮ እንመሰርታለን ከዛም ለብዙ ጊዜ በጉጉት የምጠብቀውን የ ፕሮሚስ ቀለበት እኔ እና እሷ ብቻ ፈጣሪ በሁለታችንም ልብ ውስጥ በልዩ ሁኔታ ባኖረው ጥንታዊው የላሊበላ ውቅር አቢያተክርስቲያን ላይ ተንበርክኬ ቀለበት አስርላታለሁ፣ ንሰሀም ተቀብለን ለአዲሱ ትዳራችን መሰረት ጥለን እንመለሳለን አስፈላጊ ነው ብለን ተነጋግረን ባመንን ሰዓት ወደ ታላቁ ህይወታችን ወደ ትዳር እንገባለን አልኩኝ።
ያሰብኩት ሁሉ በቅደም ተከተል በተግባር አድርጌ ከዚህ ሀሳብ እና ችግር ከፈጣሪ ጋር መውጣት እንዳለብኝ ለራሴ ነገርኩት። አዎ! ደግሞም እኔ የወሬ ሳልሆን የተግባር ሰው ነኝ! ስለዚህ አደርገዎለሁኝ! አልኩኝ። እንደ ቅደም ተከተሉ ለእርሷ የሚነገረው እየነገርኳት የማልነግራትን በሰዓቱና በጊዜው ሲደርስ እነግራታለሁ ብዬ ወሰንኩኝ። አሁን ከመኪኖቹ መጀመር አለብኝ የግድ ቶሎ ሁለቱም መኪኖች መሸጥ አለባቸው ነገር ግን ለሷ ይሄንን ከነገርኳት የኔ እንደዚህ ማድረግ በጣም ስለሚከብዳት በፍፁም ሳልነግራት ማድረግ እንዳለብኝ ወሰንኩኝ። የኔንም ቤተሰብ ይህንን ሳደርግ ምን እንደሚሉኝ አውቃለሁ ግን ቁጭ ብዬ እነግራቸዋለሁኝ አዎ... እሷን ከማጣ ምንም ነገር ልጣ ስለዚህ እኔን ልጃችሁን ደስተኛ ሆኞ እንድኖር ከፈለጋችሁ በዚህ ጉዳይ ማንም እንዳይገባብኝም እንዳይናገረኝም ብዬ ለማስረዳት እሞክራለሁ ካልተረዱኝም ምንም ማድረግ አልችልም የራሴ ንብረት ነው ማንም አያስቆመኝም። ስለዚህ ከነገ ጀምሮ ገዢ እፈልጋለሁ ለሷ ስል ምንም ባጣ ምንም አይመስለኝ አይደለም መኪና ህይወቴንም የምሰጣት ፍቅረኛ ነች ይሄንን ደግሞ አሁን ይሄ ችግር ስለመጣ ሳይሆን በፊትም በሷ ድርድር እንደማላውቅ ጠንቅቃ በደንብ ታውቃለች። ስለዚህ ይሄንን አድርጌ በታክሲ እየተሰለፍኩ ወይም በእግር ብንቀሳቀስም ተቀጥሬም ዝቅ ብዬ ብሰራ ምንም አይመስለኝም። እንደውም እንደዛ መሆኔ ይበልጥ ያጠነክረኛል እንጂ አያሰንፈኝም ንብረቱንም ከሷ ጋር አብረን ሆነን ሰርተን እናመጣዋለን አለቀ እንደዛ ነው መሆን ያለበት አልኩ። እሱን እና ሌሎች ማድረግ ስላለብኝ ነገሮች ስለሚፈጠሩት ነገር እየመላለስኩኝ እያሰብኩኝ ምንም እንቅልፍ ሳይወስደኝ ከለሊቱ 9 ሰዓት ሊል ሲል ትንሽ ሸለብ አደረገኝ። 11 ሰዐት ሲል አላርሜ መጮህ ጀመረ ምንም ሳልቆይ ልብሴን ለባብሼ ወደ መኪናዬ ሄድኩኝ እና መኪናዬን ማሞቅ ጀመርኩኝ የምወደውን የመዝሙር ክላሲካል ከፍቼ ጉዞዬን ወደ ሰፈሯ አደረኩኝ 11:45 አካባቢ ሰፈራ ደረስኩኝ እና 12 ሰዓት እስኪል እዛው መኪናዬ ውስጥ ቁጭ አልኩኝ ልክ ሰዐቱ ሲደርስ እየደረስኩ መሆኔን ቴክስት አደረኩላት። እሷም ትንሽ ቆይታ ደወለች እና "እሺ እየጨረስኩኝ ነው ጠብቀኝ" ብላኝ ስልኩን ዘጋችው። እሷ እስከምትወጣ በራቸው ላይ ቆሜ ከግቢያቸው ውሻ (ሲምባ) ጋር ቁጭ ብለን ከተወሰኑ ደቂቃዎች በኋላ የጊቢውን በር ከፍታ ወጣች ተቃቅፈን ሰላም ከተባባልን በኃላ ጉዞአችንን ወደ ሜክሲኮ ጀመርን ልክ ለ 1 ሰዓት የተወሰኑ ትንሽ ደቂቃዎች ቀርቶታል አብራት የምትሄደው የስራ ጓደኛዋ እዛው መኪናው የሚነሳበት ቦታ ላይ እንደደረሰች ደውላ ነገረቻት። እሷም ደርሻለሁ አለቻት እና ስልኩን ዘጋችው። አይን አይኔን እያየች "በጣም አፈቅርሀለሁ" ትለኛለች እኔም ከሷ የበለጠ እንደማፈቅራት እየነገርኳት ሜክሲኮ ደረስን በነገር ግን ጓደኛዋ በዛ ብርድ ላይ ቆማ እየጠበቀቻት መሆኑን ባቅም 5 ደቂቃ ብቻ እባክሽ ስጪኝ አልኳት እና አደባባዩን ዞሬ....

ይቀጥላል

ነቢያት ሙሉጌታ

=========//////=========

ግሩፕፓችንን እና ቻናላችንን join አድርጉ

@kemtshafet_teg_group
2,900 በላይ አባል ያለው

@kemtshafet_teg
250 በላይ ሰብስክራይብ ያለው

======== **** ========

የፈለጉትን መፅሐፍት በቤቶ ሆነው ይዘዙን!
"ኤግላ የመፅሐፍት ዲሊቨሪ"
@Egla_Book_Delivery

ኤግላ ኢንቴሪየር ዲዛይን እና ጠቅላላ የፊኒሺንግ ስራ ተቋራጭ በቅርብ ቀን.....